ኢዜአ - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር በተለያዩ አማራጮች ለመፍታት እየተሰራ ነው
Aug 5, 2024 111
ሀዋሳ ፤ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፦የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር በተለያዩ አማራጮች ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለ1 ሺህ 108 የመንግሥት ሠራተኞች ለጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚሆን ቦታ ዛሬ በእጣ አስተላልፏል። በቦታ ርክክቡ ላይ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ እንደገለጹት የቤት ጉዳይ ይበልጥ በከተሞች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል። ችግሩን ለማቃለል አስተዳደሩ ለስራው አመቺ የሆኑ መመሪያዎችን በማውጣት ለተግባራዊነቱ በሙሉ ቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ ነው ሲሉም ጠቁመዋል። በተለይ የመንግሥት ሠራተኛውን በቤት ልማት አማራጮች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ በዛሬው እለት ለ1ሺህ 108 የመንግሥት ሠራተኞች የቤት መስሪያ ቦታ ተላልፏል ብለዋል። መሠረተ ልማት የተሟላለት 51 ሺህ 950 ካሬ ሜትር ቦታ የተላለፈው በመኖሪያ ቤት ሕብረት ሥራ የተደራጁ 35 ማህበራት ለግንባታው ሂደት አስፈላጊውን ገንዘብ በመቆጠባቸው መሆኑንም ገልጸዋል። በቀጣይም ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ በአቅሙ ልክ ሊሳተፍበት የሚችልበትን የኮንዶሚንየም ቤት አመራጭ አስተዳደሩ በማዘጋጀት በቅርቡ ምዝገባ እንደሚጀምርም አመልክተዋል። የሲዳማ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ በበኩላቸው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በክልሉ በከተሞች ለሰው ተኮር ልማት ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ የህብረተሰቡ ችግር እየተቃለለ መጥቷል። በክልሉ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው አንዱ የቤት መስሪያ ቦታ ማመቻቸት መሆኑን ጠቅሰው፣ ቦታውን ያገኙት እድለኞች ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ በማካሄድ ለከተማዋ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ቢሮውም የዲዛይን ክትትልና ቁጥጥር ከማድረግ ባለፈ በግንባታ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ካገኙት መካከል አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ይሁንሰው አብርሃም ቦታ ለማግኘት በማህበር ተደራጅተው በየወሩ ሲቆጥቡ መቆየታቸውን ገልጸዋል። አሁን ላይ በከተሞች ያለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ እየጨመረ መምጣቱ በተለይ ለመንግስት ሠራተኛውና ዝግቀተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ከአቅም በላይ መሆኑን ተናግረዋል። ከተማ አስተዳደሩ ይህን ችግር አይቶ የቤት መስሪያ ቦታ በመስጠቱ አመስግነው በቅርቡ የቤት ባለቤት የመሆን ተስፋ ሰንቂያለሁ ሲሉ ገልጸዋል። የጤና በለሙያ አቶ ባርናባስ ተስፋዬ በበኩላቸው እሳቸውን ጨምሮ የቤት መስሪያ ቦታ የተሰጣቸው የመንግስት ሠራተኞች ለረጅም ጊዜ በኪራይ ቤት ሲኖሩ እንደነበር አስታውሰዋል። የተሰጣቸው የቤት መስሪያ ቦታ ከቤት ኪራይ ወጪ በዘላቂነት ለመገላገል ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል። ሠራተኞቹ ከተማ አስተዳደሩ አሁን የጀመረው የመኖሪያ ቤት ችግር የመፍታት ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።
በክልሉ በግብይት ወቅት ሕገ ወጥ ተግባር በፈጸሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
Aug 5, 2024 110
አርባ ምንጭ ፤ ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በግብይት ወቅት ሕገ ወጥ ተግባር የፈጸሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ። የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በህገ-ወጥ የንግድ ስርአት ቁጥጥርና ገበያ ማረጋጋት ላይ በተዋረድ ከሚገኙ መዋቅር ሥራ ሃላፊዎች ጋር በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ ውይይት አድርጓል። በዚህ ወቅት የቢሮ ሃላፊው አቶ ገሌቦ ጎልሞ እንደገለጹት፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ተከትለው በግብይት ወቅት ሕገ ወጥ ተግባር የፈጸሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል። በክልሉ አንዳንድ ነጋዴዎች በግብይት ወቅት ህገ ወጥ ተግባር እንደፈጸሙ ጠቁመው፤ በተለይ ምርቶችን የመደበቅና የማሸሽ ህገ ወጥ ተግባራት መኖራቸውን በተደረገ ምልከታ መረጋገጡን ተናግረዋል። በክልሉ በየደረጃው የአስተዳደር፣ የፀጥታ፣ የፍትህና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያካተተ የህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ-ሃይል መኖሩንም ጠቁመዋል። ግብረ-ሃይሉ ባለፉት አምስት ቀናት በ304 የንግድ ድርጅቶች ላይ ባደረገው የክትትልና ቁጥጥር ሥራ በንግድ ልውውጥ ወቅት ሕገወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በተገኙ 44 የንግድ ድርጅቶች ላይ ማሸግን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች መወሰዱን አብራርተዋል። የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ከህገ ወጥ ድርጊት በመቆጠብ በተጠያቂነት መንፈስ ሥራቸውን ማከናወን ይገባቸዋል ሲሉም አሳስበዋል።
ቅን ኢትዮጵያ ማኅበር ዜጎችን ለበጎ ዓላማ እንዲሰለፉ የጀመረው ጥረት ሊጠናከር ይገባል
Aug 5, 2024 112
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2016(ኢዜአ)፦ቅን ኢትዮጵያ ማኅበር ዜጎችን ለበጎ ዓላማ እንዲሰለፉ የጀመረው ጥረት ሊጠናከር ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ቅን ኢትዮጵያ ማኀበር በቅንነት፣ በጎ አሳቢነትና ሠላም ግንባታ ላይ ለተማሪዎች፣ ለወላጅ ተወካዮችና መምህራን ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ዛሬ ተጠናቋል። ሥልጠናው ለአንድ ሳምንት የተሰጠ ሲሆን "ተማሪ ለሀገር ሠላም" በሚል መሪ ኃሳብ ተካሂዷል። የሥልጠናው ተሳታፊዎችም በአዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሳቢያ፣ የአንድነት ፓርክ፣ ወዳጅነት አደባባይ፣ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ሥራዎችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። የሥልጠናው ማጠቃለያ መርኃ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ቅንነት፣ መልካምነትና መተሳሰብ እንደ አገር አብሮ ለመቆም፤ ለዘላቂ ሠላም መረጋገጥ ቁልፍ ሚና አለው። ሠላም ደግሞ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ መሰረት ነው ያሉት ከንቲባዋ ሁላችንም ተባብረን መሥራት አለብን ሲሉም ተናግረዋል። ቅን ኢትዮጵያ ማኅበርም የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎችን በማሰባሰብ ለበጎ ዓላማ እንዲሰለፉ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው ቀጣይነትም ሊኖረው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። የቅን ኢትዮጵያ ማህበር የቦርድ ሊቀ መንበር መሰረት ስዩም በበኩላቸው የሥልጠናው ተካፋዮች አገር ከእናንተ ብዙ ትጠብቃለች፤ የቀሰማችሁትን እውቀት ወደ መጣችሁበት አከባቢ በማስፋፋት ቅን ማኅበረሰብ የመፍጠር ጥረቱን ማጠናከር አለባችሁ ብለዋል። የቅን ኢትዮጵያ ማኅበር መሥራች አባል መሰለ ሃይሌ በኢትዮጵያ ቅንነት እንዲዳብር ማህበሩ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል። ከረጅም ጊዜ አኳያ የቅንነት ባህል እንዲሁም የሠላም እሴቶች መገንባት ላይ የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት የግንዛቤ ለውጥ እንዲመጣ እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። ለአንድ ሳምንት ያህል "ተማሪ ለሀገር ሠላም" በሚል መሪ ኃሳብ የተሰጠው ሥልጠናም የዚሁ አካል ነው ያሉት አቶ መሰለ ይሄው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በሥልጠና መርሃ ግብሩ ላይ ወላጆችን ወክለው ከተሳተፉ መካከል ከኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሶኮሩ ወረዳ የመጡት ሙኢዲን አባቦራ አባሱራ፤ ሥልጠናው ለአገሬ በተነሳሽነትና ከልብ በመነጨ ስሜት በትጋት መስራት እንዳለብኝ ግንዛቤ የጨበጥኩበት ነው ብለዋል። ከአማራ ክልል ባህዳር ከተማ ጊዮን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተወከለችው ተማሪ ትንሳኤ እስጢፋኖስ በበኩሏ በሥልጠና ቆይታዬ አንድነታችንን የበለጠ የሚያጠናክሩ ኃሳቦችን ገብይቻለሁ ብላለች። ከአፋር ክልል ሎጊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጣው ተማሪ ዑስማን መሀመድ በሰጠው አስተያየት በኢትዮጵያን በተሻለ መልኩ ለማገልገል ዝግጁ ነኝ፣ በሠላም በኩልም የሚጠበቅብኝን ድርሻ ላይ በቂ ግንዛቤ ወስጃለሁ ብሏል።
በክልሉ ምርታማነትን መጨመርና ገቢ የመሰብሰብ አቅምን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ
Aug 5, 2024 106
ባህር ዳር ፤ ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የኑሮ ውድነትን ለመከላከል ምርታማነትና ገቢን ማሳደግ ላይ አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ። የክልሉ የከተማ ልማት ክላስተር በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ፖሊሲ የትኩረት ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረክ በባህር ዳር ከተማ አካሂዷል። በዚሁ ወቅት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እንደገለጹት፤ በአዲሱ ዓመት አመራሩ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ በየዘርፉ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ሥራዎች ላይ በትኩረት ይሰራል። እንዲሁም የክልሉን የገቢ አቅም ማሳደግ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ገቢ የመሰብሰብ ሥራ ለገቢዎች ተቋም ብቻ የሚተው እንዳልሆነ ተናግረዋል። ለዚህም ከላይ እስከታች ያለው አመራር ገቢ የመሰብሰብ ስራውን የራሱ ተግባር አድርጎ መስራት እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል። በተጨማሪም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሥራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ማድረግና ገበያውን መግራት እንደሚያስፈልግ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። በክልሉ በከተማም ሆነ በገጠር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በየዘርፉ ቅንጅታዊ ሥራንና ትብብርን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራም አስረድተዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አብዱ ሁሴን በበኩላቸው እንደገለጹት፤ አሁን እየተወሰደ ያለው የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራትን ለማሻሻል እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ የመልማት እምቅ አቅም ላለው የአማራ ክልል መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በየደረጃው ያለው አመራር በልዩ ክትትል ለተግባራዊነቱ መትጋት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አሕመዲን መሐመድ፤ ክልሉን ከችግር ለማውጣት ምርታማነትንና ገቢ የመሰብሰብ አቅምን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት ይገባል ብለዋል። በከተሞች ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተጀመሩ ሁለንተናዊ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ህገ ወጥነትን በመከላከል በኩል አመራር አባላት ግንባር ቀደም ሆነው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራር አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በአለርት ሆስፒታል የሕክምና መሳሪያዎች የሚታደሱበት ማዕከል ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ
Aug 5, 2024 94
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2016(ኢዜአ)፦ በአለርት ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና መሳሪያዎች የሚታደሱበት ማዕከል ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ። የመሰረት ድንጋዩን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባና በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጁንግ ካንግ አስቀምጠዋል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ጊዜ፤ እንደ አገር ያረጁ የሕክምና ግብዓቶችን መልሶ በመጠቀም ረገድ ክፍተቶች መኖራቸውን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ የሕክምና መሣሪያዎች ታድሰው ዳግም አገልግሎት መስጠት እየቻሉ ለብክነት ይዳረጉ እንደነበር አስታውሰው ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ማዕከል ያረጁ የሕክምና መሳሪያዎችን አያያዝና አጠቃቀምን የሚያሻሽል መሆኑን ገልጸዋል። ግንባታው በኮሪያው ሪፐብሊክ ዓለም አቀፍ የጤና እንክብካቤ ፋውንዴሽን (ኮፊ) በተደረገ የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄድ መሆኑን አመላክተው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተናግረዋል። ማዕከሉ ከኢትዮጵያ ባለፈ ለጎረቤት አገራት ጭምር አገልግሎት ጭምር አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ እንደሚገነባ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጁንግ ካንግ በበኩላቸው፤ ኮሪያ ሪፐብሊክና ኢትዮጵያ የጋራ ተጠቃሚነት ላይ መሰረት ያደረገ ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው አገራት ናቸው ብለዋል። ሁለቱ አገራት በተለያዩ የልማት መስኮች ላይ በትብብር እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል። ዛሬ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት ማዕከል በኢትዮጵያ የሕክምና መሳሪያዎችን በማደስና ወደ ሥራ በማስገባት የአገሪቱን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
ፖለቲካ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀመረ
Aug 5, 2024 123
ድሬዳዋ፤ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፡-የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ ዙር 3ኛ የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀመረ። በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረው እና ለሁለት ቀናት የሚቆየው 8ኛ መደበኛ ጉባዔው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ የሚመክር መሆኑን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ከሪማ ዓሊ ተናግረዋል። ምክር ቤቱ በጉባዔው የአስፈፃሚውን እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና በተያዘው በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሏል። በተጨማሪም የምክር ቤት ፅህፈት ቤት እና ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች፣ የዋናው ኦዲተር እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የስራ አፈፃፀሞች ላይ ተወያይቶ የሚያፀድቅ መሆኑን የጉባዔው አጀንዳ ያመለክታል። ከዚህ ባሻገር ምክር ቤቱ የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚ እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋም እና ተግባርና ኃላፊነታቸውን ለመወሰን በወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ጉባዔው የዘንድሮ በጀት ዓመት የበጀት ረቂቅ በማፅድቅ እና የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ጉባዔው የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የአስፈፃሚውን እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለጉባዔው እያቀረቡ ይገኛል። በ2000 ዓ.ም የተመሠረተው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 189 አባላት እንዳሉት ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል ሲያካሂድ የቆየውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ዛሬ አጠናቀቀ
Aug 4, 2024 184
ጋምቤላ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል ሲያካሂድ የቆየውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ዛሬ አጠናቀቀ። ተሳታፊዎች በቆይታቸው ለሀገር ይበጃሉ ያሏቸውን አጀንዳዎች በማሰበሳብ በመረጧቸው ኮሚቴዎች አማካኝነት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በአደራ አስረክበዋል ። የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንዳሉት በክልሉ ካለፈው ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰበሳብ ሂደት ዛሬ በስኬት ተጠናቋል። በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መፃኢ እድል ይበጃሉ ያሏቸውን ሃሳቦች በነፃነት በማዋጣት ረገድ መልካም ተሳትፎ የታየበት ነበር ብለዋል። ተሳታፊዎች ለህዝብና ለሀገር ይጠቅማሉ ያሏቸውን አጀንዳዎች በመለየትና በማሰባሰብ ረገድ ላሳዩት የነቃ ተሳትፎም ኮሚሽኑ ከፍተኛ ምስጋና እንዳለው ገልጸዋል። እንዲሁም በክልሉ ለአንድ ሳምንት ያህል ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ያለምንም ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ተባባሪ አካላት ሁሉ ኮሚሽኑ የላቀ ምስጋና እንዳለው ኮሚሽነር መላኩ ተናግረዋል። በቀጣይም ኢትዮጵያ ያሉባትን ችግሮች በውይይት የምትፈታ ሀገር የሚለው ስም እንዲኖራት ለሀገር ዘላቂ ሰላም የጀመሩትን ፋና ወጊ ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽነር መላኩ ጠይቀዋል።
አዲስ የሚወጡና የሚሻሻሉ አዋጆች በልዩ ጥንቃቄ ታይተውና ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው የሚጸድቁ ናቸው- የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ
Aug 4, 2024 245
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦ አዲስ የሚወጡና የሚሻሻሉ አዋጆች በልዩ ጥንቃቄ ታይተውና ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው የሚጸድቁ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። በምክር ቤቱ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱ፤ በምክር ቤቱ የህግ ማርቀቅና ማጽደቅ ሂደት ሰፊና ጥልቅ የአሰራር ሂደቶችን የተከተለ መሆኑን ገልጸዋል። ለምክር ቤቱ በሚቀርቡ ረቂቅ ህጎች ዙሪያ የመንግስት ተጠሪ በኩል ለምክር ቤት አባላት ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ የሚሰጥ ስለመሆኑ አንስተዋል። በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ በቋሚ ኮሚቴው ረቂቅ ህጎች በዝርዝር እንዲፈትሹ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል። ለዝርዝር እይታ የተመራላቸው ቋሚ ኮሚቴዎችም ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በረቂቅ ህጉ ላይ ጥልቅ ውይይት የሚያደርጉበት አሰራር መሆኑን ሰብሳቢዋ ተናግረዋል። ከህገ-መንግስቱና ከዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ጋር እንዳይጣረሱ በልዩ ልዩ መንገዶች የማጣራት ስራ የሚከናወን መሆኑንም አስረድተዋል። በመሆኑም እነዚህን አሰራሮች በተከተለ መልኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለምክር ቤቱ ከቀረቡ 52 አዋጆች መካከል 42ቱ መጽደቃቸውን ጠቁመዋል። ለዚህም የባለድርሻ አካላትና በረቂቅ አዋጁ ላይ ይመለከተኛል የሚሉ ግለሰቦች በነጻነት እንዲሳተፉ የህዝብ ተሳትፎ መድረኮች እንደሚመቻቹ ነው ያብራሩት። በምክር ቤቱ አዲስ የሚወጡም ሆኑ የሚሻሻሉ አዋጆች ሀገርና ህዝብን የሚጠቅሙና ለረጅም ዓመታት የሚያገለግሉ በመሆናቸው በልዩ ጥንቃቄ ታይቶ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው የሚጸድቁ መሆኑን ገልጸዋል። ምክር ቤቱ በቀጣይም በሚያወጣቸው ህጎች ተፈጻሚነት ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ የመፈተሽ ስራ የሚሰራ ክፍል እንደሚያደራጅ ተናግረዋል። በምክር ቤቱ የሚወጡ ህጎች የታለመላቸውን ዓላማ እንዲመቱ የእያንዳንዱ ዜጋ ትብብርና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በምክክር መድረኩ የተፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ ተጠቅመን በመግባባት ለዘላቂ ሠላም የድርሻችንን እንወጣለን
Aug 3, 2024 203
ጋምቤላ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፡- በምክክር መድረኩ የተፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በመግባባት ለአገራዊ ዘላቂ ሠላም የድርሻቸውን እንደሚወጡ በጋምቤላ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል እያካሄደ ያለው አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደቀጠለ ነው። በምክክሩ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ ከምንም በላይ የህዝብና የአገርን ዘላቂ ሠላምና ጥቅም በሚያረጋገጡ ጉዳዮች ሃሳብ በማዋጣት ድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል። ከተሳታፊዎች መካከል የኢዜማ ተወካይ ኮማንደር ጋድቤል ቦል እንዳሉት፤ በምክክሩ ህዝብና አገርን ይጠቅማሉ ያሏቸውን ሀሳብ አዋጥተዋል። ''ከህዝብና ከአገር የሚበልጥ ነገር የለም'' ያሉት ኮማንደር ጋድቤል፣ ሁላችንም በመግባባት የአገሪቷን ሠላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። የህዝብና የአገርን ሠላም ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ያሉት ደግሞ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲ ንቅናቄ/ ጋብዴን/ ተወካይ አቶ ኡቦንግ ኡሞድ ናቸው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየተካሄደ ያለው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ኢትዮጵያ ከችግር የምትወጣበት መንገድ መሆኑን እንደሚያምኑ ተናግረዋል። እንደ ፖለቲካ ፓርቲም የህዝብና የአገር ሠላምና ብሔራዊ ጥቅም በሚነኩ ጉዳዮች አንድ ዓይነት አቋም መያዝ ይጠበቅብናል ብለዋል አቶ ኡቦንግ። በፖለቲካው ዓለም በምርጫ አሸንፎ መምራት የምትችለው ህዝብና አገር ሠላም ሲሆን ብቻ ነው ያሉት ተወካዩ፤ ሁላችንም ለአገር ዘላቂ ሠላም ቅድሚያ ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ሌላው የመድረኩ ተሳታፊ የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ/ጋህነን/ተወካይ አቶ ኡኮች ኡሞድ፤ የአገርን ችግር ለመፍታት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በመግባባት ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን ልንሰራ ይገባናል ብለዋል። ''የማያግባቡ ሃሳቦችን በኃይል አማራጭ ለመፍታት የሚደረግ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው'' ያሉት ተወካዩ፣ በምክክር መድረኩ የተፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀምና መግባባት ላይ መሥራት ይጠበቅብናል ሲሉ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተርክዬ አቻቸው ጋር ተወያዩ
Aug 3, 2024 247
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ጋር ተወያዩ። ሁለቱ የሥራ ኃላፊዎች በሶማሊያ እና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታና በሌሎች የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግም ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በምክክር ሀገራዊ አንድነትን እውን ለማድረግ የተጀመረው ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን ዜጎች ንቁ ተሳትፏቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል- ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ
Aug 3, 2024 202
ድሬዳዋ ሐምሌ 27/2016 (ኢዜአ)፡- በአካታችና ነጻ ህዝባዊ ምክክር ሀገራዊ አንድነትን እውን ለማድረግ የተጀመረው ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን ዜጎች ንቁ ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽነር ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ ተናገሩ። ኮሚሽኑ በድሬዳዋ አስተዳደር እና በሐረሪ ክልል ከነሐሴ ስድስት ጀምሮ አጀንዳ ለማሰባሰብ ምክክር ያካሂዳል። በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በድሬዳዋ በሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ውይይት ላይ ለሚሳተፉትና ድሬዳዋ ከሚገኙት የሲቪል ማህበራት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌቱ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ፤ኮሚሽኑ በየክልሉና በከተማ አስተዳደሮች በህዝብ ከተመረጡ ወኪሎች ጋር ለአገራዊው ምክክር የሚጠቅሙ አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ እያካሄደ ነው። ባለፈው ሳምንት ከቤኒሻንጉል እና ከጋምቤላ ክልሎች ከተመረጡ የህዝብ ወኪሎች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማህበራት እና ከሚመለከታቸው ወኪሎች ጋር በመምከር አጀንዳ አሰባስቦ አጠናቋል ብለዋል። ከነሐሴ ስድስት ጀምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር እና በሐረሪ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ የውይይት መድረኮች እንደሚያካሂድም አስረድተዋል። ነጻ፣ አካታች እና ገለልተኛ በሆነው መንገድ ከሚካሄደው ውይይት አገራዊ መግባባት የሚፈጥሩ አጀንዳዎች እንደሚሰበሰቡም ነው ዶክተር ተገኘወርቅ የገለፁት። ተቻችለን፣ ተረጋግተንና ተደማምጠን በመወያየት ብሎም ሰጥተን በመቀበል ነው ወደፊት መዝለቅ የምንችለው ያሉት ኮሚሽነሩ፣ በሰላም፣ በመመካከርና በመተባበር ከተሰራ አገርን የሚያፀኑ ውጤቶችን ማግኘት እንችላለን ብለዋል። እንደ ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌቱ (ዶ/ር) ገለፃ ድህነትና በሰላም እጦት መድቀቅ እንዲያከትም ሁሉም በሀገራዊ ምክክሩ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አለበት። የሲቪል ማህበራት ባላቸው ህዝባዊ ኃላፊነት እና ልምድ በአጀንዳ ማሰባሰቡ ላይ የነቃ ተሳትፏቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል። የኮሚሽኑ የአጀንዳ እና የምክክር አስተባባሪ አቶ ተመስገን አብዲሳ ከነሐሴ ስድስት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት አስቀድመው ከድሬዳዋ አስተዳደር ከከተማ እና ገጠር ወረዳዎች በህዝብ ከተመረጡ ወኪሎች ጋር አጀንዳ የማሰባሰብ ውይይት ይካሄዳል ብለዋል። በውይይቱም የሁሉም ህብረተሰብ ወኪሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪል ማህበራት፣ የመንግስት አካላት እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንደሚሳተፉ አስረድተዋል። በአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ ላይ የሚሳተፉት አካላት በነፃነት፣ በገለልተኝነት እና በእኩልነት ለሀገራዊ ምክክሩ የሚጠቅሙ አጀንዳዎችን ያቀርባሉ ብለዋል።
በክልሉ ሠላም በዘላቂነት ተጠብቆ ልማቱ እንዲፋጠን ሚናቸውን እንደሚወጡ የምክር ቤት አባላት ገለጹ
Aug 3, 2024 202
ባህር ዳር ፤ሐምሌ 27/ 2016 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ሠላምን በዘላቂነት በማስጠበቅ ልማቱ እንዲፋጠን የክትትልና የድጋፍ ተግባራቸውን እንደሚያጠናክሩ የክልሉ የምክር ቤት አባላት ገለጹ። ሠላም ለዘላቂ ልማትና እድገት ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም የምክር ቤቱ አባላት አመልክተዋል። በምክር ቤቱ ከሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ምርጫ ክልል የተወከሉት አቶ ጋሻው አስማሜ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ሠላምን ለማስፈን ህዝቡ አካባቢውን በመጠበቅ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ተከታታይ ውይይት እየተደረገ ነው። ችግር ውስጥ የገቡ ወገኖች ተመልሰው ከመንግስት ጋር ተቀራርበው በመወያየት ለችግሩ እልባት ሊሰጡ እንደሚገባ አመልክተዋል። ተመራጭ የምክር ቤት አባላትም ህዝብን በማወያየት የክልሉ ሰላም እንዲፀናና የታቀዱ የልማት ስራዎች እንዲሳኩ ለሠላም ዋጋ መክፈል አለብን ብለዋል። የክልሉ ሠላም በዘላቂነት ተጠብቆ ልማቱ እንዲፋጠን እኔም ለመረጠኝ ህዝብ የሰላምን ዋጋ አጥብቄ በማስረዳት የድርሻዬን ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ብለዋል። ከሰሜን ሸዋ ዞን ግሼራቤል ምርጫ ክልል በምክር ቤቱ የተወከሉት አቶ አበራ ፈንታው በበኩላቸው፤ ያለሠላም መንቀሳቀስም ሆነ ልማትን ማፋጠን እንደማይቻል ተናግረዋል። ሠላም ሰፍኖ ልማቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የምክር ቤት አባላት ሚና ከፍ ያለ እንደሆነ ጠቅሰው፤ እሳቸውም በተመረጡበት አካባቢ ሰላም እንዲመጣ የክትትልና ድጋፍ ተግባራቸውን በማጠናከር ሚናቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። ሠላም ለዘላቂ ልማትና እድገት ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ ሁሉም ህብረተሰብ ለዘላቂ ሠላም እውን መሆን ሊሰራ እንደሚገባ አመለክተዋል። ማንኛውም አካል ችግሩን በውይይት ሊፈታ እንደሚገባ ጠቅሰው ፤ይህ እንዲሳካም ድጋፋቸውን ለማጠናከር ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በክልሉ ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን " ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል" ያሉት ደግሞ ከደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ ምርጫ ክልል የተወከሉት አቶ አሰፋ ይመር ናቸው። ከመረጠን ህዝብ ጋር በጋራ ሃሳቦች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ሁላችንም ለሠላም ትኩረት ሰጥተን በመስራት ልማቱን ልናፋጥን ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። ሠላም ተጠብቆ ልማቱ እንዲፋጠን የክትትልና ድጋፍ ሥራቸውን አጠናክረው ሚናቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።። በመጠፋፋት የምናገኘው ትርፍ አለመኖሩን በመገንዘብ በክልሉ ዘላቂ ሠላም እውን እንዲሆን ሁላችንም ተቀራርበን ችግሮችን በውይይት ልንፈታ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። ችግር ውስጥ የገቡ ወገኖች የሠላም ካውንስል ያቀረባውን የሠላም አማራጭ በመቀበል ለተግባራዊነቱ መዘጋጀት እንዳለባቸው የምክር ቤቱ አባላት አመልክተዋል። የአማራ ክልል ምክር ቤት ከሐምሌ 22 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ሲያካሄድ የቆየው 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ ማጠናቀቁን በወቅቱ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
Aug 3, 2024 275
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ጠዋት የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ ብለዋል። ውይይታችን ተጠናክረው በቀጠሉት የሁለቱ ሀገሮቻችን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ያተኮረ ነበር ሲሉም አክለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

ማህበራዊ
ቅን ኢትዮጵያ ማኅበር ዜጎችን ለበጎ ዓላማ እንዲሰለፉ የጀመረው ጥረት ሊጠናከር ይገባል
Aug 5, 2024 112
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2016(ኢዜአ)፦ቅን ኢትዮጵያ ማኅበር ዜጎችን ለበጎ ዓላማ እንዲሰለፉ የጀመረው ጥረት ሊጠናከር ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ቅን ኢትዮጵያ ማኀበር በቅንነት፣ በጎ አሳቢነትና ሠላም ግንባታ ላይ ለተማሪዎች፣ ለወላጅ ተወካዮችና መምህራን ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ዛሬ ተጠናቋል። ሥልጠናው ለአንድ ሳምንት የተሰጠ ሲሆን "ተማሪ ለሀገር ሠላም" በሚል መሪ ኃሳብ ተካሂዷል። የሥልጠናው ተሳታፊዎችም በአዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሳቢያ፣ የአንድነት ፓርክ፣ ወዳጅነት አደባባይ፣ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ሥራዎችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። የሥልጠናው ማጠቃለያ መርኃ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ቅንነት፣ መልካምነትና መተሳሰብ እንደ አገር አብሮ ለመቆም፤ ለዘላቂ ሠላም መረጋገጥ ቁልፍ ሚና አለው። ሠላም ደግሞ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ መሰረት ነው ያሉት ከንቲባዋ ሁላችንም ተባብረን መሥራት አለብን ሲሉም ተናግረዋል። ቅን ኢትዮጵያ ማኅበርም የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎችን በማሰባሰብ ለበጎ ዓላማ እንዲሰለፉ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው ቀጣይነትም ሊኖረው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። የቅን ኢትዮጵያ ማህበር የቦርድ ሊቀ መንበር መሰረት ስዩም በበኩላቸው የሥልጠናው ተካፋዮች አገር ከእናንተ ብዙ ትጠብቃለች፤ የቀሰማችሁትን እውቀት ወደ መጣችሁበት አከባቢ በማስፋፋት ቅን ማኅበረሰብ የመፍጠር ጥረቱን ማጠናከር አለባችሁ ብለዋል። የቅን ኢትዮጵያ ማኅበር መሥራች አባል መሰለ ሃይሌ በኢትዮጵያ ቅንነት እንዲዳብር ማህበሩ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል። ከረጅም ጊዜ አኳያ የቅንነት ባህል እንዲሁም የሠላም እሴቶች መገንባት ላይ የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት የግንዛቤ ለውጥ እንዲመጣ እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። ለአንድ ሳምንት ያህል "ተማሪ ለሀገር ሠላም" በሚል መሪ ኃሳብ የተሰጠው ሥልጠናም የዚሁ አካል ነው ያሉት አቶ መሰለ ይሄው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በሥልጠና መርሃ ግብሩ ላይ ወላጆችን ወክለው ከተሳተፉ መካከል ከኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሶኮሩ ወረዳ የመጡት ሙኢዲን አባቦራ አባሱራ፤ ሥልጠናው ለአገሬ በተነሳሽነትና ከልብ በመነጨ ስሜት በትጋት መስራት እንዳለብኝ ግንዛቤ የጨበጥኩበት ነው ብለዋል። ከአማራ ክልል ባህዳር ከተማ ጊዮን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተወከለችው ተማሪ ትንሳኤ እስጢፋኖስ በበኩሏ በሥልጠና ቆይታዬ አንድነታችንን የበለጠ የሚያጠናክሩ ኃሳቦችን ገብይቻለሁ ብላለች። ከአፋር ክልል ሎጊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጣው ተማሪ ዑስማን መሀመድ በሰጠው አስተያየት በኢትዮጵያን በተሻለ መልኩ ለማገልገል ዝግጁ ነኝ፣ በሠላም በኩልም የሚጠበቅብኝን ድርሻ ላይ በቂ ግንዛቤ ወስጃለሁ ብሏል።
በአለርት ሆስፒታል የሕክምና መሳሪያዎች የሚታደሱበት ማዕከል ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ
Aug 5, 2024 94
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2016(ኢዜአ)፦ በአለርት ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና መሳሪያዎች የሚታደሱበት ማዕከል ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ። የመሰረት ድንጋዩን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባና በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጁንግ ካንግ አስቀምጠዋል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ጊዜ፤ እንደ አገር ያረጁ የሕክምና ግብዓቶችን መልሶ በመጠቀም ረገድ ክፍተቶች መኖራቸውን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ የሕክምና መሣሪያዎች ታድሰው ዳግም አገልግሎት መስጠት እየቻሉ ለብክነት ይዳረጉ እንደነበር አስታውሰው ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ማዕከል ያረጁ የሕክምና መሳሪያዎችን አያያዝና አጠቃቀምን የሚያሻሽል መሆኑን ገልጸዋል። ግንባታው በኮሪያው ሪፐብሊክ ዓለም አቀፍ የጤና እንክብካቤ ፋውንዴሽን (ኮፊ) በተደረገ የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄድ መሆኑን አመላክተው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተናግረዋል። ማዕከሉ ከኢትዮጵያ ባለፈ ለጎረቤት አገራት ጭምር አገልግሎት ጭምር አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ እንደሚገነባ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጁንግ ካንግ በበኩላቸው፤ ኮሪያ ሪፐብሊክና ኢትዮጵያ የጋራ ተጠቃሚነት ላይ መሰረት ያደረገ ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው አገራት ናቸው ብለዋል። ሁለቱ አገራት በተለያዩ የልማት መስኮች ላይ በትብብር እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል። ዛሬ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት ማዕከል በኢትዮጵያ የሕክምና መሳሪያዎችን በማደስና ወደ ሥራ በማስገባት የአገሪቱን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
የሀዲያ ብሔረሰብ ባህላዊ የዳኝነትና የግጭት አፈታት ሥርዓት ሳይበረዝ ለትውልድ እንዲሸጋገር እየተሰራ ነው
Aug 5, 2024 117
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፡- የሀዲያ ብሔረሰብ ባህላዊ የዳኝነትና የግጭት አፈታት ሥርዓት ሳይበረዝ ለትውልድ እንዲሸጋገር ለማስቻል በጥናት የተደገፉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የሀዲያ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ። በዞኑ የሌሞን ወረዳ ማህበረሰብን የሚወክሉ የበላይ ጠባቂ የሀገር ሽማግሌዎችን የመሰየም መርሃ ግብር ዛሬ በወረዳው ኃይሴ ቀበሌ ተካሂዷል። የመምሪያው ሃላፊ አቶ ታምሬ ኤርሚያስ በእዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ በሀዲያ የአካባቢውን ሰላም የሚያስጠብቁና የማህበረሰቡን የእርስ በርስ ትስስር ለማጎልበት የሚጠቅሙ በርካታ ባህላዊ እሴቶች አሉ። ህብረተሰቡ ግጭቶችን የሚያስወግድበትና ሰላም የሚያወርድበት ባህላዊ የዳኝነትና ግጭት መፍቻ ሥርአት ወይም የ"ጢጉላ ባህላዊ ግጭት አፈታት" ከባህላዊ እሴቶቹ አንዱ መሆኑንም ጠቁመዋል። ሥርአቱ ግጭትን በሰለጠነ መንገድ በውይይት በመፍታት ሰላምን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸው፣ ባህላዊ እሴቱ ሳይበረዝ ለትውልድ እንዲተላለፍና ተሰንዶ እንዲቀመጥ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የጥናት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስረድተዋል። ባህላዊ የዳኝነት ስርዓቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ ታምሬ፣ ስርዓቱን የሚመራው ሰውም በየጊዜው በህዝብ እየተመረጠ የስልጣን ሽግግር እንደሚደረግ ገልጸዋል። አቶ ታምሬ እንዳሉት ባህላዊ የዳኝነት ስርዓቱ ለዴሞክራሲ መጎልበት ጭምር ጉልህ ሚና አለው። የሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዳኛ ጥላሁን ዴታሞ በበኩላቸው እንዳሉት፣ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት በዘመናዊ ፍርድ ቤቶች ያለውን የሥራ ጫና ከማቃለል አንጻር አስተዋጾው የጎላ ነው። ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቱ እሴቱን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላፍ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ባህል ሽማግሌ አቶ ታደሰ ኮራ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውና ዘመናትን ያስቆጠሩ በርካታ ባህላዊ ዕሴቶች እንዳሉ ገልጸዋል። ግጭት በሰላማዊ መንገድ በውይይት የሚፈታባቸው ዕሴቶች ለሀገራዊ አንድነት እንደምሶሶ ናቸው ያሉት አቶ ታደሰ፣ ህብረተሰቡ ለዘመናት የተጠቀመባቸውን እነዚህን እሴቶች መጠበቅ ይገባናል ብለዋል። የአብሮነት እሴቶቻችንን በዘመናዊነት ሳይበረዙ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በሚሰሩ ሥራዎች ውስጥ የአገር ባህል ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል። የሀገር ሽማግሌዎች ተቀራርበው በመስራት የሰላም እጦት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን መፍታት እንደሚችሉ የጠቆሙት አቶ ታደሰ፣ እሳቸውም የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። "ሰላምን ማስጠበቅ የሚጀመረው ከአካባቢ ነው።" ያሉት ደግሞ በሌሞ ማህበረሰብ ዘንድ በሰብሳቢ ዳኝነት የተመረጡት ዳኛ ብርሃኑ ጡሞሮ ናቸው። የሀገር ሽማግሌዎች ጽንፍ ከመያዝና ከእኔነት አመለካከት ወጥተን ፍትሃዊ ፍርድ በመስጠት ለህዝብ ሰላምና አብሮነት መጠናክር ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል። የሀዲያን አንድነት ከማስጠበቅ ባለፈ በአጎራባች አካባቢ ካሉ ህዝቦች ጋር አብሮነትን በማጠናከር ኃላፊነታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች እና የባህል ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል።
ክልሉ የኮሌራና የወባ በሽታዎችን ለመከላከል ህብረተሰቡን ያሳተፈ የመከላከል ተግባር እየተከናወነ ነው
Aug 5, 2024 106
ባህር ዳር፣ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የኮሌራና የወባ በሽታዎችን ህብረተሰቡን ያሳተፈ የመከላከል ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ። ቢሮው ያለፈው ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ የትውውቅ መድረክ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። የቢሮ ኃላፊው አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ እንደገለጹት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተደረገው የተቀናጀ ጥረት በዘርፉ አበረታች ስራ ማከናወን ተችሏል። በተለይም የኮሌራና የወባ በሽታዎችን ለመከላከል መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ በማዳረስ ለመቆጣጠር ጥረት መደረጉን አውስተዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም የኮሌራ በሽታ ስርጭትን ለመግታት ህብረተሰቡ የግልና የአካባቢውን ንጽህና በመጠበቅ ራሱን ከበሽታው እንዲከላከል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። እንዲሁም ለወባ በሽታ ተጋላጭ በሆኑ 22 ወረዳዎች ላይም የጸረ ወባ ኬሚካል ርጭት እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። አሁንም ተጨማሪ ርጭት ለማከናወን ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተው፤ ህብረተሰቡ ለወባ በሽታ አጋላጭ የሆኑ ስፍራዎችን ማፅዳት እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ገበያው አሻግሬ በበኩላቸው፤ በዞኑ የወባ በሽታን ለመከላከል አንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን የአልጋ አጎበር በማሰራጨትና ህብረተሰቡን በማስተባበር የመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም በዘጠኝ ወረዳዎች የጸረ ወባ ኬሚካል ርጭትና ህብረተሰቡን ከበሽታው መከላከል በሚቻልበት አግባብ ግንዛቤን የማሰራጨት ስራ እየተከናወኑ መሆኑንም አስረድተዋል። በመድረኩ ላይም የቢሮው፣ የዞንና የወረዳ የዘርፉ አመራሮች እንዲሁም አጋርና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
ኢኮኖሚ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር በተለያዩ አማራጮች ለመፍታት እየተሰራ ነው
Aug 5, 2024 111
ሀዋሳ ፤ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፦የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር በተለያዩ አማራጮች ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለ1 ሺህ 108 የመንግሥት ሠራተኞች ለጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚሆን ቦታ ዛሬ በእጣ አስተላልፏል። በቦታ ርክክቡ ላይ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ እንደገለጹት የቤት ጉዳይ ይበልጥ በከተሞች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል። ችግሩን ለማቃለል አስተዳደሩ ለስራው አመቺ የሆኑ መመሪያዎችን በማውጣት ለተግባራዊነቱ በሙሉ ቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ ነው ሲሉም ጠቁመዋል። በተለይ የመንግሥት ሠራተኛውን በቤት ልማት አማራጮች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ በዛሬው እለት ለ1ሺህ 108 የመንግሥት ሠራተኞች የቤት መስሪያ ቦታ ተላልፏል ብለዋል። መሠረተ ልማት የተሟላለት 51 ሺህ 950 ካሬ ሜትር ቦታ የተላለፈው በመኖሪያ ቤት ሕብረት ሥራ የተደራጁ 35 ማህበራት ለግንባታው ሂደት አስፈላጊውን ገንዘብ በመቆጠባቸው መሆኑንም ገልጸዋል። በቀጣይም ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ በአቅሙ ልክ ሊሳተፍበት የሚችልበትን የኮንዶሚንየም ቤት አመራጭ አስተዳደሩ በማዘጋጀት በቅርቡ ምዝገባ እንደሚጀምርም አመልክተዋል። የሲዳማ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ በበኩላቸው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በክልሉ በከተሞች ለሰው ተኮር ልማት ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ የህብረተሰቡ ችግር እየተቃለለ መጥቷል። በክልሉ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው አንዱ የቤት መስሪያ ቦታ ማመቻቸት መሆኑን ጠቅሰው፣ ቦታውን ያገኙት እድለኞች ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ በማካሄድ ለከተማዋ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ቢሮውም የዲዛይን ክትትልና ቁጥጥር ከማድረግ ባለፈ በግንባታ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ካገኙት መካከል አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ይሁንሰው አብርሃም ቦታ ለማግኘት በማህበር ተደራጅተው በየወሩ ሲቆጥቡ መቆየታቸውን ገልጸዋል። አሁን ላይ በከተሞች ያለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ እየጨመረ መምጣቱ በተለይ ለመንግስት ሠራተኛውና ዝግቀተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ከአቅም በላይ መሆኑን ተናግረዋል። ከተማ አስተዳደሩ ይህን ችግር አይቶ የቤት መስሪያ ቦታ በመስጠቱ አመስግነው በቅርቡ የቤት ባለቤት የመሆን ተስፋ ሰንቂያለሁ ሲሉ ገልጸዋል። የጤና በለሙያ አቶ ባርናባስ ተስፋዬ በበኩላቸው እሳቸውን ጨምሮ የቤት መስሪያ ቦታ የተሰጣቸው የመንግስት ሠራተኞች ለረጅም ጊዜ በኪራይ ቤት ሲኖሩ እንደነበር አስታውሰዋል። የተሰጣቸው የቤት መስሪያ ቦታ ከቤት ኪራይ ወጪ በዘላቂነት ለመገላገል ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል። ሠራተኞቹ ከተማ አስተዳደሩ አሁን የጀመረው የመኖሪያ ቤት ችግር የመፍታት ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።
በክልሉ በግብይት ወቅት ሕገ ወጥ ተግባር በፈጸሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
Aug 5, 2024 110
አርባ ምንጭ ፤ ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በግብይት ወቅት ሕገ ወጥ ተግባር የፈጸሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ። የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በህገ-ወጥ የንግድ ስርአት ቁጥጥርና ገበያ ማረጋጋት ላይ በተዋረድ ከሚገኙ መዋቅር ሥራ ሃላፊዎች ጋር በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ ውይይት አድርጓል። በዚህ ወቅት የቢሮ ሃላፊው አቶ ገሌቦ ጎልሞ እንደገለጹት፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ተከትለው በግብይት ወቅት ሕገ ወጥ ተግባር የፈጸሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል። በክልሉ አንዳንድ ነጋዴዎች በግብይት ወቅት ህገ ወጥ ተግባር እንደፈጸሙ ጠቁመው፤ በተለይ ምርቶችን የመደበቅና የማሸሽ ህገ ወጥ ተግባራት መኖራቸውን በተደረገ ምልከታ መረጋገጡን ተናግረዋል። በክልሉ በየደረጃው የአስተዳደር፣ የፀጥታ፣ የፍትህና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያካተተ የህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ-ሃይል መኖሩንም ጠቁመዋል። ግብረ-ሃይሉ ባለፉት አምስት ቀናት በ304 የንግድ ድርጅቶች ላይ ባደረገው የክትትልና ቁጥጥር ሥራ በንግድ ልውውጥ ወቅት ሕገወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በተገኙ 44 የንግድ ድርጅቶች ላይ ማሸግን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች መወሰዱን አብራርተዋል። የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ከህገ ወጥ ድርጊት በመቆጠብ በተጠያቂነት መንፈስ ሥራቸውን ማከናወን ይገባቸዋል ሲሉም አሳስበዋል።
በክልሉ ምርታማነትን መጨመርና ገቢ የመሰብሰብ አቅምን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ
Aug 5, 2024 106
ባህር ዳር ፤ ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የኑሮ ውድነትን ለመከላከል ምርታማነትና ገቢን ማሳደግ ላይ አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ። የክልሉ የከተማ ልማት ክላስተር በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ፖሊሲ የትኩረት ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረክ በባህር ዳር ከተማ አካሂዷል። በዚሁ ወቅት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እንደገለጹት፤ በአዲሱ ዓመት አመራሩ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ በየዘርፉ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ሥራዎች ላይ በትኩረት ይሰራል። እንዲሁም የክልሉን የገቢ አቅም ማሳደግ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ገቢ የመሰብሰብ ሥራ ለገቢዎች ተቋም ብቻ የሚተው እንዳልሆነ ተናግረዋል። ለዚህም ከላይ እስከታች ያለው አመራር ገቢ የመሰብሰብ ስራውን የራሱ ተግባር አድርጎ መስራት እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል። በተጨማሪም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሥራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ማድረግና ገበያውን መግራት እንደሚያስፈልግ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። በክልሉ በከተማም ሆነ በገጠር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በየዘርፉ ቅንጅታዊ ሥራንና ትብብርን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራም አስረድተዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አብዱ ሁሴን በበኩላቸው እንደገለጹት፤ አሁን እየተወሰደ ያለው የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራትን ለማሻሻል እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ የመልማት እምቅ አቅም ላለው የአማራ ክልል መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በየደረጃው ያለው አመራር በልዩ ክትትል ለተግባራዊነቱ መትጋት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አሕመዲን መሐመድ፤ ክልሉን ከችግር ለማውጣት ምርታማነትንና ገቢ የመሰብሰብ አቅምን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት ይገባል ብለዋል። በከተሞች ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተጀመሩ ሁለንተናዊ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ህገ ወጥነትን በመከላከል በኩል አመራር አባላት ግንባር ቀደም ሆነው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራር አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በጌዴኦ ዞን የተጀመሩ የልማት ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው ተገለጸ
Aug 5, 2024 96
ዲላ ፤ሐምሌ 29/2016 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በተለያዩ ዘርፎች የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለጸ። የዞኑን ህዝብ የወከሉ የምክር ቤት አባላት በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳና በዲላ ከተማ በየዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። ጉብኝቱም በዋናነት በግብርና ዘርፍ የቡና፣ የእንሰትና የፍራፍሬ ልማት፣ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲሁም የኮሪደር ልማት ስራዎችን ያካተተ ነው። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ በወቅቱ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የቡና፣ የእንሰትና የፍራፍሬ ክላስተር ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተስፋ ሰጭና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው። በተለይ በጥቂት አርሶ አደሮች ማሳ የተጀመረው ኩታ ገጠም የቡና ልማትን ማስፋት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ ከተማ ልምድ በመውሰድ በዲላ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ወደ ስራ መገባቱ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህ ተግባር መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል። የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት አባል አቶ ንጉሴ አሰፋ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ በዞኑ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙና ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው። በተለይ የዲላ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ግንባታ ለማጠናቀቅና ለአገልግሎት ለማብቃት የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጥረቱን እንደሚያግዙም አረጋግጠዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፀሃይ ወራሳ በበኩላቸው፤ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪና የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመልሱ መሆናቸውን ገልጸዋል። የልማት ስራዎቹ ጅምራቸው መልካም መሆኑን አንስተው፤ የህዝቡን የልማት ፍላጎት እስኪመለስ ድረስ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ በበኩላቸው፤ በዞኑ በተለይ በምግብ ሰብል እራስን በመቻል ከተረጅነት ለመላቀቅ የኩታ ገጠም የግብርና ልማት ስራዎች ላይ በማተኮር በውስን ስፍራ ከፍተኛ የምርት መጠን እየተገኘ ነው ብለዋል። በሞዴል አርሶ አደሮች ማሳ ቡና በሄክታር 19 ኩንታል ማግኘት መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል። ዋና አስተዳዳሪው እንደተናገሩት፤ የዞኑ የለውጥ ሂደት ከግብ እንዲደርስ በየደረጃው ያሉ የምክር ቤት አባላት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በክልሉ መገናኛ ብዙሃን ለልማትና ለሰላም ግንባታ ያላቸውን አስተዋጽኦ ከግምት ያስገባ የተቋማቱ ተደራሽነት ይጠናከራል
Aug 4, 2024 170
ሚዛን አማን ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መገናኛ ብዙሃን ለልማትና ለሰላም ግንባታ ያላቸውን አስተዋጽኦ ከግምት ያስገባ የተቋማቱ ተደራሽነት እንደሚጠናከር የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) አስታወቁ። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የደቡብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያን ዛሬ መርቀው ከፍተዋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ መገናኛ ብዙሃን ሕዝብና መንግስትን ድልድይ ሆኖ በማገናኘት ምትክ የለሽ ሚና ስላለው አገልግሎቱን ለማስፋፋት የክልሉ መንግሥት አበክሮ እየሰራ ይገኛል። በተለይ መገናኛ ብዙሃን ለልማትና ለሰላም ግንባታ ያላቸውን አስተዋጽናኦ የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያስጠብቅ በመሆኑ የሚዲያ ተቋማትን ተደራሽነትን የማጠናከር ስራን የክልሉ መንግሥት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በሸካ ዞን የተከፈተው ጣቢያም የዚሁ እንቅስቃሴ አካል መሆኑን አስረድተዋል። የክልሉ ሚዲያ ኔትዎርክ መቋቋሙን ጠቅሰው በክልሉ ውስጥ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንን በቴክኖሎጂ ለማብቃት ጥረት እንደሚደረግም አስታውቀዋል። መገናኛ ብዙሃን ባሉበት አካባቢ ብቻ ሳይገደቡ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ተደራሽነታቸው እንዲጎላ አስፈላጊውን ግብዓት እና የሰው ኃይል በማሟላት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አመልክተዋል። በክልሉ ውስጥ እየሠሩ ያሉ መገናኛ ብዙሃን የቱሪዝም ሀብትን በማስተዋወቅና መልካም እሴቶችን በማጉላት የሕዝቦችን አብሮነት በሚያጠናክር መልኩ እንዲሠሩም አሳስበዋል። የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው መገናኛ ብዙሃን ኅብረተሰቡ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ወደ ኢኮኖሚ መቀየር የሚችልበትን መንገድ ማመላከት ላይ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። መገናኛ ብዙሃኑ የመልካም አስተዳደር እጥረቶችን ተከታትለው በመዘገብ ችግር ፈቺ ተቋም ለመሆን ጥረት ማድረግና የአካባቢውን የመለወጥ ተስፋን ተደራሽ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸውም አመልክተዋል። የማሻ ራዲዮ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ጎዱ ከክልሉ መንግስት በተገኘ የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የስቱዲዮ ግብዓት በሟሟላት በአጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት መጀመር መቻሉን ጠቅሰዋል። ዛሬ የተመረቀው የማሻ ኤፍ ኤም 103 ነጥብ 8 ራዲዮ ጣቢያ አማርኛን ጨምሮ በሸካ ዞን ውስጥ ባሉ የሸክኛ እና መዠንግርኛ ቋንቋዎች መረጃን ለማኅበረሰቡ ተደራሽ እንደሚያደርጉም አመላክተዋል።
ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ተቋማት ንብረት የማስወገድ ስራቸውን በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ብቻ ያካሒዳሉ - ባለስልጣኑ
Aug 3, 2024 334
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ተቋማት ንብረት የማስወገድ ስራቸውን በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ብቻ እንደሚያካሒዱ የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን አስታወቀ። የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወልደአብ ደምሴ፤ ለኢዜአ እንደገለጹት የመንግሥት ግዥና አስተዳደር ሥርዓትን ዘመናዊ ከማድረግ አንፃር አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል። በአሁኑ ወቅትም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በ169 ተቋማት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት በሙከራ ደረጃ እየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የንብረት ማስወገድ ተግባሩ አሁንም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ባለመሆኑ ውጤታማነቱ በቂ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። ለተቋማት የግዥ ስርዓት እንዲያገለግል የለማው (e-GP) የተሰኘው ቴክኖሎጂ ከግዥ ስራው ጎን ለጎን የንብረት ማስወገድ ተግባሩንም ያካተተ በመሆኑ ዘርፉን በማዘመን ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል። በመሆኑም ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ተቋማት ንብረት የሚያስወግዱበት መንገድ በዚሁ ቴክኖሎጂ በተደገፈ አሰራር ብቻ እንደሚሆን አስታውቀዋል። ሌላው ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም የጸደቀው የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ የተቋሙን የአሰራር ስርዓት የሚያዘምንና የሚያቀላጥፍ በመሆኑ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ ይገባል ብለዋል። አዋጁ በዋናነት ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የግዥና ንብረት ማስወገድ አሰራር መተግበር፣ ለሀገር ውስጥ አምራቾችና ምርት ቅድሚያ የሚሰጥ፣ መልሶ በመጠቀም ሒደት ከብክለት የጸዳ አረንጓዴ የማስወገድ ስርዓትን እውን የሚያደርግ እንደሆነም ጠቅሰዋል። በዚህ ሒደት በተለይም የሀገር ውስጥ አምራቾችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን የሚያበረታታ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ለዜጎች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ አበርክቶው የጎላ ነው ብለዋል። የጸደቀው አዋጅ የተቋሙን የአሰራር ስርዓት በማሻሻል በዘርፉ የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንደሚያቃልልም ገልጸዋል። አዋጁን ተከትሎ የሚወጡ የአሰራር መመሪያዎች መዘጋጀታቸውን ገልጸው ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ የተቋሙ አሰራር ሙሉ በሙሉ በአዲሱ አዋጅ ላይ ተመስርቶ የሚከናወን መሆኑን አስታውቀዋል።
የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ለማስጀመር የቅድመ ምዝገባና ማረጋገጫ ሂደት ተጀመረ
Aug 3, 2024 197
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ለማስጀመር የቅድመ ምዝገባና ማረጋገጫ ሂደት መጀመሩን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታወቀ። ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደችውን የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አለማቀፍ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማስቻል ያለመ ምክክር ከአለማቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተካሂዷል። በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የተመራ ልዑክ በካናዳ ሞንትሪያል ከአለማቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጁዋን ካርሎስ ሳላዛር ጋር በመገናኘት ምክክር አድርገዋል። ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ የዳበረ ልምድ ያላትና አለምን በአገልግሎት እያስተሳሰረ ያለ ግዙፍ የአየርመንገድ ባለቤት መሆኗን አስታውሰዋል። አለማቀፉ የአቪዬሽን ድርጅት ከጉዞ ሰነድ የደህንነት ስራዎች ጋር በተያያዘ እያደረገ ላለው ድጋፍ ዋና ዳይሬክተሯ ምስጋና አቅርበዋል። ድርጅቱ በቀጣይም ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ስርዓት በምታደርገው የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ ድጋፎች እንዲያደርግ ወይዘሮ ሰላማዊት ጠይቀዋል። ዋና ዳይሬክተር ጁዋን ካርሎስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ስርዓት ለመግባት ያሳለፈችውን ውሳኔ በማድነቅ በቀጣይ ተቋማቸው የማይቋረጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። ልዑኩ ከዚህ በተጨማሪ በየብስ የድንበር ቁጥጥር ላይ ተግባራዊ የሚደረገው ቴክኖሎጂ ከአለማቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ደረጃ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው የተቋሙ ሃላፊዎች ጋር ምክክር ተካሒዷል። በቀጣይ ቀናትም ተመሳሳይ ምክክሮች እንደሚካሄዱ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በኢትዮጵያ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ ለቴክኖሎጂ ልማት ትኩረት ተሰጥቷል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Aug 1, 2024 489
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 25/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ ለቴክኖሎጂና ለሰው ኃይል ልማት ትኩረት መሰጠቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ያለማቸውን የንብረት፣ የሰው ኃይልና የፕሮጀክት አስተዳደር የዲጂታል ስርዓትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፥ ኢትዮጵያን ከልመና ለማላቀቅና የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል። የአማራ ክልል በግብርናው መስክ ለሀገር ዕድገት ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ገልጸዋል። በቱሪዝም ዘርፉም ከነባር ቅርሶች ባሻገር እንደጎርጎራ ያሉ ውብ መዳረሻዎች መገንባታቸው ለዘርፉ ዕድገት ወሳኝ ነው ብለዋል። በቴክኖሎጂ ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በማዘመን ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነም አንስተዋል። ከዚህ አኳያ የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የንብረት፣ የሰው ኃይልና የፕሮጀክት አስተዳደርን ለማዘመንና ስራን ውጤታማ ለማድረግ ያስጀመራቸው የአይሲቲ መሠረተ ልማቶች የሚያበረታቱ ናቸው ብለዋል። የውሃ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም በአግባቡና በግልፅ ለመምራት የተጀመረው የዲጂታል ስርዓት አበረታች ስለመሆኑ ገልጸዋል። የዲጂታል ዘርፉን በአግባቡ የሚመራና የሚያስፈጽም የሰው ኃይል ግንባታ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል። በተለይም የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቱን ከዘመኑ ዕድገትና ለውጥ አኳያ በየጊዜው ማሻሻል አስፈላጊ ነው ብለዋል። የለሙ መሠረተ ልማቶችን ከዘራፊዎችና ከሳይበር ጥቃት መከላከል የግድ እንደሆነም ጠቁመዋል። ከሌሎች ተቋማት ጋር የተናበበ አገልግሎትን መዘርጋትም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል። ቴክኖሎጂ አሰራርን ለማዘመንና አገልግሎትን ለማፋጠን ጉልህ ሚና እንዳለው በመግለጽ ይህንን በውጤታማነት ለመጠቀም ለሰው ኃይል ግንባታ ትኩረት መስጠት ይገባል ነው ያሉት። የውሃና ኢነርጂ ቢሮ በቴክኖሎጂ ለተደገፈ ዘመናዊ አሰራር ያሳየው ተነሳሽነት ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፥ የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ የቴክኖሎጂ ልማት ነው ብለዋል። ከዚህ አኳያ የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ያስጀመራቸው የዲጂታል አገልግሎቶች በተለይ የህዝብ የአገልግሎት እርካታን ለማሻሻል የጎላ አበርክቶ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል። ቴክኖሎጂው በአግባቡ ውጤት እንዲያመጣ የሰው ኃይል ሙያዊነት እውቀትና ስነምግባር ላይ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል። መሰል የዲጂታል አገልግሎት ፕሮጀክቶችን በዘላቂነት ችግሮችን መፍታት እንዲችሉ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል። የዲጂታል አገልግሎቱ የህዝብን ቅሬታ የፈታ መሆኑን በየጊዜው መፈተሽ ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል። በ2017 በሁሉም ዘርፎች ዲጂታላይዜሽንን ለመተግበር መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።
ስፖርት
ተጠባቂው የ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ዛሬ ማምሻውን ይካሄዳል
Aug 5, 2024 171
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 29/2016(ኢዜአ)፦በፈረንሳይ ፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች የሚደረገውን የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን በጉጉት ይጠብቁታል። ውድድሩ ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ15 ደቂቃ 80 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ስታድ ደ ፍራንስ ብሔራዊ ስታዲየም ይከናወናል። በፍጻሜው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ አትሌት እጅጋየሁ ታዬና አትሌት መዲና ኢሳ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። አትሌቶቹ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም የተደረገውን ማጣሪያ አልፈው ለፍጻሜው ደርሰዋል። ውድድሩን ያሸንፋሉ ተብሎ የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል አንዷ የርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው ጉዳፍ ፀጋይ ናት። ጉዳፍ እ.አ.አ በ2023 በአሜሪካ ኢውጅን በተካሄደ ውድድር 14 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ ክብረ ወሰኑን የጨበጠችበት ሰዓት ነው። አትሌቷ በቶኪዮ በተካሄደው 32ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ5 ሺህ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታ ነበር፤ በሁለተኛ የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ወርቅ ለማምጣት ትሮጣለች። ሌላኛዋ ተወዳዳሪ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ይሄ ሁለተኛ ተሳትፎዋ ነው። እጅጋየሁ በ32ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃ ነበር። አትሌቷ እ.አ.አ በ2022 በአሜሪካ ኢውጅን በተደረገ ውድድር 14 ደቂቃ ከ12 ሴኮንድ ከ98 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባለች። በፍጻሜው ኢትዮጵያን የምትወክለው ሶስተኛ አትሌት ታዳጊዋ መዲና ኢሳ ናት፤ መዲና በኦሊምፒክ ስትሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አትሌት መዲና ከሁለት ዓመት በፊት በለንደን በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር 14 ደቂቃ ከ16 ሴኮንድ ከ54 ማይክሮ ሴኮንድ በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባለች። በጋና አክራ በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም በተከናወነው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች እና ከሁለት ዓመት በፊት በኮሎምቢያ በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና በ5 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በፍጻሜው የኢትዮጵያ አትሌቶች ከኬንያውያኑ ፌዝ ኪፕዬጎንና ቢትሪስ ቺቤት እንዲሁም በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኔዘርላንዳዊ ከሆነችው ሲፋን ሀሰን ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ በስፖርት ቤተሰቡ በጉጉት ይጠበቃል። በተያያዘም ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ47 ደቂቃ ላይ የ8 መቶ ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ይደረጋል፤ በውድድሩ ላይ አትሌት ፅጌ ዱጉማና አትሌት ወርቅነሽ መለሰ ይሳተፋሉ። ትናንት በተደረገው የርቀቱ የግማሽ ፍጻሜ ውድድር አትሌት ፅጌ ከምድብ 2 1ኛ እንዲሁም ወርቅነሽ መለሰ በምድብ 1 2ኛ በመውጣት ለፍጻሜ አልፈዋል። አትሌት ፅጌ 1 ደቂቃ ከ57 ሴኮንድ ከ47 ማይክሮ ሴኮንድ፣ አትሌት ወርቅነሽ 1 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ6 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓታቸው ነው። አትሌቶቹ ትናንት በተደረገው ማጣሪያ በርቀቱ ያላቸውን የግል ምርጥ ሰዓታቸውን አሻሽለዋል፤ ወርቅነሽ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የግል ምርጥ ሰዓቷን ስታሻሽል ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በተጨማሪም ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ላይ የ3 ሺህ ሜትር ወንዶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ይካሄዳል፤ ለሜቻ ግርማ፣ ጌትነት ዋለና ሳሙኤል ፍሬው ይሳተፋሉ። በ7 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ ከ11 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነው ለሜቻ ግርማ በማጣሪያው በምድብ 3 ይወዳደራል፤ በቶኪዮ በተካሄደው 32ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በርቀቱ የብር ሜዳሊያ ማግኘቱ የሚታወስ ነው። በምድብ 1 የሚገኘው አትሌት ጌትነት ዋለ 8 ደቂቃ ከ5 ሴኮንድ ከ15 ማይክሮ ሴኮንድ እንዲሁም በምድብ 2 የሚወዳደረው አትሌት ሳሙኤል ፍሬው 8 ደቂቃ ከ5 ሴኮንድ ከ78 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓታቸው ነው። በሶስት ምድብ በሚደረገው ማጣሪያ ከየምድቡ ከአንድ እስከ አምስት የሚወጡ አትሌቶች ለፍጻሜው ያልፋሉ። የፍጻሜው ውድድር ረቡዕ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ43 ደቂቃ ላይ ይካሄዳል። ኢትዮጵያ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች እስካሁን ያገኘችው 1 የብር ሜዳሊያ ብቻ ነው፤ ሜዳሊያውን ያስገኘው አትሌት በሪሁ አረጋዊ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች የፍጻሜ ውድድር ነው።
በ800 ሜትር ማጣሪያ ወርቅነሽ መለሰና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለፍጻሜ አለፉ
Aug 5, 2024 124
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ80ዐ ሜትር ዛሬ ማምሻውን በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር አትሌት ወርቅነሽ መለሰና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለፍጻሜው አልፈዋል። በምድብ 1 የተወዳደረችው አትሌት ወርቅነሽ 1 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ06 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ በመውጣት ለፍጻሜ አልፋለች። አትሌቷ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷን ለሁለተኛ ጊዜ አሻሽላለች። በምድብ 2 የሮጠችው ፅጌ ዱጉማ 1 ደቂቃ ከ57 ሴኮንድ ከ47 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት ለፍጻሜ ማለፏን አረጋግጣለች። ፅጌ በርቀቱ ያላትን የግል ምርጥ ሰዓቷን አሻሽላለች። በሶስት ምድብ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድባቸው አንደኛና ሁለተኛ የወጡት አትሌቶች ለፍጻሜው አልፈዋል። በተጨማሪም ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ ሁለት አትሌቶች ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል። የፍጻሜው ውድድር ነገ ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ላይ ይከናወናል።
በ1500 ሜትር አትሌት ሳሙኤል ተፈራና ኤርሚያስ ግርማ ለፍጻሜ ማለፍ አልቻሉም
Aug 5, 2024 119
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ1500ዐ ሜትር ወንዶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ለፍጻሜ ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል። በምድብ 1 የተወዳደረው አትሌት ሳሙኤል 3 ደቂቃ ከ33 ሴኮንድ ከ02 ማይክሮ ሴኮንድ ዘጠነኛ ወጥቷል። በምድብ 2 የተወዳደረው አትሌት ኤርሚያስ 3 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ ከ3 ማይክሮ ሴኮንድ 12ኛ በመውጣት ለፍጻሜው አላለፈም። በሁለት ምድብ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድባቸው ከአንድ እስከ ስድስተኛ የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜው አልፈዋል። የፍጻሜው ውድድር ማክሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም 3 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ ይከናወናል።
በ3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ አትሌት ሎሚ ሙለታና አትሌት ሲምቦ አለማየሁ ለፍጻሜ አለፉ
Aug 4, 2024 191
ዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ3000 ሜትር መሰናክል ሴቶች ዛሬ ረፋድ ላይ በተካሄደው ማጣሪያ አትሌት ሎሚ ሙለታና አትሌት ሲምቦ አለማየሁ ለፍጻሜው አልፈዋል። በምድብ 1 የተወዳደረችው አትሌት ሎሚ 9 ደቂቃ ከ10 ሴኮንድ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ አምስተኛ በመውጣት ነው ፍጻሜውን የተቀላቀለችው። በምድብ 2 የነበረችው ሲምቦ 9 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ ከ42 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ በመውጣት ለፍጻሜ ማለፏን አረጋግጣለች። በሶስት ምድብ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድባቸው ከአንድ እስከ አምስት የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ አልፈዋል። የፍጻሜው ውድድር ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ላይ ይከናወናል።
አካባቢ ጥበቃ
በቀሪዎቹ የክረምት ወራት ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይጠበቃል
Aug 5, 2024 97
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2016(ኢዜአ)፦ በቀሪዎቹ የክረምት ወራት የሚጠበቀው ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን ለግብርናና ለሌሎች ማኅበራዊ ሥራዎች ማዋል እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ የክረምት ወራት የዝናብ ሁኔታን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ በነሐሴና በመስከረም ወራት የክረምት ዝናብ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። የክረምት ወቅት ዝናብ አወጣጥም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና በመካከለኛ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመዘግየት አዝማሚያ እንደሚኖርም ተናግረዋል። የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች የትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፣ ሀረሪ ክልልና ድሬዳዋ አስተዳደር፣ ሰሜን ሶማሌ ክልል አካባቢ ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ ትንበያዎች ያሳያሉ ብለዋል። ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ከመደበኛ በላይ የሆነውን ዝናብ ለግብርናና ለሌሎች ማኅበራዊ ሥራዎች ማዋል እንደሚገባ ተናግረዋል። የሚኖረው ዝናብ ለመኽር ሰብሎች በቂ እርጥበት እንዲኖር የሚያስችል ሲሆን በእርጥበት አጠር አካባቢዎች የዝናብ ውኃን ለማሰባሰብ አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል። በተጨማሪም የግድቦች የውኃ መጠንና የገጸ ምድርና ከርሰ ምድር ውኃ እንደሚጨምሩ እና ለአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል። በሌላ መልኩ የአፈር ውስጥ እርጥበት መብዛት የአፈር መሸርሸርና የመሬት መንሸራተት፣ የሰብል በሽታዎች ሊኖር ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል። ጎን ለጎንም በማሳዎች ላይ የውኃ መተኛት በረባዳማ አካባቢዎች በሚዘሩ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችልና የወንዝ ሙላት ሊከስት ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
ከ157 ቶን በላይ የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ ቆሻሻ ተወግዷል
Aug 4, 2024 154
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ባለፈው በጀት ዓመት ከ157 ቶን በላይ የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ ቆሻሻ መወገዱን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። የአገልግሎት ጊዜያቸው የተጠናቀቀ የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ ዕቃዎች በአግባቡ ካልተወገዱ ለአካባቢ ብክለትና ለጤና ጠንቅ እንደሚሆኑ ይነገራል። በዚህም መሰረት የኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሪክ ቆሻሻን የማስወገድ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። በባለስልጣኑ የአካባቢ ህግ ተከባሪነት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አዲሱ ጥበቡ፤ የአካባቢ ጥበቃ የሁሉም በመሆኑ የብክለትና የንጽህና መጓደል ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን በጥንቃቄ ማስወገድ እንደሚገባ ገልጸዋል። በዚህ ረገድ በተለይም የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ ቆሻሻ አካባቢን ከማቆሸሽ አልፎ ለጤና አደገኛ በመሆኑ የክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የማስወገድ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ ቆሻሻ ለማስወገድ የሚፈልግ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከአካባቢ ጥበቃ ፈቃድ መውሰድ ግዴታ መሆኑን ጠቅሰው በዚሁ መሰረት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ157 ቶን በላይ የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ ቆሻሻ መወገዱን ገልጸዋል። አሁን ላይ የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ ቆሻሻ ክምችት እየተበራከተ መምጣቱን የጠቆሙት ተወካዩ ሁሉም የመንግሥትና የግል ተቋማት በጥንቃቄና በአግባቡ ማስወገድ እንዲችሉ አሠራር ይዘረጋልም ብለዋል። የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ማደስንና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን መልመድ ይገባል ሲሉም መክረዋል። የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክ ቆሻሻ፣ ከጨረር አመንጪ መሳሪያዎች ውጭ ሁሉም ዓይነት የተጣለ የኤሌክትሪክና የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ እና የመሳሪያ ክፍል የሚያጠቃልል ነው። በዚህም መሰረት ከሦስት ዓመታት በፊት በተካሄደ ጥናት በኢትዮጵያ 43 ሺህ ቶን የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ ክምችት መኖሩ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በምግብ እራስን የመቻል ዓላማን የሚያሳካ ነው
Aug 3, 2024 179
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በምግብ እራስን የመቻል ዓላማን የሚያሳካ መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በማእከላዊ ኢትዮጵያ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራት ሥራዎችን አስጀምረዋል። አፈ-ጉባዔው ከተለያዩ የፌዴራልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በፌዴሬሽን ምክር ቤትና በተጠሪ ተቋማት የሚሰሩ የአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳት ስራዎች በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቁ ገልጸዋል። በተጨማሪም 300 ለሚጠጉ ተማሪዎች ለ2017 ዓ.ም የሚሆኑ የትምህርት ቁሳቁሶች መበርከቱን ገልጸዋል። በቡታጅራ ከተማ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ሥራዎችን በማከናወናቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለጸዋል። ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትልቅ አቅም ያለው መሆኑን ገልጸው፤ የተጀመሩ የልማት እንዲሁም ሰላምን የማጽናት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ አካባቢን ከመጠበቅ ባሻገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ትግል አካል መሆኑን አስረድተዋል። አገራት እራሳቸውን በምግብ እስካልቻሉ ድረስ ከጥገኝነት ሊወጡ አይችሉም ያሉት አፈ ጉባኤው ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በምግብ እራስን የመቻል አላማን የሚያሳካ መሆኑን ተናግረዋል። የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጉዳይ የሞት ሽረት መሆኑን ገልጸው ለዚህም የአረንጓዴ አሻራ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። መንግሥት የገባውን ቃል በሙሉ ይተገብራል ያሉት አፈ-ጉባዔው፤ ለዚህም በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በበኩላቸው፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልሉ ለሚያከናውናቸው የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን ምስጋና አቅርበዋል። የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም ምርታማነት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ሰላምን የማጽናት እና የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማጎልበት የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል። ነሐሴ 13 ቀን 2016 ክልሉ የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአንድ ጀምበር 2 ነጥብ 5 ሚልዮን ሰው የሚሳተፍበት የችግኝ ተከላ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል። ለዚህም የመትከያ ቦታዎችን የመለየትና ጉድጓዶችን የማዘጋጀት ስራ መጠናቀቁን ገልጸዋል። አፈ-ጉባዔ አገኘው ተሻገር ከተለያዩ የፌዴራልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የቡታጅራ ከተማ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ፖሊስ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ ባለፈ በበጎ ፍቃድ ተግባራት በመሰማራት ህዝባዊነቱን እያስመሰከረ ነው
Aug 3, 2024 176
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ፖሊስ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ ባለፈ በበጎ ፍቃድ ተግባራት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን እያስመሰከረ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሮችና አባላት በዛሬው ዕለት በኮልፌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ሁሉም የፖሊስ ሰራዊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር ) አነሳሽነት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ገቢራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ፖሊስ መንግስት የጀመረውን ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ መርሀ ግብር በመደገፍ ችግኝ ይተክላል፤ ጽድቀታቸውንም ይከታተላል ብለዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለም ላይ ያስከተለውን ጎርፍ ድርቅና መሰል የተፈጥሮ አደጋ ለመከላከል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ድርሻው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መርሀ ግብሩ ምግብ ነክ የሆኑ ችግኞችን በመትከል የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል ፕሮጀክት በመሆኑ ፖሊስ በትኩረት የሚሰራበት ማህበራዊ ሃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ የደን ሽፋን እየተሻሻለ መምጣቱን የገለጹት ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ፤ ከልማት ተግባራት ባሻገር ፖሊስ በመደበኛ ሥራው የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ አለኝታነቱን አረጋግጧል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰራዊት ሰፊ ቁጥር ያለውና በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢ የሚገኝ በመሆኑ ከመደበኛ ሥራው ባሻገር በማህበራዊ አገልግሎቱ ህዝባዊነቱን ማረጋገጥ አስችሎታል ብለዋል፡፡ በመሆኑም በመንግስት ከተሰጠው የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ተልዕኮ ባሻገር በሌሎች ሀገራዊ በጎ አድራጎት ሥራዎች የሚኖረው ተሳትፎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአድማ ብተና ፖሊስ መምሪያ ሬጅመንት 1 ምክትል አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር አባተ ፈለቀ ፖሊስ እንደ ዜጋ በችግኝ ተከላ አሻራውን በማሳረፍ የቀጣዩ ትውልድ አርአያ መሆኑን በተግባር ያሳያል ብለዋል፡፡ ረዳት ሳጅን አረብ ሁሴን በበኩላቸው በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተሳትፎ ከማድረግ ባለፈ እንደ ፖሊስ ማንኛውንም መስዋዕትነት በመክፈል ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች አገር ለማስከበር እንሰራለን ብለዋል፡፡ አረንጓዴ አሻራ ህይወትን ማስቀጠል ነው የሚሉት የፖሊስ አባላቱ፤ የዜጎችን ደህንነተ ከመጠበቅ ባለፈ ሰው ተኮር በሆኑ ጉዳዮች ላይ በንቃት እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል፡፡ የፖሊስ ሰራዊቱ ችግኝ ከመትከል ባለፈ የተተከሉትን በመንከባከብ ለውጤት ማብቃት የሚያስችል መርሀ ግብር ማዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ በ2024 በርካታ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያሏቸው 10 አገራት ይፋ ሆኑ
Jul 22, 2024 1165
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ በ2024 በርካታ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያሏቸው 10 አገራት ይፋ ተደረጉ። የሩሰያ ዜና አገልግሎት ስፑትኒክ እንደዘገበው ናይጄሪያ ከሁሉም አገራት የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዛለች። ኢትዮጵያ ደግሞ ከኬኒያና ታንዛኒያን ቀድማ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ታንዛኒያ በመጨረሻው በ10ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ዘገባው ያሳያል። የደረጃ አሰጣጡ መሰረት ያደረገው ከ80 ሺህ በላይ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተመርኩዞ መሆኑን ስፑትኒክ ጠቁሞ መስፈርቱ ከ22 ሺህ 500 በላይ የመረጃ ምንጮችን የሸፈነ እንደሆነም አመልክቷል። ለደረጃ አሰጣጡ ኦንላይን ስታትስቲክስ ፖርታል በመጠቀም መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራ መከናወኑ ተገልጿል። በአፍሪካ አገራት በይነ መረብ ወይም ኢንተርኔት በተመጣጣኝ ዋጋ ባላቸው መሳሪያዎች ተደራሽነት በአሁኑ ወቅት እያደገ መምጣቱን በዘገባው ተገልጿል። በተጨማሪም የተሻለ የቴሌኮም ግንኙነት በተለይም የዲጂታል አገልግሎቶች በመስፋፋታቸው ምክንያት የዓለም አቀፍ እና የአፍሪካ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ማሻቀቡን ቀጥሏል ብሏል ስፑትኒክ በዘገባው። በአፍሪካ ያለው የኢንተርኔት አጠቃቀም ምንም እንኳን ከሌሎች ክፍለ ዓለማት ጋር ሲነጻጸር አሁንም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ቢሆንም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን አስደናቂ እድገት መታየቱን ዘገባው አስታውሷል። ዘገባው እ.ኤ.አ. በ2024 የኢንተርኔት አጠቃቀምን የሚመሩ አስር የአፍሪካ ሀገራትን ዝርዝር እንሚመለከተው አስቀምጧል፡- 1. ናይጄሪያ (103 ሚሊዮን ወይም 45 ነጥብ 2 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 2. ግብፅ (82 ሚሊዮን ወይም 76 በመቶው ህዝብ)፣ 3. ደቡብ አፍሪካ (45 ሚሊዮን ወይም ከህዝቡ 72 ነጥብ በመቶ)፣ 4. ሞሮኮ (34 ሚሊዮን ወይም 92 ነጥብ 2 በመቶው የህዝብ ብዛት)፣ 5. አልጄሪያ (33 ሚሊዮን ወይም 71 ነጥብ 8 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 6. ዲሞክራቲክ ኮንጎ (28 ሚሊዮን ወይም 27 ነጥብ 4 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 7. ጋና (24 ሚሊዮን ወይም 71 ነጥብ 3 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 8. ኢትዮጵያ (24 ሚሊዮን ወይም 21 ነጥጭብ 1 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣ 9. ኬንያ (22 ሚሊዮን ወይም 43 ነጥብ 3 በመቶው የህዝብ ብዛት)፣ 10. ታንዛኒያ (21 ሚሊዮን ወይም ከህዝቡ 33 ነጥብ 4 በመቶ
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጪው የአሜሪካ ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ
Jul 22, 2024 826
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2016(ኢዜአ)፦የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቀጣዩ አመት በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንት ባይደን በመጪው አመት በሚካሄደው የአሜሪካ ምርጫ ከተቀናቃኛቸው ሪፕብሊካን ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ጋር የምረጡኝ ቅስቀሳ ፉክክር ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል። ሆኖም ዛሬ አመሻሽ በፃፉት ደብዳቤ በምርጫው እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል። ዝርዝር ጉዳዮችን በቅርቡ እንደሚያሳውቁ የገለጹት ባይደን ድጋፍ ያደረጉላቸውንና አሜሪካውያንን አመስግነዋል። ምርጫው እስከሚካሄድበት ጊዜ ድረስ በኃላፊነታቸው እንደሚቆዩ መግለጻቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። አሁን ዘግይቶ በወጣ መረጃ ባይደን ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ በምክትላቸው ካማላ ሀሪስ የመተካት እድላቸው ሰፊ መሆኑ ተመልክቷል።
በአፍሪካ ቀንድ በመጪዎቹ ሶስት ወራት ከወትሮው የተለየ የሙቀት መጠን ሊኖር ይችላል
Jul 21, 2024 948
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2016(ኢዜአ)፦ በአፍሪካ ቀንድ በመጪዎቹ ሶስት ወራት ከወትሮው የተለየ የሙቀት መጠን ሊኖር ይችላል። የኢጋድን በይነ መረብ ዋቢ አድርጎ ዥንዋ እንደዘገበው፤ በአፍሪካ ቀንድ ከነሐሴ እስከ ጥቅምት ወራት ባለሉት ጊዜያት ከወትሮው የበለጠ የሙቀት መጠን ይኖረዋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ ኤጀንሲ የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ከነሀሴ እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት ከወትሮው የበለጠ ሙቀት እንደሚኖረው ትናንት ማስታወቁን ዘገበው አመልክቷል። የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ ማመልከቻ ማእከል ያስታወቀው፤ በአካባቢው በሚገኙ አንዳንድ ሀገራት የሙቀቱ መጠን እስከ 35 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊደርስ እንደሚችልም ነው የጠቆመው። ይሁን እንጂ ከሙቀቱ በተጋዳኝ በአንዳንድ አካባቢዎች ከወትሮው የተለየ ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ሊስተዋል እንደሚችል ድርጅቱ አስታውቋል። ሌሎች እንደ ጂቡቲ ፡ ኬንያ ፡ ደቡብ ሱዳን ፡ ሱማሊያና ኡጋንዳ በመሳሰሉት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ከፍተኛ የሙቀት መጠን የሚመዘገቡባቸው እንደሆኑም ዥንዋ በዘገባው አመላክቷል። በአካባቢው ከሚከሰተው ከፍተኛ ሙቀት በተጨማሪም ከነሀሴ እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት የአፍሪካ ቀንድ ምስራቃዊ ክፍሎች ከወትሮው የበለጠ ደረቅ የአየር ንብረት እንደሚያጋጥማቸው የማዕከሉ ትንበያ ያመለክታል።
የተዛባ የእንቅልፍ ሰዓት ለስኳር በሽታ እንደሚያጋልጥ ተመላከተ
Jul 19, 2024 1059
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2016(ኢዜአ)፡- መደበኛ ያልሆነ ወይም የተዛባ የእንቅልፍ ሰዓት በስኳር በሽታ የመያዝ እድልን እንደሚጨምር ተመላክቷል። የዩናይትድ ኪንግደም ባዮባንክ ያካሄደው ተከታታይ ጥናት መደበኛ ያልሆነ የመኝታ ሰዓት አጠቃቀም ለታይፕ 2 ስኳር በሽታ አጋላጭ ምክንያቶች ሰፊ ድርሻ እንደሚኖረው አስገንዝቧል። የተለያየ የመኝታ ሰዓት የሚጠቀሙና መደበኛ የእንቅልፍ ቆይታ የሌላቸው ሰዎች ለስኳር በሽታ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ነው ጥናቱ ያመለከተው። ጥናቱ የተካሄደው በአማካይ 62 አመት የሞላቸው 84 ሺህ ስኳር ታማሚ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ሲሆን ለ7 ተከታታይ ቀናት የእንቅልፍ ሰዓታቸው ላይ ቁጥጥር ሲደረግ ነበር። በጥናቱ ውጤት መሰረት "መደበኛ ያልሆነ" የእንቅልፍ ሰዓት ተብሎ የተለየው በየቀኑ በአማካይ ከ1ሰዓት በላይ የሚለዋወጥ የእንቅልፍ ቆይታ መሆኑን ዩፒአይ ዘግቧል። በዚህም ከ60 ደቂቃ በላይ በየቀኑ የእንቅልፍ ሰዓታቸው የሚዛባ 34 በመቶው የጥናቱ ተሳታፊዎች ለስኳር ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቱ እንዳመለከተ ተገልጿል። በተጨማሪም የጥናቱ ተሳታፊዎች ባለፉት ሰባት ዓመታት ባጋጠማቸው የስኳር በሽታ ተጋላጭነት ላይ የዳሰሳ ጥናት መደረጉም ተመልክቷል። የጥናት ቡድኑ ለስኳር በሽታ ተጨማሪ አጋላጭ የሆኑ ምክንያቶችን ከለየ በኋላ የተዛባ ወይም መደበኛ ያልሆነ የእንቅልፍ ሰዓት ለታይፕ 2 ሰኳር በሽታ አጋላጭ ምክንያት መሆኑን አረጋግጧል። የጥናት ቡድኑ መሪ የሆኑት ሲና ኪያነርሲ ወጥነት ያለው የእንቅልፍ ሰዓት በታይፕ 2 ስኳር በሽታ የመያዝን እድል ለመቀነስ ጉልህ ድርሻ እንዳለው በጥናቱ መረጋገጡን ተናግረዋል።
ሐተታዎች
በኦሊምፒክ ጨዋታዎች በርካታ ሜዳሊያዎችን ያገኙ የኢትዮጵያ አትሌቶች
Aug 4, 2024 173
ኢትዮጵያ በፓሪስ እየተካሄደ የሚገኘውን ጨምሮ በኦሊምፒክ መድረክ ስትሳተፍ ለ15ኛ ጊዜ ነው። በአውስትራሊያ ሜልቦርን እ.አ.አ በ1956 የተካሄደው 16ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ያደረገችበት ታሪካዊ ሁነት ነው። እ.አ.አ. በ1960 በሮም በተደረገው 17ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች አትሌት አበበ ቢቂላ በማራቶን በባዶ እግሩ በፈጸመው አኩሪ ገድል ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅና ታሪካዊ ሜዳሊያ አስገኝቷል። አትሌቱ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ወርቅ ያገኘ የመጀመሪያው አፍሪካዊም ሆኗል። አትሌት አበበ ከአራት ዓመት በኋላ በቶኪዮ በተካሄደው 18ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በማራቶን ክብሩን በማስጠበቅ የወርቅ ሜዳሊያውን በድጋሚ አግኝቷል። ኢትዮጵያና ኦሊምፒክ ሲታወሱ አበበ ቢቂላ በሰራው ታሪክ በትውልዶች መካከል እየተዘከረ ይኖራል። ኢትዮጵያ በፓሪስ እየተደረገ ባለው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ10000 ሜትር ወንዶች ፍጻሜ በአትሌት በሪሁ አረጋዊ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። የበሪሁንን ጨምሮ ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች 23 የወርቅ፣ 13 የብርና 23 የነሐስ በድምሩ 59 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ሁሉም ሜዳሊያዎች የተገኙት በአትሌቲክስ ስፖርት ነው። በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በማራቶን ወንዶች የሚወዳደረው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በኦሊምፒክ ተሳትፎው 3 ወርቅ እና 1 የብር በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት በርካታ ሜዳሊያዎችን ያገኘ ኢትዮጵያዊ አትሌት ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል። አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 3 የወርቅና 3 የነሐስ በድምሩ 6 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሌላኛዋ አትሌት መሰረት ደፋር 2 የወርቅ እና 1 የብር በድምሩ 3 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሶስተኛ ስፍራን ይዛለች። የወቅቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና ማርሽ ቀያሪው ምሩጽ ይፍጠር በተመሳሳይ 2 የወርቅና 1 የነሐስ በድምሩ 3 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። አትሌት አበበ ቢቂላና ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በተመሳሳይ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ቀጣዩን ደረጃ ይዘዋል። ማሞ ወልዴ፣ ፋጡማ ሮባ፣ እሸቱ ቱራ፣ ፊጣ ባይሳ፣ የወቅቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ ኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ፣ ሚሊዮን ወልዴ፣ አልማዝ አያና፣ ሰለሞን ባረጋና ጉዳፍ ፀጋይ ለኢትዮጵያ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ሜዳሊያ ካስገኙ አትሌቶች መካከል ይጠቀሳሉ። እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በሚቆየው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በአትሌቶቿ ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል።
የእናቶችን ችግር ያቀለለ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት
Aug 2, 2024 227
የእናቶችን ችግር ያቀለለ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምቹ የመኖሪያ እና አረንጓዴ አካባቢ የሚያካትተውን የክረምት በጎ ፈቃድ በአዋሬ አካባቢ ማስጀመራቸው ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ በአዲስ አበባ በተለያየ አካባቢዎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቤት እድሳትና ግንባታ መርሃ-ግብር እየተከናወነ ይገኛል። በከተማውም በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መኖሪያ ቤታቸው የታደሰላቸውና ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካማ እናቶች እንደሚሉት መርሃ ግብሩ ችግራቸውን አቃሎ እፎይታ እየሰጣቸው መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል። እማማ እቴነሽ ገብረስላሴ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ አሁን ላይ የ93 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ናቸው። ከወጣትነታቸው እድሜ ጀምሮ እንጀራ በመጋገር፣ የድግስ ምግቦችን በማዘጋጀትና የተለያየ የጉልበት ስራዎችን በመስራት ይተዳደሩ እንደነበር ያስታወሳሉ። ከጎናቸው የሚረዳቸው ልጅ፣ የቅርብ ዘመድና ቤተሰብ አለመኖሩ ደግሞ ድህነትንና ህመምን በብቸኝነት መግፋት ከባድ ፈተና መሆኑን ያስረዳሉ። በዋናነት ደግሞ ለዘመናት ያለምንም ጥገና ይኖሩበት የነበረው ጠባብ ቤት በእጅጉ ማርጀቱን ተከትሎ ሌላ የህይወት ውጣ ውረድ እንደሆነባቸውም ይገልጻሉ። እማማ እቴነሽ እንደሚሉት''እርጅናውም ሲጫነኝ ወጥቶ መስራቱ ሲቀር እንኳን ጣራና ግድግዳው የሚያፈስ ቤቴን ለማደስ በልቶ ማደርም ስቃይ ነበር'' ሲሉ የነበሩበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያስታውሳሉ። በተለይም ቤቱ ከመጸዳጃ ቤት ጋር ተያይዞ በመሰራቱ ችግሩን እንዳባባሰው ይገልጻሉ። ይሁን እንጂ በበጎ ፍቃደኞችና መልካም ሰዎች ትብብር ቤታቸው ፈርሶ በአዲስ መልክ እንደተገነባላቸውና የዘመናት ችግራቸው እንደተቀረፈላቸው በደስታ ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት በአዲሱ ቤታቸው ቀሪ እድሜያቸውን ያለምንም ስጋት እየገፉ መሆናቸውን ገልጸው፤ ለተደረገላቸው ድጋፍና እገዛ በእጅጉ አመስግነዋል። ሌላኛዋ የቤት እድሳት ተጠቃሚና የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሃያት አህመድና ወይዘሮ በሪሃ ደሊል ቀደም ሲል የነበረው ቤታቸው በእጅጉ ያረጀና ያዘመመ እንደነበር አስታውሰዋል። ወይዘሮ ሃያትና ወይዘሮ በሪሃ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ መሆናቸው ደግሞ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ለአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ መዳረጋቸውን ይናገራሉ። የገቢ ምንጫቸው ከቤተሰባቸው መሰረታዊ ፍጆታ የሚተርፍ ባለመሆኑ ቤቱን ማደስ የማይታሰብ እንደነበር ሁለቱም እናቶች ይገልጻሉ ። ይሁን እንጂ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት በጎ ፍቃደኞች ትብብር ቤታቸው በአዲስ መልክ በመታደሱ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል። ይህ እድል የበጎ ፍቃደኞች ጥረትና ርብርብ ውጤት መሆኑን ጠቁመው፤ ሁሉም ለበጎ ፍቃድ አገልግሎት አዎንታዊ ምላሽ መስጠት እንደሚጠበቅበትም አንስተዋል። የአዲስ አበባ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ኮሚሽን በበኩሉ በከተማዋ የሚሰጡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል ረገድ አይነተኛ ሚና እያበረከቱ ስለመሆናቸው ገልጸዋል። የአዲስ አበባ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብረሃም ታደሰ በበጎ ፍቃድ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የቤት ግንባታና እድሳት አንዱና ዋነኛው መሆኑን አስረድተዋል። ይህ አገልግሎት ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው ዜጎች፣ የአገር ባለውለታዎች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ታሳቢ በማድረግ የሚከናወን ነው። በዚህ የቤት እድሳትና ግንባታ መርሐ-ግብር ያለ ምንም ክፍያ በጉልበታቸው የሚያገለግሉ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች፣ የግንባታ ባለሙያዎችና ባለሃብቶች የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ጉልህ ድርሻ አለው ብለዋል። በበጎ ፍቃድ የሚገነቡ ቤቶች ጽዱና ውብ አካባቢን በመፍጠር የነዋሪዎችን ጤና ከመጠበቅ ባለፈ አስቸጋሪ በሆነ የኑሮ ሁኔታ የሚፈጠሩ ማህበራዊ ቀውሶችን ለማስቀረት አይነተኛ ሚና እንዳላቸው ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። የዜጎችን የአኗኗር ዜዬ በመቀየር፣ የስራ እድልን በመፍጠርና ዘመናዊነትን በማላመድ ረገድ የበጎ ፍቃድ የቤት እድሳትና ግንባታ ፕሮግራም ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ በጎ ፍቃደኞች በተለያዩ መስኮች እየተሳተፉ ሲሆን 5 ቢሊየን ብር የሚገመት የልማት ስራ ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ሰው ለማዳን የተከፈለ ዋጋ!
Jul 30, 2024 312
ጠዋት ሁለት ሰዓት ላይ ነው "ድረሱልን!" የሚለውን ድምጽ የሰሙት ወይዘሮ ውድነሽ ዶአ። የድረሱልን ጥሪውን እንደሰሙ 'ለሰው ደራሽ ሰው ነው' በማለት ከባለቤታቸው ጋር ከቤታቸው ወደ ስፍራው ያቀናሉ። በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የተደናገጡት የአካባቢው ነዋሪዎች የተጎዱትን ለማትረፍ ርብርብ እያደረጉ ነው። ወይዘሮ ውድነሽ እና ባለቤታቸው ከእነዚህ ሰዎች መካከል ተገኝተዋል። "ኬንቾ ቀበሌ የሚገኙ ቤተሰቦች በመሬት መንሸራተት ተውጠዋል" ተብሎ ሲነገራቸው ከቤታቸው ወጥቶ ለመሄድ ለአፍታም እንዳልቆዩ ነው ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወይዘሮ ውድነሽ ያወጉት። ሰብዓዊነት በልጦባቸው ሰው ለማዳን ነው ከትዳር አጋራቸው ጋር ተያይዘው ከቤታቸው የወጡት። በስፍራው ሲደርሱ በርካታ ሰዎች በመሬት መንሸራተቱ የተጎዱ ወገኖችን ለመታደግ ይጥራሉ፤ በእጃቸው በያዙት መሳሪያ ቆፍረው በማውጣት ህይወታቸውን ለመታደግ እየጣሩ እንደነበረም ያስታውሳሉ። "እኛም እነርሱን ተቀላቅለን ፍለጋውን ጀመርን" ሲሉም በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ይገልጻሉ። "በወቅቱ የተጎዱትን ነፍስ ማዳን እንጂ የመሬት መንሸራተቱ ዳግም የሚከሰት አልመሰለንም ነበር። በዚያ ሰዓት ሁላችንም አፈሩን ባገኘነው ነገር መቆፈራችንን ቀጠልን። 'ዳግም ሌላ ናዳ ሊመጣ ይችላል ውጡ የሚል መልዕክት ቢደርሰንም የታየን የሌሎችን ነፍስ ማትረፍ ስለሆነ ፍለጋውን ቀጠልን” ይላሉ። "ወገኔ ጎረቤቴ" ያሉት ሰው አፈር ተጭኖት ትቶት መሄድ አንጀታቸው አልቻለም፤ ለራሳቸው ህይወት ሳይሳሱ በናዳው የተጎዱትን ለማዳን ጥረታቸውን ቀጠሉ። ብዙም ሳይቆይ ግን ድንገት ሌላ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከሰተ። እርሳቸው እንደሚያስታውሱት ሁሉም ከአደጋው ለማምለጥ ነፍስ አውጪኝ ብሎ እግሩ ወደመራው መሸሽ ጀመረ። “እኔም እንዲሁ መሮጥ ጀመርኩ፤ ግን ብዙም ሳይቆይ እኔም ከፊቴ ሲሮጡ የነበሩትም ናዳው በላያችን አርፎብን ወደቅን። ፊቴን የሸፈነውን ጭቃ እየጠረኩ "አድኑኝ! አድኑኝ!" የሚል ድምጽ ደጋግሜ ማሰማት ጀመርኩ” ይላሉ ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስታውሱት። የሰው ህይወት ለማዳን ከቤታቸው በአንድ ላይ የወጡት ባልና ሚስቶች አደጋው ለያቸው። እርሳቸው ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ ባለቤታቸው ግን ዳግም ወደማይመለሱበት ዓለም ሄዱ። ለሰው ልጅ ፍቅር፤ ለሰብዓዊነት ሲባል የተከፈለ ዋጋ ሆኖ ታሪክ ይከትበዋል። “በሰዎች ድጋፍ ከተረፍኩ በኋላ ባለቤቴ አጠገቤ አልነበረም። በወቅቱ በጭንቅላቴና በእጄ ላይ ጉዳት ደርሶብኝ ስለነበር ወደ ሕክምና አመጡኝ።" የሚሉት ወይዘሮ ውድነሽ፤ ባለቤታቸው ግን ሰው ለማዳን ሲሉ ህይወታቸው አልፎ መቀበራቸውን ሆስፒታል ውስጥ ሆነው መስማታቸውን በሀዘን ድባብ ውስጥ ሆነው ነው የሚናገሩት። በአካባቢው የደረሰው ጉዳት ሁሉንም አሳዝኗል። በመንግስት የታወጀው የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ትናንት መጠናቀቁን ተከትሎም በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡትን ያሰበ የሻማ ማብራት መርሃ ግብር ተካሂዷል። ቤተሰቦቻቸውን እና ዘመድ ወዳጆቻቸውን በአደጋው ያጡትንና የተጎዱትን ከማጽናናት ባለፈ በዘላቂነት ለማቋቋም መንግስት፣ ህዝብና የተለያዩ አካላት በጋራ እየሰሩ ናቸው።
"ከራስ በፊት ለህዝብ እና ለሀገር"
Jul 28, 2024 579
"ከራስ በፊት ለህዝብ እና ለሀገር" "ከራስ በፊት ለህዝብ እና ለሀገር" ከመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች መካከል አንዱ ነው። በመሆኑም ይህ እሴት ሠራዊቱ በሚሠማራባቸው አካባቢዎች ሁሉ ተግባር ላይ የሚውል የሠራዊቱ መለያ ባህሪ የሆነ የበጎነቱ ማሳያ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሚሠማራባቸው ቀጠናዎች ሁሉ ከህዝብ ጋር አብሮነትን በመፍጠር በሠላምም ይሁን በልማት ዙሪያ አብሮ መሥራት የዘወትር ተግባሩ ነው። ይህ ለሠላምና ለልማት በጋራ የመቆም ተግባር ሀገርን ወደ ከፍታ ማማ የሚወስድ ከመሆኑ በሻገር አብሮነትን እና አንድነትን የሚያጎለብት መልካም ሥራ ነው። በዚህ የአንድነት ሂደት ውስጥም መደጋገፍን በሠራዊቱና በህዝቡ ዘንድ በእጅጉ ጎልቶ እናገኘዋለን። ህብረተሰቡ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት ከደጀን እስከ ግንባር ድረስ በመጓዝ ለሠራዊቱ ያደረገው ድጋፍ፣ በበዓላት ጊዜ የእርድ ሠንጋዎችን ማበርከቱ ፣ሠራዊቱን የሚደግፉ ህዝባዊ ሠልፎችን ማካሄዱ እና ሌሎች አብሮነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎች ህብረተሰቡ ለሠራዊቱ ያለውን መልካም እይታና ድጋፍ የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ በተጓዳኝ መከላከያ ሠራዊቱ የሀገርን ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ በዘለለ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉ፣ ለተቸገሩ ለተፈናቀሉ ወገኖች ካለው ከትንሿ ቀንሶ መደገፉ፣ መማር እየፈለጉ የአቅም እጥረት ላለባቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ማበርከቱ፣ ለተጠማ ማጠጣቱ፣ ለተቸገረ ማብላቱ ለታረዘ ማልበሱ እና ሌሎች ድጋፎቹ ሁሉ የህዝባዊነቱ ማሳያዎች ናቸው። መከላከያ ዛሬም በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዕለት ደራሽ ምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ። በመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ አማካኝነት ቦታው ድረስ በመገኘት የተደረገው ድጋፍ ሠራዊት በሠው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ፈጥኖ የሚደርስ መሆኑን የሚያሥመሰክር ተግባር ነው። በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች የተደረገው የዕለት ደራሽ የአይነት ድጋፍ ሁለት መቶ ኩንታል የስንዴ ዱቄት፣ሁለት መቶ ሃያ አምስት ኩንታል ብስኩት ፣ሃምሳ ኩንታል ስኳር፣ ስድስት ኩንታል ሻይ ቅጠል፣ ጥንድ አንሶላ ዘጠኝ መቶ ብርድ ልብስ፣ ሲሆን አጠቃላይ በገንዘብ ሲተመን ስድስት ሚሊየን ሶስት መቶ አምስት ሺህ ብር መሆኑን ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ገልፀዋል። አደጋው በተከሰተ ማግስት በቀጠናው የሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አንድ የህክምና ቡድን ከአምቡላንስ ተሽከርካሪ ጋር ወደ ስፍራው ከመላኩ በተጨማሪ ከአምስት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ምግብ ነክ ድጋፍ ቦታው ድረስ ተገኝቶ ማሥረከቡ የመከላከያ ሠራዊቱን ህዝባዊ ወገንተኝነት የሚያረጋግጡ እውነታዎች ናቸው። መከላከያ ሠራዊት መተኪያ የሌላትን ህይወቱን ለሀገርና ለህዝብ ከመሥጠቱ ሌላ በማንኛውም ጊዜ የህዝቡን ችግር ተገንዝቦ የቻለውን ሁሉ የሚያደርግ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።
ትንታኔዎች
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ ከኢንቨስትመንትና ንግድ ተወዳዳሪነት አኳያ
Jul 31, 2024 380
በቁምልኝ አያሌው ኢትዮጵያ ወደተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ መግባቷን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ማሳወቁ ይታወቃል። የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያን የፖለቲካ ለውጥ ተከትሎም ላለፉት ስድስት ዓመታት የተከማቹ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ችግሮችን ለመፍታት መንግሥት በርካታ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ሲወስድ ቆይቷል። የዕዳ ጫና፣ የዋጋ ንረት፣ ሥራ አጥነት፣ አዝጋሚ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ፣ የሀብት ብክነት፣ ዝቅተኛ የዘርፎች ምርታማነት እና የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸሞችም መንግስት የተረከባቸው ዋና ዋና የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚጠይቁ ዕዳዎች እንደሆኑ ተገልጿል። የተወሰዱ የፖሊሲና የሕግ ማሻሻያ እርምጃዎችን ተከትሎም በ2011 ዓ.ም ተግባራዊ የተደረገው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚው ወደተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ እንዲሸጋገር አዲስ ተስፋን አምጥተዋል። በዚሁ መነሻነትም የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባትን ለማረም የዕዳ ጫናን ለማቃለል፣ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የዕድገት ምንጮችን ለማስፋት፣ የስራ ዕድል ለመፍጠር እና ማነቆዎችን ለመፍታት በተደረገው ጥረት ውጤት ተገኝቷል። በዚህም ኢትዮጵያ ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም ባሉት በጀት ዓመታት በአማካይ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት 7 ነጥብ 1 በመቶ በማድረስ በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያሳዩ ካሉ ሀገራት አንዷ ለመሆን በቅታለች። ከምሥራቅ አፍሪካ ትልቁን ኢኮኖሚ በመገንባት ከሰሐራ በታች ካሉ አፍሪካ ሀገራት 3ኛውን ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት በመሆን ለዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት አሳይታለች። ቀሪ ስራዎችን በሚገባ በመስራት አገራዊ ግብን ለማሳካትም በአራት ምሰሦዎች የተገነባው 2ኛው ምዕራፍ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ስራ ገብቷል። ምሰሦዎቹም:- የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትንና ዘላቂነትን የሚደግፍ ዘመናዊና ጤናማ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማዕቀፍ መመሥረት፣ ፈጠራን የሚያበረታታ ምቹ የኢንቨስትመንትና የንግድ ዘርፍ ከባቢና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ ምርትና ምርታማነት ዐቅምን ማጠናከር እና ጥራት ያለው አገልግሎትን በብቃት ለማቅረብ የመንግሥትን አቅም ማሳደግ ናቸው። የፕሮግራሙ ተግባራዊነት በሚቀጥሉት ዓመታት ከፍተኛ እና የተረጋጋ የኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣት የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘመናዊና ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ሥርዓትን ለመገንባት የተጣለውን ትልቅ ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ከሚተገበሩ በርካታ ጉዳዮች መካከል የመንግሥትን ኢንቨስትመንት ውጤታማነት ማሻሻል የሚል ይገኝበታል። ይህም ከ2ኛው ምዕራፍ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አራት ምሰሶዎች መካከል የሚጠቀስ ነው። ምቹ የኢንቨስትመንትና የንግድ ተወዳዳሪነት መንግስት ከሀገራዊ ለውጡ ማግስት ጀምሮ ለብዝኃ ኢኮኖሚ ግንባታ በሰጠው ትኩረት በግብርና፣ ኢንዳስትሪ፣ ቱሪዝሪም፣ ማዕድን እና አይሲቲ የልማት ምሰሶዎች የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤቶች ተገኝተዋል። ምቹ ኢንቨስትመንትና ተወዳዳሪ የንግድ ሥርዓትን ለመፍጠርም ሰፋፊ እርምጃዎች ተወስደዋል። ለአብነትም ኢትዮ-ቴሌኮምን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ወደግል በማዞር ምቹ ኢንቨስትመንትና ተወዳዳሪ የንግድ ሥርዓትን ለመፍጠር ሲሰራ ቆይቷል። በኢንቨስትመንት መስክ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች መንግስት ባመቻቸላቸው የኢንዳስትሪ ፓርኮች ተሰማርተው በተኪ እና ወጪ ንግድ ምርት ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአልሚ ባለሀብቶች የተደረገው የመሰረተ ልማት አቅርቦት እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ድጋፍ የምርት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ አስችሏቸዋል። በዚህም በተጠናቀቀው 2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 3 ነጥብ 82 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መሳብ እንደተቻለ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል። የንግድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ ገቢ፣ ጅምላና ችርቻሮ የንግድ ዘርፎች የውጭ ባለሃብቶች እንዲሳተፉ ገበያው ክፍት ተደርጓል። በዚህም የውጭ ባለሃብቶች በጥሬ ቡና፣ ቅባት እህል፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ላይ መሳተፍ የሚችሉበት ዕድል ተመቻችቷል። ኢትዮጵያ እያስመዘገበች የምትገኘውን ዕድገት ለማስቀጠል ከ2013 ጀምሮ እስከ 2022 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚደረግ ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ተዘጋጅቶ እየተሰራበት ይገኛል። ዕቅዱም በጥራት ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ዕድገትን ማምጣት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት፣ የሥርዓት ለውጥ ማምጣት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ የሴቶችና ወጣቶችን ፍትሕዊነት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲሁም የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ የመሪነት ማረጋገጥ ዓላማን ሰንቋል። ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መደረጉም ምርታማነትን በማሳደግ በምጣኔ ሃብት ዕድገት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመዘገብ አስችሏል። የመጀመሪያ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ያስመዘገባቸውን ተጨባጭ ስኬቶች በማስቀጠል ቀሪ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠልም ሁለተኛ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ተደርጓል። ሁለተኛው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደር የሚያስችል ስራ ፈጣሪ ማህበረሰብ መገንባት እንደሚያስችል ታምኖበታል። የግሉ ዘርፉ ወደ ላቀ የዕድገት ምዕራፍ እንዲሸጋገር የሚያግዝና አሁን የግሉ ዘርፍ ያሉበትን ችግሮች በመቅረፍ ባለሀብቶች በወሳኝ ዘርፎች ላይ እንዲያተኩሩ ይደርጋል። በተጨማሪም ጥራት ያለው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ጠንካራ የወጭ ንግድ ስርአት እንዲኖር መደላድል ይፈጥራል። ፈጠራን በማበረታታት ምቹ የኢንቨስትመንትና የንግድ ዘርፍ ከባቢ እንዲኖር በማድረግ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ረገድም ሚናው የጎላ ነው። በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ተግባራዊ መደረጉ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ዕድገት በማስቀጠል ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ሀገራዊ ራዕይን ዕውን ለማድረግ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ከመልከ-ብዙ የኢኮኖሚ ገጽታ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ
Jul 30, 2024 622
በረከት ሲሳይ (ኢዜአ) አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ገቢራዊ ከመደረጉ ከ2011 ዓ.ም በፊት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተከታታይ እድገት የነበረው ቢሆንም በጥቅሉ ሲገመገም የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ይስተዋልበት ነበር። ዕድገቱ በመንግሥት ከፍተኛ ወጪ በተስፋፋ የመሠረተ-ልማት አማካይነት የተመዘገበ በመሆኑ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የፈጠረ፣ አስተማማኝ የሥራ ዕድል በተፈለገው መጠን በቋሚነት መፍጠር የተሳነው፣ ከፍተኛ የብድር ጫና የፈጠረ መሆኑ ተገምግሟል። እነዚህን መዋቅራዊ ችግሮች በዘላቂነት በመፍታት በአገሪቱ ቀጣይነትና ጥራት ያለው እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የኢኮኖሚ እድገት እውን ለማድረግ በማለም በ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ወደ ሥራ ገብቷል። ማሻሻያው በተለይም የማክሮ ኢኮኖሚ የፋይናንስ መረጋጋት ለማረጋገጥ በዋናነት ጥብቅ የፊስካል ፖሊሲ ገቢራዊ አድርጓል። የዕዳ ክምችትን ማቃለል ከዚህ አንጻር በተለይም የአገሪቱን የብድር ጫና ለማቃለል ከፍተኛ ወለድ ያለው ብድር (commercial loan) በማስቀረት አነስተኛ ወለድ ያለውና የመክፈያ ጊዜው ረዘም ያለውን የብድር አማራጭ (concessional loan) ተግባራዊ ተደርጓል። ይህም ብቻ ሳይሆን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚወስዱትን ከፍተኛ ብድር በመቀነስ አነስተኛ ብድር እንዲወስዱ ማድረግ ተችሏል። በተጨማሪም ፕሮጀክቶች ሲካሄዱ አስፈላጊው ጥናት ተጠንቶ እንዲካሄድና የተቋማት የመፈጸም አቅም እንዲገነባ ለማድረግ ተችሏል። ከአበዳሪ አካላት ጋር የዕዳ ቅነሳና ሽግሽግ እንዲደረግ ያላሰለሰ ጥረት ተደርጓል። እነዚህ እርምጃዎች ተግባራዊ በመደረጋቸው አጠቃላይ የብድር ጫናው ላይ አዎንታዊ ለውጥ አምጥቷል። የወጪ ገቢ ንግድ ሚዛን ሌላው የወጪ ገቢ ንግድ ሚዛኑን ለማስተካከል ምርትና ምርታማነትን ከማበረታታት ጎን ለጎን የዘርፍ ተቋማትን አቅም የማጠናከር ሥራ ተሰርቷል። በተለይም የአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምንጭን በማስፋት የብዝኃ-ኢኮኖሚ አተያይ እንዲኖርና ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና አይ ሲ ቲ ዘርፎች ላይ በልዩ ትኩረት የተሰራው ሥራ ውጤት አምጥቷል። በዚህ ዘርፍ ላይ የተደረገው ማሻሻያ በተለይም ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የውጭ ንግድ አፈጻጸምን በማሳደግ የንግድ ሚዛኑን ከማሻሻል በተጨማሪ የአገሪቱ ገቢ እንዲያድግና የዕዳ ክፍያ በተገቢው መልኩ እንዲካሄድ ተደርጓል። ለአብነትም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከምርትና አገልግሎት ወጪ ንግድ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል። ከሐዋላ አገልግሎትም 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል። በ2016 በጀት ዓመት የ3 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ተመዝግቧል። ስንዴን ጨምሮ በተኪ ምርቶችም ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ ሲሆን፤ ለአብነትም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አሥር ወራት 2 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካት ተችሏል። ከ2010 እስከ 2015 ባሉት በጀት ዓመታት በአማካይ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት 7 ነጥብ 1 በመቶም ደርሷል። የበጀት ጉድለትን መሙላት ሌላው በፊስካል ፖሊሲው ላይ በተወሰደው እርምጃ የመንግሥት ገቢን ከአጠቃላይ አገራዊ ምርት አኳያ ለማሳደግ የተሰራው ሥራ ውጤት አምጥቷል። ከዚህ አንጻር በተለይም የታክስ ምኅዳሩን በማስፋትና ዘመናዊ የታክስ አሰባሰብ ሥርዓት ባለፉት ዓመታት ገቢራዊ በመደረጋቸው አዎንታዊ ለውጦች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ለአብነትም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ529 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል። የዋጋ ንረትን ማርገብ የምርት አቅርቦትን በማስፋት በተለይም የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ይገኛል። ምርታማነትን ማሻሻልም ሌላኛው ሥራ ነው፡፡ በዘንድሮው ዓመት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ100 ሚሊየን ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት መሰብሰብ ተችሏል። በተጨማሪም መንግሥት 10 ቢሊየን ብር ገቢ በመተው መሠረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ አድርጓል። ጎን ለጎንም የጥሬ ገንዘብ በገበያ ውስጥ ያለው ፍሰት የዋጋ ንረት እንዳያስከትል ለመቆጣጠርና መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረው የገንዘብ መጠን ለመቀነስ ሰፋፊ ሥራዎች ተሰርተዋል። የንግድ ባንኮች ለደንበኞቻቸው የሚለቁትን የብድር መጠን ላይ ገደብ መቀመጡም ተመላክቷል። እነዚህንና ሌሎች ተያያዥ የማስተካከያ ሥራዎች በመሠራታቸው የዋጋ ንረት ከዚህ ቀደም ከነበረው 30 በመቶና ከዚያ በላይ ወደ 19 ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል። የሥራ ዕድል ፈጠራ ባለፉት የሪፎርም ዓመታት የተሰሩ ሥራዎች ውጤት ያመጡ ሲሆን፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል። የሥራ ዕድሉ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በከተማ ልማትና ሌሎች መሠረተ-ልማት ዘርፎች የተፈጠረ ነው። በተጓዳኝም ከ300 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በሕጋዊ መንገድ ክብራቸውና ጥቅማቸው ተጠብቆ በውጭ አገራት የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል። ከ60 የሚልቁ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በአገር ቤት ሆነው በአውት ሶርሲንግ የተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ውስጥ የመሥራት ዕድል አግኝተዋል። የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ የመጀመሪያው የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርኃ-ግብር ቀሪ ሥራዎች ቢኖሩም፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባትን ለማስተካከል በተደረገው ጥረት ውጤቶች ማስገኘቱ ተጠቅሷል። ይህንንም ከግምት በማስገባት ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ ገብታለች። ይህ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም በአራት ምሰሶዎች ላይ የተገነባ ሲሆን፤ እነዚህም የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን እና ዘላቂነትን የሚደግፍ ዘመናዊ እና ጤናማ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማዕቀፍ መመሥረት፤ ፈጠራን የሚያበረታታ ምቹ የኢንቨስትመንትና የንግድ ዘርፍ ከባቢ እና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ ምርትና ምርታማነት አቅምን ማጠናከር እና ጥራት ያለው አገልግሎትን በብቃት ለማቅረብ የመንግሥትን አቅም ማሳደግ የሚሉ ናቸው። የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳው ለጠንካራ፣ በግሉ ዘርፍ ለሚመራ፣ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ መሠረት እንደሚሆን ታምኖበታል። ፕሮግራሙ በሚተገበርበት ወቅት ከፍተኛ እና የተረጋጋ የኢኮኖሚ ዕድገት እና ነጠላ አኃዝ የዋጋ ግሽበት ይኖራል ተብሎ ግብ ተጥሏል። የውጭ ምንዛሬ መዛባትን በማስተካከል፣ የፋይናንስ ዘርፉን ይበልጥ በማጠናከር፣ የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር፣ የታክስ ገቢን በማሳደግ፣ የመንግሥትን ኢንቨስትመንት ውጤታማነት በማሻሻል፣ የባንክ ዘርፍን ተወዳዳሪነትና ጤናማነት በማጎልበት እና የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢን በማሻሻል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘመናዊና ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ሥርዓትን ለመገንባት ትልቅ ሀገራዊ ግብ ተጥሎ እየተሰራ ይገኛል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ፣ በወለድ ተመን ላይ የተመሠረተ ዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓት ማዘመን፣ የመንግሥት ፋይናንስ ጫናዎችን የሚቀንስ የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያ፣ የልማት ፋይናንስ ዕድሎች እና የመንግሥት ዕዳ አስተዳደር ማሻሻያ እንዲኖር በማድረግ ጠንካራ፣ አካታች እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ሥርዓት የመገንባት ቁልፍ ዓላማና ግብ ሰንቆ ነው ወደ ተግባር የገባው። የፖሊሲ እርምጃዎቹ ከአጠቃላይ ሀገራዊ የረዥምና የመካከለኛ ዘመን የልማት ዕቅዶች ጋር ተጣጥመው የሚከናወኑ በመሆኑ በመጀመሪያው የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርኃ-ግብር የተስተዋሉ ቀሪ ሥራዎችን በምልዓት በመሥራት የዕዳ ክምችት በማቃለል፣ የወጪ ገቢ ንግድ ሚዛን በመጠበቅ፣ የበጀት ጉድለትን በመሙላት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን በማስፋት፣ የዋጋ ንረትን በማቃለል ትልቅ እመርታ እንደሚኖራቸው ታምኗል። በዚህም በሚቀጥሉት አራት ዓመታት በማክሮ ኢኮኖሚ የማሻሻያ እርምጃዎች ምክንያት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአማካይ በ8 በመቶ ያህል እንደሚያድግ፤ የዋጋ ንረት ወደ 10 በመቶ ዝቅ እንደሚል፤ የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 11 በመቶ እንደሚደርስ፤ የመንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ወደ 35 በመቶ ዝቅ እንደሚል፤ የወጪና የገቢ ንግድ ዋጋ ወደ 20 ቢሊየን ዶላር እንደሚያድግ፤ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ወደ 8 ቢሊየን ዶላር ከፍ እንደሚል፤ ዓለም አቀፍ የመጠባበቂያ ክምችት ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚሆን ይጠበቃል። እነዚህ ትንበያዎች በቀጣይ ዓመታት ሊመጣ የሚችለውን የኢኮኖሚ ሽግግር ደረጃ የሚያመለክቱ ናቸው። በመሆኑም ኢትዮጵያ በተሟላ መንገድ የጀመረችው ይህ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚያስጠብቅ እና የዜጎችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲተገበር ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በምታደረገው ጥረት ያልተነገረ ታሪክ
Jul 24, 2024 812
ከሚዲያ ሞኒተሪንግና ትንተና ዳይሬክቶሬት ቀደም ባሉት ዘመናት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 40 በመቶ እንደነበረ፤ ቀስ በቀስ ይህ የደን ሀብት በተለያየ ምከንያት ተራቁቶ ወደ ሦስት በመቶ ያህል አሽቆልቁሎ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። ከደን ሀብት መራቆት ጋር በተያያዘ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ተፅዕኖ የበረሃማነት መስፋፋት፣ በተደጋጋሚ የድርቅና ሌሎች ተጓዳኝ አደጋዎች መከሰት ያሳሰባት ኢትዮጵያ የደን ሀብት ልማት፣ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን አጠናክራ በመቀጠሏ እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ የደን ሀብቷ ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ ወደ 17 ነጥብ 2 በመቶ ከፍ ማለቱንም መረጃዎቹ ይጠቁማሉ። በሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያን የመምራትና የማስተዳደር ሥልጣንን የተረከቡት ባለራዕይውና የለውጥ አራማጁ መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2011 ዓ.ም ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውን እና አያሌ ትሩፋቶችን እያገናጸፈ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ሀገር አቀፍ መርሃ ግብርን ይፋ አደረጉ። መላው ኢትዮጵያውያን ባለፉት ስድስት ዓመታት መርሃ ግብሩን እውን ለማድረግ በፅናት፣ በቁርጠኝነትና በኅብረት ባከናወኗቸው አያሌ ተግባራት በአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ከራሳቸው አልፎ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ያስደመመ ውጤት አስመዝግበዋል፤ እያስመዘገቡም ይገኛሉ። የዚህ ጽሑፍ አብይ ዓላማም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጨነት እውን የሆነውን፣ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውን እና አያሌ ትሩፋቶቹን እያቋደሰ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ሀገር አቀፍ መርሃ ግብርን ዘርዝሮ ማስረዳት አይደለም። ይልቁንም ተቀማጭነታቸውን በቱርክ አንካራ ያደረጉት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት አፈወርቅ ሽመልስ “Untold story of Ethiopia's endeavor in combating climate change” በሚል ርዕስ ያሰናዱትን ጽሑፍ ወደ አማርኛ ቋንቋ በመመለስ ስለኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ያልተነገረ ታሪክ ላይ የሰጡትን ህያው እማኝነት ለውድ ተደራሲያን በአጭሩ ማቋደስ ነው። የዲፕሎማቱን እማኝነት እነሆ ብለናልና አብራችሁን ዝለቁ። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የምታደርገው ጥረት ተጨባጭ ውጤቶችን እያሳየ ነው። ሆኖም ግን በሚገባው ልክ እንዳልተነገረለት ተቀማጭነታቸውን በቱርክ አንካራ ያደረጉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት አፈወርቅ ሽመልስ ይገልጻሉ። ዲፕሎማቱ ዴይሊሳባህ ለተባለው የቱርክ ድረገጽ በላኩት ጽሁፍ ከስድስት ዓመት በፊት አረንጓዴ አሻራ ማኖር በሚል የተጀመረው አገር አቀፍ ዘመቻ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዛፍ ችግኞች የመሸፈን ብሄራዊ መርሃግብር የደን ሽፋንን በማሳደግ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል። እንደ ዲፕሎማቱ ማብራሪያ አየር ንብረት ለውጥ በተደጋጋሚ መከሰቱ ለምድራችንና ለሰው ልጆ የማይታመን ከባድ ፈተና ፈጥሯል። በአሁኑ ጊዜ የአየር ንብረት ለውጥ የሰው ልጅን ህልውና የሚፈታተን የማይቀር አደጋና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋት ሆኗል። እ.ኤ.አ. ከ1980ዎቹ ጀምሮ በዓለማችን የከፋ የአየር ሁኔታ መዛባት፣ ተደጋጋሚና ከባድ የሙቀት ማዕበል፣ በረሃማነት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የአርክቲክ በረዶ መቅለጥ፣ የብዝሀ ህይወት መጥፋት፣ የመሬት መራቆት፣ የደን ሽፋን መመናመን፣ የለም አፈር መከላት፣ የምርታማነት ዕድገት መቀነስ እና ሌሎች በርካታ ፈተናዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየታዩ ነው። በዚህ ረገድ ያደጉ አገሮች በተለይም በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ የሚገኙ ከከባድ ኢንዱስትሪዎቻቸው በሚለቀቀው የሙቀት አማቂ ጋዞች ከባቢ አየርን በመበከል የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ። ለዓለም ሙቀት መጨመር እና ለካርቦን ልቀት እዚህ ግባ የሚባል አስተዋጽኦ የሌላት አፍሪካ በጣም የተጎዳችና እየተሰቃየች ትገኛለች። በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በየጊዜው የሚያጋጥሙ ችግሮች እየተለመዱ ከመምጣታቸው የተነሳ ድንጋጤ መፍጠር እያቆሙ መሆናቸውን ያተቱት ዲፕሎማቱ አፍሪካ ለችግሮቹ እዚህ ግባ የሚባል አበርክቶ ሳይኖራት የጉዳቱ ዋነኛ ሰለባ ከሆነች በርካታ አስርት ዓመታት እንደዋዛ መንጎዳቸውን ይገልጻሉ። የአፍሪካ ቀንድ ለዓለም ጠቃሚ የጂኦ ስትራቴጂክ አካባቢ ነው። በዚህ የዓለም ክፍል ውስጥ ያሉ ሀገራት ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለከፋ ችግሮች ተጋልጠዋል ይላሉ ዲፕሎማቱ። አገራቱ ካጋጠሟቸው ተግዳሮቶች መካከል በረሃማነት፣ የብዝሀ ህይወት መጥፋት፣ተደጋጋሚ ድርቅ መከሰት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የመሬት መራቆትና የጎጂ ነፍሳት ክስተትና መስፋፋት ዋነኞቹ ናቸው። ይህ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ችግር ለከፍተኛ የምግብና የውሃ እጦት እና ለአዳዲስ የወረርሽኝ በሽታዎች መጨመርን አስከትሏል። የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን ለረጅም ጊዜ ድርቅ ተጋላጭ አድርጎታል፤ ለሶስት ተከታታይ የምርት ወቅቶች ያጋጠመው የዝናብ እጥረት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖችን ለዘለቄታው የምግብ እጥረት፣ ለስቃይ እና መፈናቀል አጋልጧል፤ ድርቁ በከብቶች ህልውና ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ ሲሆን፤ በሦስት ዓመታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶች ሞተዋል ይላሉ ዲፕሎማት አፈወርቅ በጽሑፋቸው። ዲፕሎማት አፈወርቅ አያይዘውም የአየር ንብረት ለውጥ በአፍሪካ ቀንድ በምትገኘው ኢትዮጵያም በተደጋጋሚ ለድርቅ ተጋላጭ እንድትሆን፣ በአካባቢ መራቆት፣ በረሃማነት መጨመር ረገድ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። የአየር ንብረት ለውጥ በአከባቢው በተለይም በኢትዮጵያ ያለውን አደጋ የተረዱት የኢትዮጵያ የለውጥ አራማጅ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እ.ኤ.አ በ2019 አረንጓዴ ሌጋሲ ኢኒሼቲቭ በመባል የሚታወቀውን ዛፎች የመትከል ሀገራዊ መርሃ ግብር ይፋ ማድረጋቸውን ይገልጻሉ። ይህ ተነሳሽነት በኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ያለመ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመላ ሀገሪቱ የመትከል ታላቅ ዓላማ ያለው መርሃ ግብር ነው። መንግሥት በመጀመርያው ዓመት ከ4 ቢሊዮን በላይ የተለያዩ ችግኞችን በመትከል በአንድ ጀምበር ከ353 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብሮታል ይላሉ። እንደ ዲፕሎማቱ ማብራሪያ መንግስት ለዚህ ዓለማ መሳካት በየዓመቱ ከ25 ሚሊዮን በላይ የሰው ኃይል በማነሳሳትና በመላ አገሪቱ በማሰባሰብ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ የጋራ የኃላፊነት ስሜት እንዲፈጠር አድርጓል። መንግስት የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በየዓመቱ ከሰኔ እስከ መስከረም ባለው የዝናብ ወቅት ችግኝ ተከላውን ቀጥሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተያዘው የክረምት ወራት 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን የተለያዩ ችግኞችን ለመትከል ግብ አስቀምጠው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ተጀምሯል። በመላ ሀገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ለየአካባቢው ስነምዕዳር ተስማሚ የሆኑ ከ32 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ እውን መሆን በመቻሉ የሀገሪቱ የደን ሽፋን እ.ኤ.አ በ2019 ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ በ2023 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ አድጓል። በመላ አገሪቱ በመርሃግብሮቹ ከተተከሉት ችግኞች እንደ ወይራ፣ዋንዛ፣ኮሶና ጽድ የመሳሰሉት ለየአካባቢው ስንምዕዳር ተስማሚ የሆኑ የሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች ይገኙበታል። ከዚህም በሻገር በምግብ ራስን በመቻል ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው እንደ አቮካዶ፣ማንጎ፣ዘይቱን እና ኮክ የመሳሰሉ ለቆላማና ለከፊል ቆላማ አከባቢዎች ተስማሚ የሆኑ ቋሚ የፍራፍሬ ተክሎች በአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው መሆናቸውን ዲፕሎማት አፈወርቅ አብራርተዋል። የአረንጓዴው አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ ዓላማ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህዝቦቿ የተቀናጀ ጥረት የኢትዮጵያን ተራሮች፣ ኮረብታዎች፣ ሜዳ ሸንተረሮች እና ከተሞችን አረንጓዴ በማልበስ በኢትዮጵያና በቀጣናው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚያጋጥሙ አስደንጋጭ ተግዳሮቶች ማስወገድ ነው። ዲፕሎማት አፈወርቅ በጽሑፋቸው እንዳስገነዘቡት የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር የሀገሪቱን የደን ሽፋን በማሳደግ፣ የመሬት መራቆትን በመከላከልና የደን ሀብትን በመጠበቅና በመንከባከብ ስነ-ምህዳሩን በማመጣጠን ለቀጣዩ ትውልድ ምቹና ዘላቂ አረንጓዴ አካባቢን ለማውረስ ይረዳል። እንዲሁም የዛፍ ችግኞችን በመትከል የተራቆተውን የደን ሀብት መልሶ በማልማት በከባቢ አየር ውስጥ የሚገኘውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና ሌሎች አደገኛ የሙቀት አማቂ ጋዞችን በመቀነስ ለኦዞን ሽፋን መሳሳትና ለዓለም ሙቀት መጨመር ምክንያት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥን አስከፊ ተፅዕኖ ለመቋቋም የላቀ አስተዋጽኦ ያደርጋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ አፍስሶና በሀገሪቱ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብን ጨምሮ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎችን አንቀሳቅሶ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመግታት ብርቱ ጥረት አድርጓል ይላሉ። ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ቀጣናዊ ውህደት ለመፍጠር 1 ቢሊዮን ችግኞችን ለስድስት ጎረቤቶቿ በማከፋፈል በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ የቀጣናዊ ውህደቱ አካል እንዲሆኑ አድርጋለች ሲሉም ይገልጻሉ። ዲፕሎማቱ አያይዘውም በሌላ በኩል መንግሥት በክረምት ወራት አርሶ አደሩን በማንቀሳቀስ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራውን በመላ ሀገሪቱ አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ ሺህ ኪሎ ሜትር የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ተከናውነዋል።በተለያየ ምክንያት በተራቆቱ ተራራማ፣ ዳገተማና ኮረብታማ አካባቢዎች እንዲሁም ተፋሰሶች መልሰው እንዲያገግሙና እንዲታደሱ የድንጋይና የአፈር እርኮኖችና ጋቢዮኖች ሥራ እንዲሁም ባህላዊ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ የውሃ መውረጃ ቦዮችና ማስተላለፊያ ቱቦች ግንባታ መካሄዱን በጽሑፋቸው አመላክተዋል። ፀሐፊው አክለውም የደን ልማቱና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የመሬት መራቆትን፣ በጎርፍ የመጥለቅለቅ አደጋን፣ የለም አፈር መከላትን በመታደግ የከርሰና የገፀ ምድር የውሃ ሀብት እንዲጨምሩ የሚያስችሉና አረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ውጥኖች የሆኑትን የውሃ ሼድ አያያዝ በኢትዮጵያ ሥነ-ምህዳራዊ ስርዓት መደበኛ በማድረግ በረሃማነትን በዘላቂነት በመከላከል ዓባይን በመሳሰሉት ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን የውሃ ፍሰትን ለማስቀጠል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸውም ያስረዳሉ። በመሆኑም የታችኛው የተፋሰሱ አገራት ግብፅ እና ሱዳን፣ የዓባይን ውሃ በብቸኝነት ካልተቆጣጠርነው በሚል እሳቤ ያልተገባ ስሞታ ከማቀረብ ይልቅ፤ ለራሳቸው ብሄራዊ ጥቅም ሲሉ አረንጓዴ ኢኒሼቲቭን በገንዘብ ጭምር በመደገፍ የውሃ ፍሰትን ዘላቂነት በማረጋገጥ ላይ በትብብር መንፈስ ቢሰሩ ይመራጣል ሲሉ ዲፕሎማት አፈወርቅ ይመክራሉ። ዲፕሎማት አፈወርቅ በጽሑፋቸው ማጠቃለያ አንኳር ሃሳብ እንዳስገነዘቡት ከዚህም ባሻገር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የፓርቲዎች ኮንፈረንስ (CoP) እና ሌሎች ማህበረሰቦች ተመሳሳይ መርሃ ግብር በሌሎች የቀጣናው አካባቢዎች እንዲደግሙ ለማነሳሳት ሰብዓዊነትን እንደ አንድ የጋራ ጥቅም እንዲያገለግል በተነሳሽነት መደገፍ አለባቸው። የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ የተራቆቱ አካባቢዎችን በማሻሻል ካስመዘገበው ስኬት ባለፈ ዋነኛ ዓላማው የሆነውን የኢትዮጵያ ህዝቦችን አንድነት በማጠናከር የአፍሪካ አረንጓዴ ቀበቶ ኢኒሼቲቭን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህም ባሻገር የካርቦን ልቀትን በ2030 ዜሮ ለማድረግ ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት የኤሌክትሪክ ኃይልን ሙሉ በሙሉ ከውሃ፣ ከነፋስ፣ ከፀሐይና ከእንፏሎት ወዘተ. ለማመንጨት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው። ኢትዮጵያ የቀጣናዊ ውህደቱ ዋና አንቀሳቃሽ እንደመሆኗ መጠን የኤሌክትሪክ የመሰረተ ልማት አውታርን ከጅቡቲ፣ ሱዳንና ኬንያ ጋር በማገናኘት ንፁህ ኃይሏን በማጋራት ከታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር እየሰራች ነው። እንዲሁም የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርን እና የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን ከብክለት የፀዳ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ አካል በማድረግ በኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሰራ አድርጓል።
የሽግግር ፍትሕ - የአያሌ ችግሮች መፍቻ
May 11, 2024 4433
የሽግግር ፍትሕ - የአያሌ ችግሮች መፍቻ (ሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በደል፣ ግፍ እና መሠረታዊ የመብት ጥሰቶች ተከስተዋል። የቁርሾ እና የቂም በቀል አዙሪት፣ የተበዳይነት እና የብሶት ትርክት በሀገሪቱ ዋነኛው የፖለቲካ ማጠንጠኛ የሆነበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። በደሎችን በማከም ሰላምና ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር መገንባትን ባለመ መልኩ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ለመተግበር ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የነበረውን ኢ-ፍትሃዊነት በፍትሕ፣ በእርቅና በይቅርታ መፍትሔ ለመስጠት የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ ሰነድ ዝግጅት በጥር ወር 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደኅንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በቅርቡ ያወጣው መግለጫ እንዳመላከተውም በኢትዮጵያ የበዳይ ተበዳይ አዙሪት ለመስበር የሽግግር ፍትሕ አንዱ ተመራጭ ሥልት ነው። ከአንድ ዓመት በላይ በዝግጅት ሂደት የቆየው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን ተከትሎ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብርም ተካሂዷል። የሽግግር ፍትሕ ታሪካዊ ዳራ የሽግግር ፍትሕ ዘርፍ ታሪካዊ መነሻ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1939 እስከ 1945 ከተደረገው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በአውሮፓ ፍትሕን ለማስፈን የተደረገ እንቅስቃሴ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1945 በጀርመን ኑረንበርግ የተሰየመ ዓለም አቀፍ ወታደራዊ ችሎት የተቋቋመ ሲሆን፤ ችሎቱ የተቋቋመው ዋና የናዚ መሪዎችን የፍርድ ሂደት ለመከታተልና ውሳኔ ለመስጠት ነው። በወቅቱ የናዚ መሪዎች በጦር ወንጀል፣ በሰብዓዊ ጥፋት እንዲሁም ወንጀሎችን ለመፈጸም በማሴር ተከሰዋል። ለአንድ ዓመት የቆየው የፍርድ ሂደትም በናዚ ሰዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ “ታሪካዊ” እና “ታላቅ” የሚል አድናቆትን አግኝቶ ነበር። የጦርነቱም የፍርዱም ተሳታፊዎች “ጨርሶ አይደገምም፤ Never again” የሚል ቃል ገብተው ነበር። በወቅቱ የጃፓን ወታደሮች የፍርድ ሂደት የሚታይበት የቶኪዮ ወታደራዊ ችሎትም ተቋቁሞ ነበር። በኑረንበርግ እና በቶኪዮ የነበሩት ወታደራዊ ችሎቶች ለሽግግር ፍትሕ እሳቤ መጠንሰስ ቁንጮ ማሳያዎች እንደሆኑ ይነገራል። በግሪክ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1945 እና በአርጀንቲና እ.አ.አ በ1983 የቀድሞ ወታደራዊ መንግሥት አባላት የፍርድ ሥርዓትም እንደ ሽግግር ፍትሕ ማሳያ ይጠቀሳሉ። የሽግግር ፍትሕ ዘርፍ እ.አ.አ ከ1980 በኋላ ያለው እሳቤና ተፈጻሚነቱ እያደገ የመጣ ሲሆን፤ እ.አ.አ በ1970 እና 1980ዎቹ ትኩረቱን የሰብዓዊ መብቶች መከበርና መጠበቅ ላይ አድርጓል። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሽግግር ፍትሕ ተቀባይነት እንዲያገኝና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕጎችና ስምምነቶች እንዲቋቋሙ በር ከፍቷል። በወቅቱ የሽግግር ፍትሕ እሳቤ ማዕከል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በፖለቲካ ሽግግር እንዲሁም በሕግና ወንጀል ፍርዶች ወቅት እንዴት ይቃኛሉ? እንዴት ይታያሉ? የሚለው ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ የሽግግር ፍትሕን አስመልክቶ የነበሩ ክርክሮች “ፍትሕ” ለሚለው ዓለም አቀፍ ጽንሰ-ሀሳብ መዳበርና መስፋት አስተዋጽዖ እንደነበረውም ይጠቀሳል። በሂደት የሽግግር ፍትሕ እየሰፋ በተለይም እ.አ.አ በ1980ዎቹ መጨረሻና በ1990 መግቢያ ላይ ዴሞክራሲና የዴሞክራሲ እሳቤዎች ዓለምን እየተቆጣጠሩና ተጽዕኗቸው እየጨመረ ሲመጣ የሽግግር ፍትሕ ከዴሞክራሲ አንጻር መቃኘት ጀመረ። በዚህም የሽግግር ፍትሕ የዴሞክራሲ እሳቤ አንዱ የጥናት ዘርፍ መሆን የቻለ ሲሆን፤ የሽግግር ፍትሕ “ጠባብ ከነበሩ የሕግ ጥያቄዎች ወደ የተረጋጉ የዴሞክራሲ ተቋማት መገንባትና የሲቪክ ተቋማት እንደገና ማደስ ወደሚል ሰፊ የፖለቲካ አመክንዮዎች አድማሱን አስፍቷል” ሲሉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። የሽግግር ፍትሕን ማዕቀፍ ከፖለቲካዊ ሂደቶችና ዴሞክራሲያዊ ለውጦች ጋር ያቆራኙ አገራት ከአምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር ምቹ መደላድል እንደፈጠረላቸው በዘርፉ ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች ይጠቅሳሉ። በዴሞክራሲያዊ ሂደት ውስጥ ያሉ የሽግግር ፍትሕ ፈተናዎች በርካታ ናቸው የሚሉት ምሁራን የዴሞክራሲ ሂደቱ ሳይጓተት ላለፉ ቁርሾዎች መፍትሔ መስጠት፣ ግጭቶችን የሚፈታ የዳኝነት ወይም የሦስተኛ ወገን የፍትሕ ሥርዓት መዘርጋት፣ የካሳ ክፍያዎችን መፈጸም፣ ያልሻሩ ቁስሎች እንዲሽሩና የባህል እርቆችን የተሟላ ማድረግ ከፈተናዎቹ መካከል የሚጠቀሱ እንደሆኑ ያነሳሉ። ካናዳ፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አገራቱን የቆረቆሩ ነባር ዜጎች ይደርስባቸው ለነበረው ጭቆና ምላሽ ለመስጠት የሽግግር ፍትሕን ተጠቅመውበታል። በአሜሪካም “የዘር ፍትሕ Racial justice” አስመልክቶ በሚደረጉ ውይይቶችና ክርክሮች የሽግግር ፍትሕ ቋንቋና ሀሳብ ደጋግሞ ይነሳ ነበር። የሽግግር ፍትሕ አንድ የወለደው ሀሳብ ቢኖር የ”እውነት ፈላጊ” ኮሚሽኖች (Truth commissions) ማቋቋም ነው። በአርጀንቲና እ.አ.አ በ1983፣ በቺሊ እ.አ.አ በ1990 እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ እ.አ.አ በ1995 የ”እውነትን አፈላላጊ” ኮሚሽኖች ተቋቁመዋል። ኮሚሽኖቹ በላቲን አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ እስያና ምስራቅ አውሮፓ እንደ ሽግግር ፍትሕ “ምልክት” ይታዩ የነበረ ሲሆን፤ ይሁንና በዩጎዝላቪያ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ቀጣናዊ የእውነት ፈላጊ ኮሚሽን ለማቋቋም ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም በፖለቲካ መሰናክሎች ምክንያት ሳይሳኩ መቅረታቸውን የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። የዴሞክራሲ ምሁራንና ባለሙያዎች አገራት በሽግግር ፍትሕ ማዕቀፎቻቸው ውስጥ ብሔራዊ ስትራቴጂዎቻቸውን ሲቀርጹ ያለፉ በደሎችንና ቁርሾዎችን እንደ አገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታና ባህርይ መፍታትን በዋናነት ከግምት ውስጥ ሊያስገቡ እንደሚገባ ይመክራሉ። ይህ ቁርሾን የመፍታት ሂደት ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ ከሕግ ተጠያቂነት የማምለጥ ዝንባሌን ለማስቀረት፣ በዜጎችና መንግሥታት መካከል ያለውን ግንኙነት እንደገና ለማደስና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባት አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ይገልጻሉ። የሽግግር ፍትሕ ሰፊ የአስተሳሰብ ማዕቀፍ ዜጎች ሁሌም ኋላቸውን እያዩ ወይም ካለፉ ክስተቶች ጋር ከመጋፈጥ ወደፊት የተሻለ ነገር ይመጣል ብለው ተስፋ እንዲሰንቁ እንደሚያደርግም ይጠቅሳሉ። እ.አ.አ በ2001 በሽግግር ፍትሕ፣ እርቅና ርትዕ ላይ የሚሰራ “ዓለም አቀፍ የሽግግር ፍትሕ ማዕከል” የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም የተመሠረተ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ግብረ-ኃይል ተቋቁሟል። የሽግግር ፍትሕ በዘላቂ ልማት ግቦች መካከል ግብ 16 “የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አፋጣኝ የፍትሕ ጣልቃ-ገብነት እርምጃዎች በመውሰድ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማምጣት” የሚለውን ለማሳካት አጋዥ ነው። የሽግግር ፍትሕ ትርጓሜዎች እንደ ዓለም አቀፉ የሽግግር ፍትሕ ማዕከል ከሆነ የሽግግር ፍትሕ “ከግጭት የወጡ አገራት በመደበኛ የፍትሕ ሥርዓት በቂ ምላሽ ሊሰጡባቸው የማይችሏቸውን ከፍተኛ፣ የተደራጁና በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ምላሽ የሚሰጡባቸው መንገዶች ናቸው።” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሽግግር ፍትሕ ለፍትሕ ብቻ ትኩረት በማድረግ ፍትሃዊ የኃብትና አገልግሎት ክፍፍል ማድረግ ወይም ለኢ-ፍትሃዊነት ምላሽ መስጠት ሳይሆን “ከአቅም በላይ ለሆኑና ልዩ ባህርይ ላላቸው ፈተናዎች ምላሽ የሚሰጥበት አካሄድና መንገድ ነው” ሲል ይገልፀዋል። የወንጀል ቅጣቶች፣ የእውነት ፈላጊ ኮሚሽኖች መቋቋም፣ ካሳ መክፈል፣ ሰዎች በግጭት ወቅት ያጡትን ወይም የተሰረቁትን ንብረትና ኃብት መተካት፣ በጅምላ መቃብር ውስጥ የተቀበሩ ሰዎች በክብር ለየብቻ እንዲቀበሩ ማድረግ፣ ይቅርታና ምህረት ማድረግ፣ መታሰቢያዎችን መገንባት፣ በግጭቶቹ ላይ ሳይንሳዊ ምርምር በማድረግ ግጭቶችና በደሎች እንዳይደገሙ በሚያደርግ መልኩ ትምህርቶችን ማስተማርና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ምላሽ የሚሰጡ ተቋማዊ የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ በሽግግር ፍትሕ ውስጥ ከሚካተቱ ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል። በሌላ በኩል በሽግግር ፍትሕ በፖለቲካዊ ሽግግር ውስጥ የሕግ የበላይነትን ማስፈን በዚህም ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት የሚደረግ ጉዞን ማፋጠን ያስፈልጋል የሚሉ ምሁራንም አሉ። የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት በደሎችን በማከም ሰላምና ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር መገንባትን ባለመ መልኩ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ለመተግበር ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ያሉ አለመግባባትና ግጭቶችን ለመፍታት የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ትክክለኛ አማራጭ መሆኑ ይገለጻል። የሽግግር ፍትሕ በሕዝቦች መካከል መተማመን እና ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር ሁሉንም የሚያሳትፍ፣ የሕግ ተጠያቂነት፣ ፍትሕ፣ እርቅና ካሳን ጭምር ታሳቢ የሚያደርግ እንደሆነ ተጠቅሷል። በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ መዘርጋት አስፈላጊነት ታምኖበት ሁሉን አቀፍ አካታችና ተመጋጋቢ የሆነ ፖሊሲ ለማዘጋጀት ላለፉት ጊዜያት ሰፊ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ኢትዮጵያ በዘመናት ሂደት ያጋጠሟትን ፈተናዎች በዘላቂነት ለመፍታት የሽግግር ፍትሕ ሂደት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ታምኖበታል። የሽግግር ፍትሕ ሰላምና ፍትሕን አስተሳስሮ የመሄድ ጉዳይ እንደሆነና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የማይተካ ሚና እንዳለው እንዲሁም በሂደቱ የይቅርታና ምህረት ጉዳዮችን እንደሚያቅፍ የሕግ ምሁራን ይገልጻሉ። በጦርነት የተጎዱ አካላትን ማቋቋም በሽግግር ፍትሕ እንደሚታይና በዚህም ዘላቂ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ማምጣት እንደሚቻል ያስረዳሉ። የተለያዩ አገራት ከነበሩባቸው በርካታ ቀውሶች ወጥተው ወደ ሰላም የመጡበት ሂደት መሆኑን በማውሳት የዘርፉ ባለሙያዎችን ባካተተ መልኩ በቁርጠኝነት ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ ምክረ-ሀሳባቸውን ያስቀምጣሉ። የሽግግር ፍትሕ ስልቶች ያለፉ በደሎችን፣ ቁርሾዎችን፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ አለመግባባትና ጥርጣሬን በአግባቡ በመፍታት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ምቹ መደላድል መፍጠር ዋነኛ ዓላማው ነው። ቀደም ሲል ከነበረ አለመግባባት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲላቀቅ በማድረግ ቀጣይነት ያለው አብሮነትና መተማመን መፍጠር የሚያስችል የፍትሕ ማስገኛ ስልትም ነው። አፍሪካን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ አገራት በሽግግር ፍትሕ ስልቶች አልፈው ከነበሩበት ውስብስብ ችግር በመውጣት የተሻለ ሰላም፣ መረጋጋት እና የሕግ የበላይነት ማስፈን ችለዋል። ለአብነትም ኮሎምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዩጋንዳና ሴራሊዮን ካለፉበት አስከፊ የእርስ በርስ ግጭትና አፓርታይድ ሥርዓት በሽግግር ፍትሕ መፍትሔ በመስጠት የተሻለ ሀገር መገንባት መቻላቸው በማሳያነት የሚቀርብ ነው። በኢትዮጵያም በመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት ሊፈቱ የማይችሉ የረዥም ዓመታት ጥፋቶችን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑ ታምኖ እየተሰራበት ይገኛል። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅት በኢትዮጵያ የነበረውን ኢ-ፍትሃዊነት በፍትሕ፣ በእርቅና በይቅርታ መፍትሔ ለመስጠት የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ ሰነድ ዝግጅት በጥር ወር 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ የሚያዘጋጅና ከተለያዩ ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ምህረት መስጠትን፣ የሕግና ተቋማት ማሻሻያ ማድረግን፣ ማካካሻ መስጠትን፣ እውነትን ማፈላለግን እና ተጠያቂነትን ማስፈንም የሽግግር ፍትሕ ሰነዱ ዓላማ አድርጎ የሽግግር ፍትሕ የደረሰበትን ደረጃ ባገናዘበ መልኩ ፖሊሲው ሲዘጋጅ ቆይቷል። ሰላምን በማረጋገጥ፤ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የማኅበረሰብን ትስስር መመለስ ያስፈልጋል የሚለው ጉዳይ ከፖሊሲው የትኩረት አቅጣጫ መካከል የሚጠቀስ ነው። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን በተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ከዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ ተቋማት ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በርካታ ውይይቶች ተደርገዋል። የፖሊሲው ዝግጅት የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ፣ ዓለም አቀፍ ልምድን መሠረት ያደረገ ነው። በቅድመ-ፖሊሲ ማርቀቅ ሂደቱ ብቻ 60 የክልል እና 20 ሀገራዊ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኮች እንደተካሄዱበት ተልጿል። በተጨማሪም መንግሥት የሽግግር ፍትሕ አማራጮችን አስመልክቶ ሕዝባዊ ውይይቶችን በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች አድርጓል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ጸድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል። በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርክቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች መደረጋቸውን አስታውሷል። ሆኖም እነዚህ አሠራሮች በእውነት፣ በዕርቅ፣ በምህረት፣ በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብዓዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም ብሏል። ስለሆነም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡንና ምክር ቤቱ ግብዓቶችን በማከል ፖሊሲው ከጸደቀበት ቀን እንስቶ ሥራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል። የባለድርሻ አካላት ሚና በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲተገበር የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ወሳኝ መሆኑ ዕሙን ነው። በፖሊሲው እንደተመላከተውም የሽግግር ፍትሕ ሥራዎችን ተግባራዊ የሚያደርጉ ተቋማት በርከት ያሉ ናቸው፡፡ በዚህ ሂደት የመንግሥት አካላት ሚናቸው ከፍተኛ ሲሆን ለአብነትም የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ሰላም ሚኒስቴር፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው። ለምሳሌ የፍትሕ ሚኒስቴር የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓቱን በበላይነት የመምራት እና የማስተባበር ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲፈፀም ለማድረግ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንፃር ትልቅ የቤት ሥራ አለበት፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴርም የአገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት የማስተዳደር፣ የፌዴራል መንግሥት በጀትን የማዘጋጀት፣ የተፈቀደ በጀትን ለሚመለከተው አካል የመላክ፣ አፈጻጸሙን የመገምገም እና የመሳሰሉት ተግባራት እና ኃላፊነቶች ያሉት መሥሪያ ቤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ትግበራ ጋር በተያያዘ የሚኖሩት ተግባርና ኃላፊነቶች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የሽግግር ፍትሕ ሥርዓቱ አተገባበር በሕዝብ ተቀባይነት እንዲኖረው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማኅበረሰቡን የማሳወቅ እና የማንቃት ሥራ እንዲሰሩ እንዲሁም በሽግግር ፍትሕ አተገባበር የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስተባበር ይጠበቅበታል። የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋማት የተለያዩ የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚቋቋሙ ተቋማት ወይም አደረጃጀቶች ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ የሰላም እና የፀጥታ ችግር እንዳይገጥማቸው አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ረገድ ሚናቸው የጎላ ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የተለያዩ የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሕጎችን ቅድሚያ እና ትኩረት በመስጠት ከማጽደቅ፣ ለሽግግር ፍትሕ ሥርዓቱ ትግበራ የሚቋቋሙ ተቋማት ኮሚሽነሮች እና ዳኞች ሹመት ግልፅ በሆነ እና የሕዝብን ተሳትፎ በሚያረጋግጥ ሂደት እንዲከናወን ከማድረግ ወዘተ አኳያ ኃላፊነቱ ከፍተኛ ነው። የሰላም ሚኒስቴር በበኩሉ የሽግግር ፍትሕ አተገባበርን አስመልክቶ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር እና አዎንታዊ ሰላም እንዲገነባ ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአቅም ግንባታ ሥራ በመሥራት፣ የሽግግር ፍትሕ ዘላቂ ሰላምን ሊያመጣ በሚችል አግባብ በሁሉም ክልሎች ወጥ በሆነ መንገድ እየተተገበረ ስለመሆኑ በመከታተልና አስፈላጊውንም ድጋፍ በማድረግ ረገድ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቀዋል። በአጠቃላይ ከሽግግር ፍትሕ ሥርዓት አተገባበር ጋር በተያያዘ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ሚና የሚኖራቸው የመንግሥት ተቋማት ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎችም አካላት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው። እነዚህ አካላት የሽግግር ፍትሕ ሂደት ትግበራው የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን ያከበረ፣ ተጎጂን ማዕከል ያደረገ እና የፖሊሲውን መርሆዎች ያከበረ መሆኑን በመከታተልና በመደገፍ፤ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ስለ ሽግግር ፍትሕ ሥርዓት እና ሂደት በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና የሽግግር ፍትሕ ሥርዓቱ አተገባበር በሕዝብ ተቀባይነት እንዲኖረው በማድረግ፤ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል። እንደ መውጫ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በቅርቡ ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት እንደተገለጸውም መንግሥት የተሟላና ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚያስችል የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ለማዘጋጀት አስቀድሞ የገለልተኛ ሙያተኞች ቡድን በማዋቀር ሲሰራ ቆይቷል። ከ80 በላይ ሕዝባዊ የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረኮች በማዘጋጀት ማኅበረሰቡ በስፋት ሃሳብ እንዲሰጥ በማድረግም የተገኙ ግብዓቶችን በፖሊሲው በማካተት እንዲፀድቅ መደረጉ ተገልጿል። የፖሊሲው አጠቃላይ ዓላማ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አውድ መሠረት ያደረገ፣ የተቀናጀ እና የተናበበ የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላም፣ ዕርቅ፣ የሕግ የበላይነት፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ የሚረጋገጥበትን መደላድል መፍጠር መሆኑ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል። የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲያመጣና ዜጎች ነገን በተስፋ እንዲጠብቁና በአገራቸው ላይ ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸው በተሟላ መልኩ መተግበር አለበት። ለዚህም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ ነው። የሽግግር ፍትሕ ሂደቱና አገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ካለችበት ችግር ወጥታ ወደ ቀጣዩ የእድገት ምዕራፍ እንድትሸጋገር ከማድረግ አኳያ እርስ በርስ የሚመጋገቡ ሲሆን፤ ከዚህ አንጻር ሁለቱ በሚጣጣሙባቸው አጀንዳዎችና ግቦች ላይ በጋራ በመሥራት ሁሉን አቀፍ ውጤት ማግኘትም ይቻላል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 17954
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 20911
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 11531
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል። “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 12980
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
መጣጥፍ
በኦሊምፒክ ስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ የተካተተው ብሬክ ዳንስ
Jul 29, 2024 489
በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ የኦሊምፒክ ውድድር በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶችን በማካተት ዘንድሮ ለ33ኛ ጊዜ በፈረንሳይ ከተማ ፓሪስ እየተከናወነ ይገኛል። ከዛሬ አራት ዓመት በፊት በጃፓን ቶኪዮ በተከናወነው ኦሊምፒክ ስድስት የስፖርት ዓይነቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ የተካተቱት ስፖርቶች፤ ካራቴ፣ ስኬትቦርዲንግ፣ ቤዝቦልና ሶፍትቦል፣ በገመድና ያለገመድ ግርግዳ መውጣት (Sport climbing) እና በውሃ ላይ መንሸራተት (Surfing) ናቸው። በፈረንሳይ እየተከናወነ በሚገኘው 33ኛው የበጋ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ "ብሬኪንግ" ወይም "ብሬክ ዳንስ" የሚባለው የዳንስ ዓይነት በኢሊምፒክ ጨዋታዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተካቷል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1970ዎቹ በብሮንክስ ጎዳናዎች ላይ የበቀለው ዳንስ፤ ለኒውዮርክ አፍሪካ አሜሪካዊ ማኅበረሰብ ምስጋና ይግባውና፤ በፓሪስ ኦሊምፒክ አንዱ ስፖርታዊ ውድድር ሆኖ ቀርቧል። ብሬክ ዳንስ ምንድነው? ብሬክ ዳንስ በአርባን ፖፕ፣ በሂፖፕና ራፕ በሚባሉ የሙዚቃ ዓይነቶች የሚሰራ የዳንስ እንቅስቃሴ ሲሆን አራት ዓይነት እንቅስቃሴዎች የሚደረጉበት ስልት ነው፡፡ "ቶፕ ሮክ" የሚባለው ደግሞ የመጀመሪያው ስልት ነው። በቶፕ ሮክ ዳንሰኛው ወይም ዳንሰኛዋ ቆመው በእግር እንቅስቃሴ ይጀምሩና፤ የማማሟቂያ እንቅስቃሴዎችን በማስከተል ወደ ሞቀ እንቅስቃሴ የሚገቡበት ነው። ሁለተኛው "ዳውን ሮክ" የሚባል ሲሆን፤ እጅና እግርን ወለል ላይ በማሳረፍ፤ ሰውነትን በተለያየ መንገድ እንዲተጣጠፍ በማድረግ፤ ፈጣን እንቅስቃሴ የሚደረግበት ስልት ነው። ሦስተኛው "ፓወር ሙቭ" የሚባለው የብሬክ ዳንስ ክፍል ሲሆን፤ በፍጥነት አክሮባት በመሥራት ዳንሰኞች ትርኢት የሚያሳዩበት ነው። አራተኛውና የመጨረሻው የብሬክ ዳንስ ክፍል ደግሞ፤ "ፍሪዝ" የሚባለውና እየደነሱ በመሀል ቆም በማለት መልሶ ወደ ዳንስ እንቅስቃሴ የሚገባበት ነው። የብሬክ ዳንስ ውድድር አጀማመርና ወደ ኦሊምሊክ ያደረገው ጉዞ የመጀመሪያው የብሬክ ዳንስ ውድድር የተከናወነው፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1990 አሜሪካን ውስጥ ነበር። በተለይ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2004 ጀምሮ፤ "ሬድ ቡል ቢሲ ዋን" የሚባለውና በሁለቱም ፆታዎች የሚከናወነው ዓመታዊ የብሬክ ዳንስ ሻምፒዮና፤ ስመጥር የዘርፉ ውድድር ነው። ዓለም አቀፉ የዳንስ ስፖርት ፌዴሬሽን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2018 ፤ የብሬክ ዳንስን በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተደረገው የበጋ የወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ አስተዋውቆ ነበር። አሁን ላይ በተጀመረው 33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ ውድድር ደግሞ፤ ብሬክ ዳንስ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ተካቶ ውድድር ይደረግበታል። ውድድሩም ፓሪስ በሚገኘው "ላኮንኮርድ" ከሚባለው የኦሊምፒክና፣ የፓራ ኦሊምፒክ መንደር 5 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ቦታ ላይ ይከናወናል። በሁለቱም ፆታዎች በሚደረገው የብሬክ ዳንስ ውድድር አንድ ሀገር በወንድም በሴትም በተመሳሳይ 16 ተወዳዳሪዎችን የሚያሰልፍ ሲሆን፤ ተወዳዳሪዎች ዲጄዎች በሚያጫውቷቸው ሙዚቃዎች ታጅበው ውድድሩን ያከናውናሉ። 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከሐምሌ 19 ጀምሮ በፈረንሳይ ፓሪስ እየተከናወነ ሲሆን እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይከናወናል። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 206 ሀገራት እየተሳተፉ ሲሆን፤ 10 ሺህ 714 ስፖርተኞች በ32 የስፖርት ዓይነቶች ውድድራቸውን እያደረጉ ነው።
የዘንድሮው የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር ልዩ አጋጣሚ
Jul 2, 2024 3163
በይስሐቅ ቀለመወርቅ የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1916 በአርጀንቲና አስተናጋጅነት ተጀመረ። ዘንድሮ ደግሞ 48ተኛው የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር በአሜሪካን አዘጋጅነት እየተደረገ ይገኛል። በውድድሩ 16 አሰልጣኞች የተለያየ ሀገራትን ብሔራዊ ቡድን ይዘው የሚያሰለጥኑ ሲሆን፤ ከነዚህ ሰባቱ አርጀንቲናውያን አሰልጣኞች መሆናቸው የዘንድሮውን የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር ልዩ ያደርገዋል። በራሳቸው ሀገር ተወላጆች እየሰለጠኑ በኮፓ አሜሪካው እየተሳተፉ የሚገኙ ሀገራትን ስንመለከት ብራዚል በብራዚላዊው አሰልጣኝ ዶሪቫል ሲልቬስትር፤ ሜክሲኮ በሜክሲኳዊው ጃሚን ሎዛኖ፣ አዘጋጇ ሀገር አሜሪካ ደግሞ በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ግሬግ ማቲውና አርጀንቲና ደግሞ በአርጀንቲናዊው ሊዮኔል ስካሎኒ እየሰለጠኑ ይገኛሉ። ፓናማ በዴንማርካዊው አሰልጣኝ ቶማስ ክርስቲያንሰን፤ ጃማይካ በአዬስላንዳዊው አሰልጣኝ ሂመር ሃልግሪምሰን፤ ካናዳ በአሜሪካዊው ጂሲ አለን፤ኢኳዶር በስፔናዊው ፍሊክስ ሳንቼዝ ፤ቦሊቪያ በብራዚላዊው አንቶኒዮ ካርሎስ እና ፔሩ በኡራጋዊው አሰልጣኝ በጆርጅ ፎሳቴ እየሰለጠኑ በኮፓ አሜሪካ በመሳተፍ ላይ ናቸው። በዘንድሮው ኮፓ አሜሪካ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝን ጨምሮ ሰባት አርጀንቲናውያን አሰልጣኞች ሰባት ሀገራትን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። ለመሆኑ እነዚህ አርጀንቲናውያን አሰልጣኞች እነማናቸው? ሊዮኔል ስካሎኒ፡- ይህ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2018 እያሰለጠነ የሚገኝ ሲሆን በ2021 የኮፓ አሜሪካን፤ በ2022 ደግሞ የዓለም ዋንጫን ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር አሸንፏል። ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን ይዞ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን አርጀንቲና በምድብ ጨዋታዎቿ ካናዳ፣ ቺሊንና ፔሩን አሸንፋ ወደ ሩብ ፍፃሜ እንድትገባ አስችሏታል። ማርሴሎ ቤልሳ፡- የ68 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋው አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የኡራጋይ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2023 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ይገኛሉ። ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የኡራጋይ ብሔራዊ ቡድን የተሻለ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ያገዙት ሲሆን ፓናማን፣ ቦሊቪያንና አዘጋጇ ሀገር አሜሪካንን አሸንፎ ሩብ ፍፃሜ እንዲቀላቀል አስችለውታል። ፈርናንዶ ባቲስታ፡- በ53 ዓመት ዕድሜው ላይ የሚገኘው ይህ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የቬንዙዌላ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2023 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ይገኛል። ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የቬንዙዌላን ብሔራዊ ቡድንን ይዞ እየተሳተፈ ሲሆን፤ ቬንዙዌላ በምድብ ጨዋታዎቿ ኢኳዶርን፣ ሜክሲኮና ጃማይካን አሸንፋ ሩብ ፍፃሜ እንድትገባ አስችሏታል። ኔስተር ሎሬንዞ ፡- የ58 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የኮሎምቢያ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2022 ጀምሮ እያሰለጠነ ይገኛል። ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የኮሎምቢያን ብሔራዊ ቡድንን ይዞ ፓራጓይና ኮስታሪካን በምድብ ጨዋታ በማሸነፍ ኮሎምቢያ ሩብ ፍፃሜ እንድትገባ ያደረገ ሲሆን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ከብራዚል ጋር ያደርጋል። ሪካርዶ ጋርሲያ፡- የ66 ዓመቱ አንጋፋ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ ሪካርዶ ጋርሲያ የቺሊ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2024 ጀምሮ እያሰለጠኑ ይገኛሉ። ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የቺሊ ብሔራዊ ቡድንን ይዘው በሚፈልጉት ርቀት መጓዝ አልቻሉም። በምድብ ጨዋታቸው ከካናዳና ፔሩ ጋር በተመሳሳይ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት አጠናቀውና በአርጀንቲና 1 ለ 0 ተሸንፈው ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል። ዳንኤል ጋርኔሮ፡- የ55 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የፓራጓይ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2024 ጀምሮ እያሰለጠነ ይገኛል። ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የፓራጓይ ብሔራዊ ቡድንን ይዞ እተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን፤ በሚፈለገው ርቀት መጓዝ አልቻለም። ከኮሎምቢያና ብራዚል ጋር ባደረጋቸው ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ሽንፈትን በማስተናገዱ፤ከኮስታሪካ ጋር የሚያደርገው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ እየቀረው ከውድድሩ ውጪ ሆኗል። ጉስታቮ አልፋሮ፡- የ61 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ የኮስታሪካ ብሔራዊ ቡድንን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2023 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ይገኛሉ። ዘንድሮም በኮፓ አሜሪካ ውድድር የኮስታሪካን ብሔራዊ ቡድንን ይዘው በምድብ ጨዋታቸው በኮሎምቢያ ተሸንፈው ከብራዚል ጋር አቻ ተለያይተዋል። ወደ ሩብ ፍፃሜው ለማለፍ ከፓራጓይ ጋር የሚደርጉትን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ማሸነፍና የኮሎምቢያና የብራዚልን የጨዋታ ውጤት መጠበቅ ግድ ይላቸዋል። በኮፓ አሜሪካ የዋንጫ ውድድር አርጀንቲና፣ ካናዳ፣ ቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር፣ ኡራጋይ፣ ፓናማና ኮሎምቢያ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ ቡድኖች ናቸው። ኮሎምቢያ ከብራዚል፤ ኮስታሪካ ከፓራጓይ ከሌሊቱ 10 ሰዓት በሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ሩብ ፍፃሜ የሚገባው ቀሪ አንድ ቡድን የሚለይ ይሆናል። በዘንድሮው የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ውድድር ሰባት አርጀንቲናውያን አሰልጣኞች ሰባት ሀገራትን እያሰለጠኑ እየተፋለሙበት ያለ ልዩ አጋጣሚ ፈጥሯል።