በ800 ሜትር ማጣሪያ ወርቅነሽ መለሰና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2016(ኢዜአ)፦በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ80ዐ ሜትር ዛሬ ማምሻውን በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር አትሌት ወርቅነሽ መለሰና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለፍጻሜው አልፈዋል።

በምድብ 1 የተወዳደረችው አትሌት ወርቅነሽ 1 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ06 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ በመውጣት ለፍጻሜ አልፋለች።

አትሌቷ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷን ለሁለተኛ ጊዜ አሻሽላለች።

በምድብ 2 የሮጠችው ፅጌ ዱጉማ 1 ደቂቃ ከ57 ሴኮንድ ከ47 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት ለፍጻሜ ማለፏን አረጋግጣለች። ፅጌ በርቀቱ ያላትን የግል ምርጥ ሰዓቷን አሻሽላለች።


 

በሶስት ምድብ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድባቸው አንደኛና ሁለተኛ የወጡት አትሌቶች ለፍጻሜው አልፈዋል።

በተጨማሪም ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ ሁለት አትሌቶች ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።

የፍጻሜው ውድድር ነገ ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ላይ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም