ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳዋ ሆቴሳ በ55ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ወልዋሎን መሪ አድርጓል።

ይሁንና ፍቃድ ዓለሙ በ68ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ኢትዮ ኤሌክትሪክን አቻ አድርጓል።

ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በስድስት ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። 

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ19 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሃዋሳ ከተማ ከመቻል ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም