በአፍሪካ ቀንድ በመጪዎቹ ሶስት ወራት ከወትሮው የተለየ የሙቀት መጠን ሊኖር ይችላል  

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2016(ኢዜአ)፦ በአፍሪካ ቀንድ በመጪዎቹ ሶስት ወራት ከወትሮው የተለየ የሙቀት መጠን ሊኖር ይችላል። 

የኢጋድን በይነ መረብ ዋቢ አድርጎ ዥንዋ እንደዘገበው፤ በአፍሪካ ቀንድ ከነሐሴ እስከ ጥቅምት ወራት ባለሉት  ጊዜያት  ከወትሮው የበለጠ የሙቀት መጠን ይኖረዋል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ ኤጀንሲ የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ከነሀሴ እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት ከወትሮው የበለጠ ሙቀት እንደሚኖረው ትናንት ማስታወቁን ዘገበው አመልክቷል።

የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ ማመልከቻ ማእከል ያስታወቀው፤ በአካባቢው በሚገኙ አንዳንድ ሀገራት የሙቀቱ መጠን እስከ 35 ዲግሪ ሴልሺየስ  ሊደርስ እንደሚችልም ነው የጠቆመው።  

ይሁን እንጂ ከሙቀቱ በተጋዳኝ በአንዳንድ አካባቢዎች ከወትሮው የተለየ ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ሊስተዋል እንደሚችል ድርጅቱ አስታውቋል። 

ሌሎች  እንደ ጂቡቲ ፡ ኬንያ ፡ ደቡብ ሱዳን ፡ ሱማሊያና ኡጋንዳ በመሳሰሉት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ከፍተኛ የሙቀት መጠን የሚመዘገቡባቸው እንደሆኑም ዥንዋ በዘገባው አመላክቷል።

በአካባቢው ከሚከሰተው ከፍተኛ ሙቀት በተጨማሪም ከነሀሴ እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት የአፍሪካ ቀንድ ምስራቃዊ ክፍሎች ከወትሮው የበለጠ ደረቅ የአየር ንብረት እንደሚያጋጥማቸው የማዕከሉ ትንበያ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም