ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ በ2024 በርካታ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያሏቸው 10 አገራት ይፋ ሆኑ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ በ2024 በርካታ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያሏቸው 10 አገራት ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ በ2024 በርካታ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያሏቸው 10 አገራት ይፋ ተደረጉ።
የሩሰያ ዜና አገልግሎት ስፑትኒክ እንደዘገበው ናይጄሪያ ከሁሉም አገራት የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዛለች።
ኢትዮጵያ ደግሞ ከኬኒያና ታንዛኒያን ቀድማ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ታንዛኒያ በመጨረሻው በ10ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ዘገባው ያሳያል።
የደረጃ አሰጣጡ መሰረት ያደረገው ከ80 ሺህ በላይ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተመርኩዞ መሆኑን ስፑትኒክ ጠቁሞ መስፈርቱ ከ22 ሺህ 500 በላይ የመረጃ ምንጮችን የሸፈነ እንደሆነም አመልክቷል።
ለደረጃ አሰጣጡ ኦንላይን ስታትስቲክስ ፖርታል በመጠቀም መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራ መከናወኑ ተገልጿል።
በአፍሪካ አገራት በይነ መረብ ወይም ኢንተርኔት በተመጣጣኝ ዋጋ ባላቸው መሳሪያዎች ተደራሽነት በአሁኑ ወቅት እያደገ መምጣቱን በዘገባው ተገልጿል።
በተጨማሪም የተሻለ የቴሌኮም ግንኙነት በተለይም የዲጂታል አገልግሎቶች በመስፋፋታቸው ምክንያት የዓለም አቀፍ እና የአፍሪካ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ማሻቀቡን ቀጥሏል ብሏል ስፑትኒክ በዘገባው።
በአፍሪካ ያለው የኢንተርኔት አጠቃቀም ምንም እንኳን ከሌሎች ክፍለ ዓለማት ጋር ሲነጻጸር አሁንም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ቢሆንም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን አስደናቂ እድገት መታየቱን ዘገባው አስታውሷል።
ዘገባው እ.ኤ.አ. በ2024 የኢንተርኔት አጠቃቀምን የሚመሩ አስር የአፍሪካ ሀገራትን ዝርዝር እንሚመለከተው አስቀምጧል፡-
1. ናይጄሪያ (103 ሚሊዮን ወይም 45 ነጥብ 2 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣
2. ግብፅ (82 ሚሊዮን ወይም 76 በመቶው ህዝብ)፣
3. ደቡብ አፍሪካ (45 ሚሊዮን ወይም ከህዝቡ 72 ነጥብ በመቶ)፣
4. ሞሮኮ (34 ሚሊዮን ወይም 92 ነጥብ 2 በመቶው የህዝብ ብዛት)፣
5. አልጄሪያ (33 ሚሊዮን ወይም 71 ነጥብ 8 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣
6. ዲሞክራቲክ ኮንጎ (28 ሚሊዮን ወይም 27 ነጥብ 4 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣
7. ጋና (24 ሚሊዮን ወይም 71 ነጥብ 3 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣
8. ኢትዮጵያ (24 ሚሊዮን ወይም 21 ነጥጭብ 1 በመቶ የህዝብ ብዛት)፣
9. ኬንያ (22 ሚሊዮን ወይም 43 ነጥብ 3 በመቶው የህዝብ ብዛት)፣
10. ታንዛኒያ (21 ሚሊዮን ወይም ከህዝቡ 33 ነጥብ 4 በመቶ