ለአቅመ ደካማ ወገኖች የሚከናወነው የቤት ግንባታ በፍጥነት እየተከወነ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/ 2016 (ኢዜአ)፦ በአዋሬ አካባቢ ለአቅመ ደካማ ወገኖች እየተከናወነ ያለው የቤት ግንባታ በታሰበው መሠረት እየሄደ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በየዓመቱ ለአረጋውያን እና በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች የሚደረገው የቤት እድሳት እና ግንባታ ላይ የሚያተኩረው ማኅበራዊ በጎ ሥራ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥራዎች ቁልፍ ምሰሶ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም በአዋሬ አካባቢ ለሰው የተሻለ እና የተከበረ አኗኗር ለመፍጠር እየተደረገ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ በፌደራል እና ክልል የመንግሥት አካላት የሚተገበረው የዚሁ ትልም ዐቢይ አካል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

የዘንድሮው ሥራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግንቦት ወር ማስጀመራቸውን ያስታወሰው ጽህፈት ቤቱ፤ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የሚከናወነው የቤት ግንባታ በፍጥነት እየተከወነ እንደሚገኝ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም