ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሊጉ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል 

አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤፍሬም ታምራት በ88ኛው እና ኪቲካ ጅማ በ94ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ18 ነጥብ ከነበረበት 14ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ከፍ ብሏል። በውድድር ዓመቱም አራተኛ ድሉን አስመዝግቧል። 

ንግድ ባንክ ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። 

በአንጻሩ በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ15 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ቀን ላይ በተደረገ የ17ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ እና አርባምንጭ ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም