ለማሻ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

ሚዛን አማን፤ ሐምሌ 28/2016 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሸካ ዞን ከ400 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት ለሚገነባው የማሻ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክቱን የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ናቸው።

በመርሃ ግብሩ ወቅት  የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው እንደተናገሩት፤ የውሃ ፕሮጀክቱ ግንባታ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሲጠናቀቅ 46 ሺህ ህዝብን ተጠቃሚ ያደርጋል።

ከዋን ዋሽ ጋር በመተባበር ለሚሠራው የውሃ ፕሮጀክት ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መያዙን ጠቅሰው ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ ትኩረት መሰጠቱን አስታውቀዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም