በሐረሪ ክልል የዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በሐረሪ ክልል የዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ ተጀመረ
ሐረር፤ ጥር 17/2017(ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል የዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ "አፈራችን ለሀገራዊ ብልፅግናችን" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
በተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ በየደረጃው ያሉ የክልሉ አመራር አባላት፣ አርሶ አደሮችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በክልሉ ለአንድ ወራት በሚቆየው የተፋሰስ ልማት ስራ በ16 ተፋሰሶች 900 ሄክታር መሬት ላይ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ዕቀባ ስራ ለማከናወን መታቀዱን በክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ አራርሶ አደም ገልጸዋል።