አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ራምታኔ ላማምራ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሱዳን ያለውን ግጭት ለመፍታት በሱዳናውያን የሚመራና በአፍሪካ የተደገፈ የሰላም ሒደት አስፈላጊነት ላይ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡