በ1500 ሜትር አትሌት ሳሙኤል ተፈራና ኤርሚያስ ግርማ ለፍጻሜ ማለፍ አልቻሉም - ኢዜአ አማርኛ
በ1500 ሜትር አትሌት ሳሙኤል ተፈራና ኤርሚያስ ግርማ ለፍጻሜ ማለፍ አልቻሉም
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ1500ዐ ሜትር ወንዶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ለፍጻሜ ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።
በምድብ 1 የተወዳደረው አትሌት ሳሙኤል 3 ደቂቃ ከ33 ሴኮንድ ከ02 ማይክሮ ሴኮንድ ዘጠነኛ ወጥቷል።
በምድብ 2 የተወዳደረው አትሌት ኤርሚያስ 3 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ ከ3 ማይክሮ ሴኮንድ 12ኛ በመውጣት ለፍጻሜው አላለፈም።
በሁለት ምድብ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድባቸው ከአንድ እስከ ስድስተኛ የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜው አልፈዋል።
የፍጻሜው ውድድር ማክሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም 3 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ ይከናወናል።