ድርጅቱ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ሳውላ ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ6 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ። 

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) የድርጅቱ ሠራተኞችና አመራሮች በክስተቱ እጅግ ማዘናቸውን ተናግረዋል።

የተቋሙ ሠራተኞችና አመራሩ ከተጎጂዎች ጎን መሆናቸውን ለማረጋገጥ ዛሬ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።


 

በድጋፉ ድርጅቱ የ5 ሚሊዮን ብር፤ የተቋሙ አመራረና ሠራተኛው ደግሞ ከ1 ሚሊዮን 912 ሺህ ብር በላይ በማዋጣት በጠቅላላ ከ6 ሚሊዮን 912 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። 

በየደረጃው ያለው የክልሉ መንግስት መዋቅር እና የአካባቢው ማህበረሰብ በነፍስ አድን ሥራው ያደረጉት ርብርብና አስተዋጾ የሚደነቅ መሆኑንም ተናግረዋል። 

ድርጅቱ የጀመረውን ድጋፍ በቀጣይም እንደሚያጠናክር ገልጸው፣ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም