ኢዜአ ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝብ ተደራሽ ከማድረግ በተጨማሪ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝብ ተደራሽ ከማድረግ በተጨማሪ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር  በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑ ተገለፀ።

የዘንድሮ ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ሐይቅ ከተማ ተገኝተው በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

የኢዜአ አመራሮችና ሰራተኞች ዛሬ በእንጦጦ ፓርክ  አረንጓዴ  አሻራቸውን አኑረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ነጋሲ አምባዬ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ኢዜአ ለተከታታይ ዓመታት ችግኞችን በመትከል የራሱን አሻራ እያኖረ መጥቷል። 

የተተከሉት ችግኞች አገር በቀል ከመሆናቸው ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የአፈር ለምነትን ለመጠበቅና  ለምግብነት የሚውሉ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

ተቋሙ በቀጣይም የተተከሉ ችግኞችን የጽድቀት ምጣኔ ከፍ ለማድረግ ፕሮግራም አውጥቶ እንክብካቤ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

 

በችግኝ ተከላው ከተሳተፉ የተቋሙ ሰራተኞች መካከል ዮሐንስ ወንድይራድ እና የንጉስ ውቤ ፤ ባለፉት ተከታታይ አመታት ኢዜአ ባዘጋጃቸው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች መሳተፋቸውን አመላከተዋል፡፡


 

ችግኞችን ከመትከል ባሻገር እንዲጸድቁ እንክብካቤ ማድረጋቸውን ጠቁመው፤ በቀጣይም ይህንኑ ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

በዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር "የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙ ይታወቃል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም