የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

ባህር ዳር፤ ሐምሌ 27/2016 (ኢዜአ)፦የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰተማራቸውን ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ነው።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል ወይዘሮ አስቴር ዘውዴን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የተመራቂ ወላጆች ተገኝተዋል።

ዩኒቨርሲቲው እያስመረቀ ያለው በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰተማራቸውን 8 ሺህ 524 ተማሪዎችን ሲሆን ከተመራቂዎቹ መካከል በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ 3 ሺህ 708፣ በሶስተኛ ዲግሪ 82፣ በስፔሻሊቲና ሳብ ስፔሻሊቲ 62 የህክምና ዶክተሮች ይገኙበታል።


 

እንዲሁም በማሪታይም፣ በአመራርነትና በሌሎች መርሃ ግብሮች የሰለጠኑ ተማሪዎችን እንደሚገኙበት ተመላክቷል።

ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች መካከልም 3 ሺህ 34ቱ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች ከ28 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ መሆኑም ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም