የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በጉጂ ዞን የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በጉጂ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ልማት ስራዎችን ጎበኙ።

የክልሉ ፕሬዝዳንትና ሌሎችም የክልልና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በጉጂ ዞን በቦሬ እና አኖ ቄረንሳ ወረዳዎች የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።


 

በክልሉ በግብርና ልማትና የእንስሳት እርባታ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ሽመልስ ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ በጉጂ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የግብርና እና የእንስሳት ልማት ስራዎች ጥሩ ማሳያ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በመሆኑም በእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ፣ በመኖ ልማትና አቅርቦት እንዲሁም የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ዙሪያ የተጀመሩ ስራዎች የሚበረታቱ በመሆናቸው ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።

በእንስሳት እርባታ በተገኘው ስኬት ልክ የተቀናጀ የግብርና ስራም በስፋት ሊከናወን እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

በሁሉም ዘርፎች መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ የሚያደርግ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም