የአውሮፓ ዋንጫን ለበርካታ ጊዜ ያነሱት አገራት እነማን ናቸው?

(በሙሴ መለስ)

.. 1960 የመጀመሪያው የአውሮፓ ዋንጫ (በቀድሞ አጠራሩ ኢሮፒያን ኔሽንስ ካፕ) የጀመረበት ዓመት ነው።

 

በፈረንሳይ አስተናጋጅነት .. ከሐምሌ 6 እስከ 10 1960 በተካሄደው ውድድር የያኔዎቹ ሶቪየት ሕብረት፣ ቼኮዝሎቫኪያና ዩጎዝላቪያ ተሳትፈዋል።

 

ሶቪየት ሕብረት (በአሁኑ ስያሜዋ ሩሲያ)  በፍጻሜው ጨዋታ ዩጎዝላቪያን ስላቫ ሜትሬቬሊና ቪክቶር ፖንዴልኒክ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 1 በማሸነፍ ታሪካዊውን ዋንጫ አንስታለች።

 

64 ዓመት በፊት የተጀመረው የአውሮፓ ዋንጫ የዘንድሮውን ሳይጨምር 10 አገራት የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል።

 

ጀርመንና ስፔን በተመሳሳይ ሶስት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ስኬታማ የሆኑ አገራት ናቸው።

 

ምዕራብ አውሮፓዊቷ ጀርመን .. 1972 1980 እና 1996 አህጉራዊውን ክብር ከፍ አድርጋ አንስታለች።

 

ጀርመን ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ያነሳችው ምዕራብ ጀርመንና ምስራቅ ጀርመን ከመዋሃዳቸው በፊት ነበር።

 

ብሔራዊ ቡድኑ ካነሳቻው ዋንጫዎች በተጨማሪ 3 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሶ ተሸንፏል።

 

በደቡብ ምዕራብ አውሮፓ የምትገኘው ስፔን .. 1964 2008 እና 2012 በተካሄዱ ውድድሮች ዋንጫውን አንስታለች።

 

1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሳ ሽንፈትን አስተናግዳለች።

 

ስፔን በሁለት ተከታታይ የአውሮፓ ዋንጫዎች ዋንጫ ያነሳች ብቸኛ አገር ናት።

 

ጣልያንና ፈረንሳይ የአውሮፓ ዋንጫን ክብር ሁለቴ በመጎናጸፍ ይከተላሉ።

 

የደቡብ ማዕከላዊ አውሮፓዊቷ አገር ጣልያን .. 1968 እና 2020 ዋንጫውን አንስታለች።

 

16ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ባለቤት ጣልያን በጀርመን አስተናጋጅነት እየተደረገ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በጥሎ ማለፉ በስዊዘርላንድ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ መሆኗ የሚታወስ ነው።

 

ሰማያዊዎቹ በሚል ቅጽል ስም በሚጠራው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን .. 1984 እና 2000 የአውሮፓ ዋንጫን ወስዷል።

 

በተጨማሪም ጣልያን 2 ጊዜ እና ፈረንሳይ 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰው ሽንፈት አስተናግደዋል።

 

ፖርቹጋል፣ዴንማርክ፣ ኔዘርላንድ፣ግሪክ፣ ሩሲያና በቀድሞ አጠራሯ ቼኮዝሎቫኪያ( በአሁኑ ሰዓት ቼክ ሪፐብሊክና ስሎቫኪያ የሚጠሩት አገራት) በተመሳሳይ አንድ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫን አንስተዋል።

 

ሩሲያ 3 ጊዜ እንዲሁም ቼኮዝሎቫኪያና ፖርቹጋል በተመሳሳይ 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰው ተሸንፈዋል።  

 

ከዚህ ውጪ ዋንጫ ባያነሱም የቀድሞ ዩጎዝላቪያ 2 ቤልጂየምና እንግሊዝ በተመሳሳይ 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰዋል።

 

በጀርመን እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ አዲስ የዋንጫ ባለቤት ይገኝ ይሆን? ጥያቄው ሐምሌ 7 ቀን 2016 . ምላሽ ያገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም