የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት በተጠናቀቀው የአውሮፓውያን አመት ስኬታማ ነበር

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 22/2016 (ኢዜአ)፡- በተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ አመት የኢትዮጵያና የቻይና ሁለንተናዊ ግንኙነት ስኬታማ ሆኖ ማለፉን ምሁራን ገለጹ። 

የሀገራቱ ግንኙነት በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ የማይለወጥ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ የእውቀትና የመረጃ ልውውጥ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ትብብር በአውሮፓውያኑ 2023 ከተከወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል መሆናቸውን ዥንዋ አስነብቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቻይና ቤጂንግ ባደረጉት ጉብኝት የሀገራቱ ግንኙነት በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ የማይለወጥበት ደረጃ ላይ መድረሱ ይፋ እንደተደረገ ያስታወሰው ዘገባው ኢትዮጵያና ቻይና በጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ አብረው ሊሰሩባቸው የሚያስችሉ በርካታ እድሎች እንዳሉ አስነብቧል።

ስለጉዳዩ አስተያየታቸውን የሰጡት በኢትዮጵያ የስትራቴጂክ ግንኙነት ተቋም የአለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ተመራማሪው መላኩ ሙሉአለም የአውሮፓውያኑ 2023 በኢትዮጵያና በቻይና ግንኙነት ሂደት ውስጥ “ታሪካዊ” ተብሎ ሊታወስ የሚችል መሆኑን ገልጸው አመቱ ከሚተባበሩባቸው የአለም ሰላምና ሁለንተናዊ ልማት ባሻገር የሃገራቱ ምጣኔሃብታዊ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር የደረሰበትን ደረጃ አመላካች ነው ብለዋል።

“አመቱ ኢትዮጵያና ቻይና በልማትና ዘርፎች ለመርዳት የገባችውን ቃል ማክበሯን በተግባር ያሳየችበት ነው” ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፐብሊክ ፖሊሲ ፕሮፌሰር ቆስጠንጢኖስ በርሄ ተስፋ ናቸው።

በተጠናቀቀው አመት ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን የቻይና ድጋፍ ጉልህ እንደነበር ያስነበበው ዘገባው፤ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ኢትዮጵያ በብሪክስ ቡድን የምታደርገው ተሳትፎ ከራሷ አልፎ ለአካባቢው ሃገራትም የሚተርፍ እንደሚሆን ተገልጿል። 

“በደቡብ-ደቡብ ትብር ውስጥ ኢትዮጵያ ወሳኝ የሚባል ድርሻ ስላላት አባል በሆነችበት የብሪክስ ቡድን ውስጥም ይሄንን ሚናዋን አጉልታ ታሳያለች” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ያስታወሰው ዘገባው ቻይና ከቴክኒክና ሙያ በባቡር መሰረተልማት እንዲሁም በሳተላይት ዘርፎች ለኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የምትሰጠውን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች አጠናክራ ትቀጥላለች ብሏል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም