ኮደርስ መርሃ ግብር አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክሂሎት የሚያስጨብጥ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2016(ኢዜአ)፦ ኮደርስ መርሃ ግብር አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክሂሎት የሚያስጨብጥ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የ''አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ’’ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥታት የተጀመረ የዲጂታል ሥራ ክሂሎቶችን የማሳደጊያ የትብብር ፕሮጀክት እንደሆነም ተገልጿል።

በማደግ ላይ ባለው ዲጂታል ኢኮኖሚ ከባቢ የመጪው ትውልድ ኢትዮጵያውያንን ለማብቃት ታልሞ የተጀመረ እንደሆነም ተመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም አዲሱን መርሃግብር የዲጂታል እውቀትን ክፍተት ለማጥበብ የሚያስችል የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 አካል በማድረግ በይፋ ማስጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

እ.ኤ.አ በ2026 መርሃግብሩ አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክሂሎት የሚያስጨብጥ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም