በኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ላይ ተደረሰ - ኢዜአ አማርኛ
በኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ላይ ተደረሰ
አዲስ አበባ ፤ ታኅሣስ 14/2016 (ኢዜአ) በኮፕ28 ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ላይ መደረሱ ይፋ ተደረገ።
የኮፕ28 ፕሬዚዳንት ሱልጣን አሕመድ አል ጃባር እንዳስታወቁት የተመድ የአየር ንበረት ለውጥ ጉባኤ ተሳታፊዎች “ታሪካዊ ስምምነት” ላይ ደረሰዋል።
የተደረሰው ስምምነት ከዚህ ቀደሞቹ የተሻለ፣ ስህተቶችን ያረመና ለተግባራዊነቱ ሁሉም አጽንኦት የሰጡበት ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ ።
በዚህም ስምምነት የአየር ንበረት ለውጥን ለመከላከል የሚያስችሉ የገንዘብ፣ የፖሊሲና ሰትራቴጂ ቅየሳዎች መካተታቸውንም ተናግረዋል።
የታዳሽ ኃይል ተግባራትን ለማከናውን የሚያስችሉ ማዕቀፎች በስምምነቱ ከተካተቱ አንኳር ጉዳዮች አንዱ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ መናገራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ኢትዮጵያም በኮፕ 28 ጉበኤ የአየር ጠባይ ለውጥን ለመከላከል እየከወነች ያለችውን ተጨባጭ መፍትኄ በአረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ ያቀረበች ሲሆን መካነ ርዕዩን የሀገራት መሪዎችና የአለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች መጎብኘታቸው ይታወሳል።