ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በመካከለኛ ርቀት ለፍጻሜ ለማለፍ የሚያደርጓቸው የማጣሪያ ውድድሮች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ አትሌቶች በመካከለኛ ርቀት ለፍጻሜ ለማለፍ የማጣሪያ ውድድራቸውን ዛሬ ያደርጋሉ።

ከረፋዱ 5 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ላይ በሚካሄደው የ3000 ሜትር መሰናክል ሴቶች የማጣሪያ ውድድር ሎሚ ሙለታና ሲምቦ አለማየሁ ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ።

በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ሁለተኛ ተሳትፎዋን የምታደርገው አትሌት ሎሚ በማጣሪያው በምድብ 1 ትወዳደራለች።

በቶኪዮ በተካሄደው 32ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ርቀት ባደረገችው ማጣሪያ 10ኛ ወጥታ ለፍጻሜ አላለፈችም።

ሎሚ እ.አ.አ በ2021 በኔዘርላንድ ሄንግሎ በተካሄደ ውድድር 9 ደቂቃ ከ14 ሴኮንድ ከ04 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዘግባለች።

በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም በጋና በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ3000 ሜትር መሰናክል ሴቶች ፍጻሜ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የማጣሪያ ውድድሯን በምድብ 2 ታደርጋለች። ሲምቦ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ስትሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

አትሌቷ እ.አ.አ በ2023 በጣልያን ፍሎረንስ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር 9 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ ከ71 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባለች።

ሲምቦ እ.አ.አ በ2022 በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3000 ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

በሶስት ምድብ በሚካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድቡ ከአንድ እስከ አምስት የሚወጡ አትሌቶች ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የፍጻሜ ፍልሚያ ያልፋሉ።

ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ35 ደቂቃ የ800 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ይደረጋል። በማጣሪያው አትሌት ፅጌ ዱጉማና አትሌት ወርቅነሽ መለሰ ይሳተፋሉ።

ሁለቱም አትሌቶች ከትናንት በስቲያ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ከየምድባቸው አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸው ይታወቃል።

የመጀመሪያ የኦሊምፒክ ተሳትፎዋን እያደረገች የምትገኘው አትሌት ወርቅነሽ መለሰ በምድብ 1 ውድድሯን ታደርጋለች።

አርብ በነበረው የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ 1 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ7 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን በ68 ማይክሮ ሴኮንድ አሻሽላለች።

በምድብ 2 የምትገኘው አትሌት ፅጌ ዱጉማ እ.አ.አ ግንቦት 18 2024 በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በተካሄደ ወድድር 1 ደቂቃ ከ57 ሴኮንድ ከ56 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓት አስመዘግባለች።

ወጣቷ ተስፈኛ አትሌት በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም በስኮትላንድ ግላስኮው በተካሄደው 19ኛው የወርልድ አትሌቲክስ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና እንዲሁም በጋና አክራ በተደረገው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ800 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በሶስት ምድብ በሚደረገው የማጣሪያ ውድድር ከየምድቡ አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ ያልፋሉ። በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ምድብ በተመሳሳይ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ ሁለት አትሌቶች ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ።

ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ10 ደቂቃ በሚካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ አትሌት ኤርሚያስ ግርማና አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ይወዳደራሉ።

ኤርሚያስ ከትናንት በስቲያ በተደረገው ማጣሪያ 1ኛ እንዲሁም ሳሙኤል 6ኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው ደርሰዋል።

አትሌት ኤርሚያስ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም በፊንላንድ በተካሄደ ውድድር 3 ደቂቃ ከ34 ሴኮንድ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቱን አስመዝግቧል።

በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም በጋና አክራ በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች በርቀቱ የብር ሜዳሊያ ማግኘቱ ይታወሳል።

ሌላኛው ተወዳዳሪ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ከሶስት ዓመት በፊት በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደ ውድድር 3 ደቂቃ ከ30 ሴኮንድ ከ71 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓቱን አስመዝግቧል።

አትሌት ሳሙኤል በ17ኛው እና 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮናዎች በ1500 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል።

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በሚካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድቡ ከአንድ እስከ ስድስት የሚወጡ አትሌቶች ለፍጻሜው ያልፋሉ።ከረፋዱ 5 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ላይ በሚካሄደው የ3000 ሜትር መሰናክል ሴቶች የማጣሪያ ውድድር ሎሚ ሙለታና ሲምቦ አለማየሁ ኢትዮጵያ ወክለው ይሳተፋሉ።

በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ሁለተኛ ተሳትፎዋን የምታደርገው አትሌት ሎሚ በማጣሪያው በምድብ 1 ትወዳደራለች።

በቶኪዮ በተካሄደው 32ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ርቀት ባደረገችው ማጣሪያ 10ኛ ወጥታ ለፍጻሜ አላለፈችም።

ሎሚ እ.አ.አ በ2021 በኔዘርላንድ ሄንግሎ በተካሄደ ውድድር 9 ደቂቃ ከ14 ሴኮንድ ከ04 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዘግባለች።

በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም በጋና በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ3000 ሜትር መሰናክል ሴቶች ፍጻሜ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የማጣሪያ ውድድሯን በምድብ 2 ታደርጋለች። ሲምቦ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ስትሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

አትሌቷ እ.አ.አ በ2023 በጣልያን ፍሎረንስ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር 9 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ ከ71 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባለች።

ሲምቦ እ.አ.አ በ2022 በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3000 ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

በሶስት ምድብ በሚካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድቡ ከአንድ እስከ አምስት የሚወጡ አትሌቶች ማክሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የፍጻሜ ፍልሚያ ያልፋሉ።

ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ35 ደቂቃ የ800 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ይደረጋል። በማጣሪያው አትሌት ፅጌ ዱጉማና አትሌት ወርቅነሽ መለሰ ይሳተፋሉ።

ሁለቱም አትሌቶች ከትናንት በስቲያ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ከየምድባቸው አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸው ይታወቃል።

የመጀመሪያ የኦሊምፒክ ተሳትፎዋን እያደረገች የምትገኘው አትሌት ወርቅነሽ መለሰ በምድብ 1 ውድድሯን ታደርጋለች።

አርብ በነበረው የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ 1 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ7 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን በ68 ማይክሮ ሴኮንድ አሻሽላለች።

በምድብ 2 የምትገኘው አትሌት ፅጌ ዱጉማ እ.አ.አ ግንቦት 18 2024 በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በተካሄደ ወድድር 1 ደቂቃ ከ57 ሴኮንድ ከ56 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓት አስመዘግባለች።

ወጣቷ ተስፈኛ አትሌት በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም በስኮትላንድ ግላስኮው በተካሄደው 19ኛው የወርልድ አትሌቲክስ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና እንዲሁም በጋና አክራ በተደረገው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ800 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በሶስት ምድብ በሚደረገው የማጣሪያ ውድድር ከየምድቡ አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ ያልፋሉ። ከእያንዳንዱ ምድብ በተመሳሳይ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ ሁለት አትሌቶች ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ።

ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ10 ደቂቃ በሚካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ አትሌት ኤርሚያስ ግርማና አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ይወዳደራሉ።

ኤርሚያስ ከትናንት በስቲያ በተደረገው ማጣሪያ 1ኛ እንዲሁም ሳሙኤል 6ኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው ደርሰዋል።

አትሌት ኤርሚያስ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም በፊንላንድ በተካሄደ ውድድር 3 ደቂቃ ከ34 ሴኮንድ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቱን አስመዝግቧል።

በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም በጋና አክራ በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች በርቀቱ የብር ሜዳሊያ ማግኘቱ ይታወሳል።

ሌላኛው ተወዳዳሪ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ከሶስት ዓመት በፊት በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደ ውድድር 3 ደቂቃ ከ30 ሴኮንድ ከ71 ማይክሮ ሴኮንድ የርቀቱን የግል ምርጥ ሰዓቱን አስመዝግቧል።

አትሌት ሳሙኤል በ17ኛው እና 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮናዎች በ1500 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል።

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በሚካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድቡ ከአንድ እስከ ስድስት የሚወጡ አትሌቶች ለፍጻሜው ያልፋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም