ወንዞቿን ከብክለት ወደ ትሩፋት ለመለወጥ የተነሳችው አዲስ አበባ

 

አዲስ አበባ ከተቆረቆራች አንድ ከግማሽ ምዕተ ዓመት ልትደፍን ጥቂት ዓመታት ይቀራታል። ከተማዋ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ዑደት አስኳል ሆና ሁሉን አስተናግዳለች።

May be an image of skyscraper and twilightMay be an image of fog, horizon, twilight and skyscraper

 

ዕድል ቀንቷት ከኢትዮጵያዊያን አልፋ የአፍሪካዊያን መዲና ሆናለች። ዘመን ችሯት የዓለም ዲፕሎማሲ ማዕከል አድርጓታል። ከአፍሪካ ወደ ዓለም፤ ከዓለም ወደ አፍሪካ መግቢያና መውጫ በር ናት።

No photo description available.

May be an image of twilight and skyscraper

የሀገሪቷ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ዕድገት የስበት ማዕከል ናት። በፍጥነት ያደገችና ነዋሪቿን ያበዛች፤ ምጣኔ ሀብትን ያጎለመሰች ከተማ ናት። ዳሩ የከተሜነት መዋቅራዊ ፕላኗ አኳያ ውስንነቶች እንደሚስተዋልባት በባለሙያዎች ዘንድ ይነሳል።

No photo description available.

ትውልድን ታሳቢ ያደረገ ዘመን ተሻጋሪ፣ ለኑሮ ምቹና ስሟን የሚመጥን የክትመት ዕቅድ ይዛ ባለመጓዟ ውበትም፤ ኑረትም፣ ምቾትም አጉድላለች። በጽዳትና ውበቷ ረገድ በእንግዶቿም ዘንድም ለትቸት ተጋልጣ ታውቃለች።

No photo description available.

ከአዲስ አበባ ድክመቶች አንዱ የብዙ ወንዞች ባለቤት ሆኗ አንዱንም እሴት ጨምራ ወደ ሀብትትነት አለመቀየሯ ነው። ፈሳሽ ወንዟን አልምታ በውበት አለመፍሰሷ።

No photo description available.

በመዲናዋ ከ76 ያላነሱ ዋና እና ገባር ወንዞች ይገኛሉ። ዳሩ በየዘመኑ የከተማ ልማት ዕቅዶች የወንዝ ዳርቻን ታሳቢ ባለማድረጋቸው ወንዞቿ ለገጽታዋ ውበት ሳይሆን ሳንካ ሆነዋታል። የከተሜነት ወጓ ከወንዞቿ ልማት ጋር አልተመራም። የሰዎች አሰፋፈር ከዓለም አቀፋዊ የከተሜነት ልክን አልጠበቀም። ይህ ደግሞ ወንዞች ለነዋሪዎቿ ጠንቅ እንጂ ትሩፋት እንዳይሆኑ አድርጓል።

በርካታ ሀገራት ከተሞች ጥቂት ወንዞቻቸውን ለጌጥም፤ ለበረከትም አውለዋል። ባለበዙ ወንዞች ባለቤቷ አዲስ አበባ ግን "ጽድቁ ከርቶ..." እንዲሉ ከወንዞቿ ጥቅሟ ቀርቶ፤ ጠንቋ በዝቶ ቆይታለች።

ወንዞቹን ለምተው ለዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከመዋል ይልቅ ለብክለት ተጋልጠው ለሕዝብ ጤና ጠንቅ ነበሩ። በክረምት ወራትም ጎርፍ እየተሞሉ ነዋሪዎችን ለአደጋ አጋልጠዋል።

እነሆ አሁን የዘመናት ክፍተቷን ለመቅረፍ ተነስታለች። ከተማ አቀፍ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ተጀምረዋል። የመዲናዋን ወንዞች ከሕዝብ ጤና ጠንቅነት ወደ ጥቅም የመለወጥ ተግባር እየተከናወነ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከሚፈሱ ወንዞች መካከል እስካሁን አንድ ወንዝ ለቱሪስት መስህብነት፣ ለመዝናኛነትና ለሌላ አገልግሎት ለማዋል የተሰራ የተፋሰስ ልማት እየተከናወነ ነው።

የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የበርካታ ሀገራት ከተሞች የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ወንዞችን አልምተው ለቱሪስት መነሃሪያ እንዲሆኑ በማስቻል ለቱሪዝም ዘርፍ እመርታ ወሳኝ ድርሻ እንዲይዙ ማድረጋቸውን ይጠቅሳሉ።

አዲስ አበባ ግን በርካታ ወንዞችን ታቅፋ ይህን መልካም ዕድል አልምታ ሳትጠቅም በመቆየቷ ቁጭት የሚፈጥር ጉዳይ እንደሆነ ያነሳሉ።

May be an image of grass

እናም እየተከናወነ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት የህብረተሰቡን አኗኗር ብቻ ሳይሆን ለተፋሰስ ልማትም ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ወንዞች ከጠንቅነት ወደ ህዝብ ጥቅምነት የመለወጥ ስራዎች እንደቀጠሉ ከንቲባዋ አብስረዋል።

በዚህም አዲስ አበባ ካሏት 76 ወንዞች መካከል አንድ ሶስተኛው ትልልቅ ወንዞቿ ለቱሪስት መዝናኛ አገልግሎት መዋል የሚችሉ ናቸው ብለዋል።

ከነዚህም መካከል እስካሁን ሁለት ወንዞችን በወንዝ ዳርቻ ልማት በማስገባት ወደ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የመለወጥ ጉዞ መጀመሩን ተናግረዋል።

May be an image of 9 people and lake

በትናንትናው ዕለት የከተማዋ አመራሮች እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማቶችን ጎብኝተው ነበር። ከተጎበኙ የከተማ ልማት ስራዎች መካከል የቀበና ቁጥር-1 እና 2 እንዲሁም ከእንጦጦ-ፍሬንድ ሽፕ- ፒኮክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ይገኝበታል።

May be an image of lake

ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የወንዝ ዳርቻ ልማት ከብክለት ነጻ አካባቢን በመፍጠር፣ ከተማዋን ጽዱና አረንጓዴ በማድረግና በሽታን በመከላከል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

የእንጦጦ-ፍሬንድ ሽፕ- ፒኮክ የወንዝ ዳርቻ ልማት የተለያዩ ፓርኮችን በማስተሳሰር በፕላን የተገነባ ከተማን እውን ማድረግ የሚያስችል እንደሆነ በማብራራት።

በቀበና ቁጥር 2 እንዲሁም ከእንጦጦ- ፍሬንድ ሽፕ- ፒኮክ የወንዝ ዳርቻ አፍንጮ በር አካባቢ የመጓተት ችግሮችን በመቅረፍ ስራው በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

70 ደረጃ እና 40 ደረጃ ታሪካዊ ቅርስነታቸውን ጠብቀው እየታደሱ እንደሚገኙ ገልጸው፤ ከዕይታ ተደብቆ የቆየውን የራስ መኮንን ሀውልት ከቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ዕድሳት ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ፒያሳ አካባቢ እየተሰራ የሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የሩጫ፣ የሳይክል፣ የመዋኛና ሌሎች ቦታዎችን ነው።

May be an image of grass

ልማቶቹ አለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮችንና ሁነቶችን ለማስተናገድ የሚያስችሉ እንደሆኑ ከንቲባዋ በጉብኝቱ ወቅት አብራርተዋል። የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ፓርኪንግ፣ የታክሲ ተርሚናል፣ ሱቆችንና ሌሎች ልማቶችን አካቶ እየተሰራም ነው።

ፕላኑን የጠበቀ ዘመናዊ ከተማን እውን የሚያደርግ ከንቲባዋ ጠቁመዋል። የወንዝ ዳርቻን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አቀፍ የልማት ስራዎች ዘመናዊ ከተማን ያሟሉ በመሆኑ ለአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ይጨምራሉ።

No photo description available.

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም