የኢትዮጵያና የቻይና የሳይንስና ቴክኖሎጂ የትብብር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያና የቻይና ሦስተኛው የሳይንስና ቴክኖሎጂ የትብብር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በጉባዔው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሊበ ዢን እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንገዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ በሚያስችል ጥረት ውስጥ መሆኗን ገልጸዋል። 

የኢትዮጵያና ቻይና ዲፕሎማሲ በጠንካራ ግንኙነት መቀጠሉን ጠቅሰው፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ድጋፍና ትብብሩም ለድጅታል ትራንስፎርሜሸን እቅድ መሳካት የላቀ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል። 

ሁለቱ አገሮች በኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በመሠረተ-ልማትና ሌሎችም መስኮች ተቀራርበው መስራታቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

የዛሬው መድረክም የዘርፉ ባለሙያዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ የእውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ይሆናል ነው ያሉት።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም