የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ14ተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ፖሊሶች እያስመረቀ ነው

ድሬዳዋ፤ ሐምሌ 28/2016 (ኢዜአ)፡- የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ14ተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ፖሊሶች በሁርሶ የኮንቲንጀንት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት  እያስመረቀ ነው።

ተመራቂዎች  የፖሊሲነት ሙያን በንድፈ ሀሳብና በተግባር በብቃት አጠናቀው መመረቃቸው በስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል ።

ለስልጠናው ስኬታማነት  የሁርሶ የኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አመራሮች ፣ መኮንኖችና ሠራተኞች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውም ታውቋል።

በምረቃው ስነስርዓት ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ምክርቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፈቲህያ አደን፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ  ከድር ጁሃር፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ  የአስተዳደሩ ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ተገኝተዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ፣ የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ፣ መኮንኖችና የተመራቂ ቤተሰቦችም ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የአገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ተመራቂዎች በስልጠናቸው ወቅት የቀሰሙትን የፖሊስነት ሙያና ምግባር በተለያዩ ትርኢቶች  ለታዳሚዎች አሳይተዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም