ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ጠዋት የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ ብለዋል።

ውይይታችን ተጠናክረው በቀጠሉት የሁለቱ ሀገሮቻችን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ያተኮረ ነበር ሲሉም አክለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም