የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮችና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፅዳት ኤጀንሲ አመራሮችና ሰራተኞች በረጲ ደረቅ ቆሻሻ ስፍራ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በችግኝ ተከላው ላይ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ቆንጅት ደበላ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ለማ(ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች ተሳትፈዋል።

የፅዳት ሰራተኞችና ሽርክና ማህበራት አባላትም በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።

መርሐ ግብሩ የተካሄደው "የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

በዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዟል።

የተለያዩ ተቋማት፣ ማህበራትና ልዩ ልዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም