የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራርና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራርና ሠራተኞች ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

የዘንድሮው ሀገር አቀፍ  የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር "የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ሃሳብ በመካሄድ ላይ ነው።

በዚሁ መርኃ ግብር የተለያዩ ተቋማት አሻራቸውን እያኖሩ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራርና ሠራተኞች ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።

አመራርና ሠራተኞቹ የአረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ነው።


 

ባንኩ  በዘንድሮው መርኃ ግብር  በአዲስ አበባ ማዕከል ብቻ  ከ50 ሺህ በላይ ለምግብነት የሚውሉ ፣ ሀገር በቀልና ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ዛፎችና ችግኞች ለመትከል አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ማዕከል በተጨማሪ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ 23 ዲስትሪክቶች የችግኝ ተከላው እንደሚካሄድ ነው የተገለፀው።

የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ  ለመትከል ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም