ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጪው የአሜሪካ ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2016(ኢዜአ)፦የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቀጣዩ አመት በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ባይደን በመጪው አመት በሚካሄደው የአሜሪካ ምርጫ ከተቀናቃኛቸው ሪፕብሊካን ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ጋር የምረጡኝ ቅስቀሳ ፉክክር ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል።

ሆኖም ዛሬ አመሻሽ በፃፉት ደብዳቤ በምርጫው እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል።

ዝርዝር ጉዳዮችን በቅርቡ እንደሚያሳውቁ የገለጹት ባይደን ድጋፍ ያደረጉላቸውንና አሜሪካውያንን አመስግነዋል።

ምርጫው እስከሚካሄድበት ጊዜ ድረስ በኃላፊነታቸው እንደሚቆዩ መግለጻቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።

አሁን ዘግይቶ በወጣ መረጃ ባይደን ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ በምክትላቸው ካማላ ሀሪስ የመተካት እድላቸው ሰፊ መሆኑ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም