በስፖርት ፌስቲቫሉ 12 ተወዳዳሪዎች በወርልድ ቴኳንዶ የወርቅ ሜዳሊያ አገኙ 

አዲስ አበባ፤ጥር 22/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ ስድስተኛ ቀኑ ይዟል።

በወርልድ ቴኳንዶ በወንዶች በተደረጉ ውድድሮች በ80 ኪሎ ግራም  ፋሲል ላቀው ከደብረብርሃን ፣ በ74 ኪሎ ግራም ግዛቸው ደምሴ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፣ በ68 ኪሎ ግራም አማኑኤል ዳንኤል ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፣ በ63 ኪሎ ግራም ፍቃዱ ዳንኤል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፣ በ58 ኪሎ ግራም ተከታይ አደራው ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፣ በ54 ኪሎ ግራም ድሪባ ደበላ ከጅማ ዩኒቨርስቲ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

በወርልድ ቴኳንዶ ሴቶች በ67 ኪሎ ግራም ዘይነባ ቦንታ ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ በ62 ኪሎ ግራም ፀገነት ጎርፉ ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፣ በ57 ኪሎ ግራም አዜብ ጎንፋ ከሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፣ በ53 ኪሎ ግራም ያብስራ በቀለ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፣ በ49 ኪሎ ግራም  አደዋ ካሳ ከደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ፣ በ46 ኪሎ ግራም እየሩሳሌም ተሾመ ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ዩኒቨርሲቲ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነዋል። 


 

በወንዶች የሰላሌ፣ የመቅደላ አምባ ፣ የሐረማያ ፣ የዋቸሞ ፣ የአርሲ እና የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲዎች የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችለዋል።

በሴቶች የወራቤ፣ የጂንካ ፣ ድሬዳዋ ፣ ሰመራ እና ፌዴራል ቴክኒኒክና ሙያ ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪዎች የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

በወርልድ ቴኳንዶ በወንድም በሴትም በድምሩ 24 የነሐስ ሜዳሊያዎችን አሸናፊ ዩኒቨርሲቲዎች ወስደዋል።

በፌስቲቫሉ በቼዝ፣ በባህላዊ ስፖርት፣ እግር ኳስ እና አትሌቲክስ ጠንካራ ፉክክር እየተካሄደ እንደሚገኝ ይገኛል።

የስፖርት ፌስቲቫሉ እስከ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ፌስቲቫሉ በኮቪድና በተለዩዩ ምክንያቶች ለዘጠኝ ዓመታት ከተቋረጠ በኋላ በድጋሚ መጀመሩ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም