በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

 አዲስ አበባ፤ ጥር 182017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት መርሃ ግብር  ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አጥቂው ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕና 1 ለ 0 በማሸነፍ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የ16ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከአንድ ቀን እረፍት በኋላ ከጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።

ኢትዮጵያ መድን በ29 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው።

መቻል በ27፣ ሀዲያ ሆሳዕና በ26 እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በ25 ነጥብ ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ያዘዋል።

አዳማ ከተማ፣ ስሑል ሽሬ፣ ሃዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ15ኛ እስከ 18ኛ  ያለውን ደረጃ በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም