የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታን ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 24/2016(ኢዜአ)፦የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ ሀገራዊ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታን በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስታወቀ።


 

በውይይቱ ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ እየተሻሻለ የመጣውን የአገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ የሚጠብቁ ሀገራዊ ሁነቶች በሰላም እንዲካሄዱ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ለተግባራዊነቱ እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።


 

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ በወቅታዊ ሀገራዊ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጉን አስታውቋል።

በውይይቱ የተገኘውን ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል ቀጣይ የሀገሪቱን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ አቅጣጫዎች ማስቀመጡን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም