በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ተጀመረ
ሺሾ-እንዴ፤ ጥር 22/2017(ኢዜአ)፡- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የዘንድሮው የበጋ ወቅት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ተጀምሯል።
በክልሉ በካፋ ዞን ሺሾ-እንዴ ወረዳ በተጀመረው የተፋሰስ ልማት ስራ የክልል፣ የዞን እንዲሁም የወረዳ አመራር አባላት ተገኝተዋል።
''የአፈር ሀብታችን ለብልጽግናችን'' በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የተፋሰስ ልማት ስራ ለ45 ቀናት የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል።
የተፋሰስ ልማት ስራው በ1ሺህ 100 ንዑስ ተፋሰሶች ላይ የሚካሄድ ሲሆን በዚህም 225 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ እንደሚከናወን ተጠቁሟል።