የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተርክዬ አቻቸው ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተርክዬ አቻቸው ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ጋር ተወያዩ።
ሁለቱ የሥራ ኃላፊዎች በሶማሊያ እና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታና በሌሎች የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግም ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።