የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመሪነት ሚናው ፡- - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመሪነት ሚናው ፡-
75 ዓመታትን በስኬት የተጓዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚው የአቬዬሽን ግሩፕ ነው፤
አየር መንገዱ 63 የአፍሪካ ከተሞችን ጨምሮ በየቀኑ ወደ ተለያዩ የአለም ክፍሎች በርካታ በረራዎችን ያደርጋል፣
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የትስስር ሚናው ከየትኛውም አየር መንገድ በላይ በአህጉሩ በረራ ያደርጋል፣
አየር መንገዱ በ5 አህጉሮች በ58 መዳረሻዎች በ100 አለም አቀፍ በረራዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፤
ይህም በቱሪስቶቸ ተመራጭ የሆኑትን የአፍሪካ ስፍራዎች አዲስ አበባ፣ ዛንዚባር፣ ኪሊማንጃሮና ሲሼልስን በዋናነት ያካተተ ነው፤
በዚህም ከስካይ ትራክስ ለ5 ዓመታት ተከታታይ ስኬት ያስመዘገበ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ በመባል ባለ 4 ኮከብ ሽልማት ተበርክቶለታል፤
በቀውስ ወቅት የላቀ የአመራር ስኬት ደግሞ በ2020 ሽልማት ተብርክቶለታል፤
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ፣ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእስያ ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በሌሎቸም የአለም ክፍሎች በምቹ በረራው እያገለገለ ይገኛል።