ሃዋሳ ከተማ ከ12 ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ ከ12 ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ መቻልን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዓሊ ሱሌይማን በ55ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ቡድኑን አሸናፊ አድርጋለች።
ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ ከ12 ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰ ሲሆን በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
ቡድኑ በ15 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 16ኛ ከፍ ቢያደርግም አሁንም ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በ27 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።