ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሶማሊያ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ባለፈው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሶማሊያ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ባለፈው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሶማሊያ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ባለፈው የሰው ህይወትና ባስከተለው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በሶማሊያ ሞቃዲሾ የባህር ዳርቻ ላይ በደረሰው አሰቃቂ የሽብር ጥቃት በሰው ህይወት መጥፋት እና በደረሰው ጉዳት በጣም አዝነናል ብለዋል፡፡