በሲዳማ ክልል የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ ተጀመረ

ቦርቻ፤ ጥር 19/2017(ኢዜአ):- በሲዳማ ክልል የዘንድሮ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በይፋ ተጀምሯል።

የተፋሰስ ልማት ስራው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ አልዳዳ ደላ ቀበሌ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።


 

የ''አፈር ሀብታችን ለብልጽግናችን''በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የተፋሰስ ልማትን ሥራ ለአንድ ወር ይዘልቃል።

በክልሉ 678 ንዑስ ተፋሰሶች ላይ 136 ሺህ 400 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ይከናወናል ተብሏል።


 

በዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም