በ50 ሜትር ሴቶች ነጻ ቀዘፋ ማጣሪያ ሊና አለማየሁ አራተኛ ብትወጣም ወደ ግማሽ ፍጻሜ አላለፈችም

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የ50 ሜትር ሴቶች ነጻ ቀዘፋ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ዋናተኛዋ ሊና አለማየሁ አራተኛ ብትወጣም ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሳታልፍ ቀርታለች።

በምድብ 2 የተወዳደረችው ሊና በውድድሩ የገባችበት ሰዓት 31 ሴኮንድ ከ87 ማይክሮ ሴኮንድ ነው።

የ50 ሜትር ሴቶች የነጻ ቀዘፋ ውድድር ማጣሪያ በ10 ምድቦች ተከፍሎ የተካሄደ ሲሆን ከየምድቡ አንደኛ የወጡ ዋናተኞች ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፈዋል።

በተጨማሪም ከምድቦቹ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ ተጨማሪ 6 አትሌቶች ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግረዋል።

የ50 ሜትር ሴቶች የነጻ ቀዘፋ የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ39 ደቂቃ ላይ ይደረጋል።

ኢትዮጵያ በውሃ ዋና ስፖርት በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ስትሳተፍ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም