አፍሪካ የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ ማሳየት ችላለች - ኢዜአ አማርኛ
አፍሪካ የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ ማሳየት ችላለች
አዲስ አበባ፤ ታኅሳሥ 25/2017 (ኢዜአ) አፍሪካ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ ማሳየቷ ተገለፀ።
አሕጉሪቱ የወሰደቻቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ደግሞ ለተገኘው ጥንካሬ በምክንያት ተነስተዋል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ያወጡት ትንበያ እንዳመለከተው አፍሪካ በዓመቱ የ 3 ነጥብ 6 በመቶ ዕድገት ታስመዘግባለች።
እንዲያም ሆኖ የዋጋ ግሽበት እና የብድር ዕዳ መጨመር ዋነኛ የሕጉሪቱ ፈተና ሆነው መቀጠላቸውን የአፍሪካ ቢዝነስ ዘገባ አመልክቷል።