አዲሱ የጎርጎሮሳውያን ዓመት ስኬቶች የሚመዘገቡበት የብልፅግና ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ- የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ - ኢዜአ አማርኛ
አዲሱ የጎርጎሮሳውያን ዓመት ስኬቶች የሚመዘገቡበት የብልፅግና ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ- የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 22/2016 (ኢዜአ)፦ የጎርጎሮሳውያን አዲሱ ዓመት ስኬቶች የሚመዘገቡበት እና የብልፅግና ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ተናገሩ።
በጎርጎሮሳውያን የዘመን አቆጣጠር ቀመር የሚጠቀሙ ሀገራት አዲሱን የ2024 ዓመት በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እያከበሩ ይገኛል።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴም የጎርጎሮሳውያን 2024 አዲስ አመት ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕከት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም አዲሱ አመት አስደሳች የበአል ጊዜና ስኬታማ የብልፅግና ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።
የተለያዩ የአውሮፓ፣ አሜሪካና ኤዢያ ሀገራት አዲሱን የፈረንጆች ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ ይገኛሉ።