ስለ እኛ - ኢዜአ አማርኛ
አድራሻ
ኢሜል:
info@ena.et
የቢሮ ስልክ:
0111550011/0111117059
ፋክስ:
0111559931/0111551609
የፖስታ ሳጥን ቁጥር:
530
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
አዲስ አበባ ሰሜን ሆቴል አካባቢ
ስለእኛ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በ1934 ዓ.ም የተመሰረተና ላለፉት 82 ዓመታት ከመላው ኢትዮጵያ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በማደራጀትና በማጠናቀር ዘገባዎቹን በመገናኛ ብዙኃን፣ በድረ-ገጹና ማህበራዊ ትስስር ገጾቹ በኩል ለህብረተሰቡ ሲያሰራጭ የቆየና የዳበረ ልምድ ያለው ተቋም ነው። አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ ባሻገር በመላ አገሪቱ ካሉት ከ38 በላይ ቅርንጫፎቹ በየእለቱ አካባቢዎቹን የተመለከቱ ዘገባዎችን፣ የቴሌቭዥንና የሬዲዮ ፕሮግራሞችን፣ ዘጋቢ ፊልሞችን እያዘጋጀ ያሰራጫል ፤ በተጨማሪም በየሁለት ወሩ በሚያሳትመው ነጋሪ መጽሔት ወቅታዊ ሃገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን የዳሰሱ መረጃዎችን ተደራሽ እያደረገ ይገኛል።
በስድስት የአገር ውስጥ እና የውጭ ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግሪኛ፣ አንግሊዝኛ፣ አረብኛና ፈረንሣይኛ ዜና እና ዜና ነክ ዘገባዎችን በማዘጋጀት ያሰራጫል።
ኢዜአ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ተደራሽነት የበለጠ ለማስፋትና ተቋማዊ እድገቱን ለማፋጠን እንዲያስችለው ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሆኖ በ2011 ዓ.ም እንደገና እንዲዋቀር ተደርጓል።
ኢትዮጵያ የምታከናውናቸውን የተለያዩ ተግባራት የተመለከቱ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በማደራጀትና በመተንተን ዜና እና ዜና ነክ ዘገባዎችን እንዲሁም ፕሮግራሞችን በአገር ውስጥና በውጭ አገር ማሰራጨት፤ የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚመለከቱ ዓለምአቀፍ ጉዳዮችን መዘገብ፤ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች በአገር ውስጥና በውጭ አገር ዋነኛ የዜና ምንጭ መሆን፤ የአገሪቱን ገጽታ መገንባት፤ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የህዝብ አስተያየት ጥናት ማካሄድ እንዲሁም ዋና ዋና ኹነቶችንና ክስተቶችን በፅሁፍ፣ በድምጽና በምስል ቀርፆና አደራጅቶ ማስቀመጥ ዋነኛ ዓላማዎቻችን ናቸው።
የስፖት፣ ፕሮግራም እና ዘጋቢ ፊልሞች ዝግጅት፣ የመገናኛ ብዙህንና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት የሚያስችሉ ስልጠናዎችን፣ የህትመት አገልግሎትና የህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን እንዲሁም ተግባራትን ያከናውናል። ከእነዚህ መካከልም፡-
ኢዜአ ለረጅም ዓመታት ያካበተውን ልምድ በመጠቀም ከዜና እና ዜና ነክ ዘገባዎች ባሻገር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ለደንበኞቹ በጥራት ይሠራል።
• የቴሌቪዥንና ሬዲዮ ፕሮግራሞች፣ ዘጋቢ ፊልሞች፣ የማስታወቂያ ክሊፖች፣ አጫጭር የመልዕክት ማስተላለፊያ ሥራዎችን (ስፖቶች)፤
• የኹነቶች ዝግጅት /የምክክር መድረኮች፣ የፓናል ውይይቶች፣ ቶክሾው …/፤
• የህትመት ሥራዎች /የመጽሔት፣ ዓመታዊ መጽሐፍ፣ የተቋማት ፕሮፋይል፣ ፎቶ መጽሔት …/
• የህዝብ አስተያየት እና የደንበኞች እርካታ ደረጃ ጥናቶች፤
• የእለት ከእለት የመገናኛ ብዙሃን የይዘት ሥራዎች ክትትል (media monitoring service) እና ዘርፍ ተኮር የመገናኛ ብዙሃን የይዘት ሥራዎች፣ የተቋማት ሪፖርቶችና ጥናቶች ክትትል (cluster or sector based monitoring service)፤
• የድምጽና ምስል ቀረጻና ቅንብር አገልግሎት፤
• ከክምችት የተንቀሳቃሽ ምስል፣ የፎቶና የድምጽ አቅርቦት፤
• የስቱዲዮ አገልግሎት ይገኙበታል።
ኢዜአ የሚሰጣቸውን የይዘት ሥራዎችና ሌሎች አገልግሎቶች የጥራት ደረጃ ለማሻሻል እና ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር ለማዘመን በሚያደርገው ጥረት አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ ሦስት የቴሌቪዥን እና አራት የሬዲዮ ስቱዲዮዎችን የያዘ ህንጻ በመገንባት ወደ ሥራ ማስገባት ችሏል። ከዚህም በተጨማሪ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ጥራትና ፍጥነት ለማረጋገጥም የሚያስችሉ ዘመናዊ የስቱዲዮ፣ የቀረጻ፣ የኤዲቲንግ እና የቀጥታ ማሳረጫ መሣሪያዎች ባለቤትም ነው።
ተልዕኳችን
በኢትዮጵያና በህዝቦቿ ጥቅም ላይ ያተኮሩ አገራዊና ዓለምአቀፍ ዜና እና ዜና ነክ ዘገባዎችን እንዲሁም ፕሮግራሞችን በማሰራጨት በአገር ውስጥና በውጭ ዋነኛ የዜና ምንጭ በመሆን ብሔራዊ መግባባት መፍጠርና አገራዊ ገጽታን መገንባት ነው።
እሴቶቻችን
• ትክክለኛነት (Accuracy)
• ፍትሀዊነት (Fairness)
• አክብሮት (Respect)
• ብዝሐነት (Diversity)
• ቁርጠኝነት (Commitment)
• ጥራት (Quality Service)
• ፍጥነት (Timeliness)
• ተጠያቂነት (Accountability)
ራዕያችን
በአፍሪካ ተምሳሌት፣ አስተማማኝና ተጽዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ መሆን ነው።