በ3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ አትሌት ሎሚ ሙለታና አትሌት ሲምቦ አለማየሁ ለፍጻሜ አለፉ

ዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ3000 ሜትር መሰናክል ሴቶች ዛሬ ረፋድ ላይ በተካሄደው ማጣሪያ አትሌት ሎሚ ሙለታና አትሌት ሲምቦ አለማየሁ ለፍጻሜው አልፈዋል።

በምድብ 1 የተወዳደረችው አትሌት ሎሚ 9 ደቂቃ ከ10 ሴኮንድ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ አምስተኛ በመውጣት ነው ፍጻሜውን የተቀላቀለችው።

በምድብ 2 የነበረችው ሲምቦ 9 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ ከ42 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ በመውጣት ለፍጻሜ ማለፏን አረጋግጣለች።

በሶስት ምድብ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድባቸው ከአንድ እስከ አምስት የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ አልፈዋል።

የፍጻሜው ውድድር ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ላይ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም