መቀሌ 70 እንደርታ እና አርባምንጭ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
መቀሌ 70 እንደርታ እና አርባምንጭ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ እና አርባምንጭ ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያሬድ ብርሃኑ እና ቦና ዓሊ ግቦቹን ለመቀሌ 70 እንደርታ አስቆጥረዋል።
አህመድ ሁሴን እና ፍቃዱ መኮንን ለአርባምንጭ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ ያሳረፉ ተጫዋቾች ናቸው።
ውጤቱን ተከትሎ መቀሌ 70 እንደርታ በ22 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አርባምንጭ ከተማ በ23 ነጥብ 6ኛ ደረጃን ይዟል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይጫወታሉ።