በሕገ ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ 1 ሺህ 400 ሊትር በላይ ነዳጅ ተያዘ - ኢዜአ አማርኛ
በሕገ ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ 1 ሺህ 400 ሊትር በላይ ነዳጅ ተያዘ
መተማ ፤ ጥር 23/2017 (ኢዜአ):- በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ በሕገ- ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ ከ1 ሺህ 400 ሊትር በላይ የቤንዚን ነዳጅ መያዙን የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሙልዬ አየልኝ እንደገለጹት፤ ቤንዚኑ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከማደያ በድብቅ ተቀድቶ ሊሰራጭ ሲል ተደርሶበት ትናንት ማምሻውን ነው የተያዘው።
ነዳጅን ጨምሮ የንግድ ግብይትን ፍትሃዊነት ለመከታተል ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የሕገ- ወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለማስቆም ግብረ ሃይሉ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የገንዳ ውኃ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተወካይ ኢንስፔክተር ሀይሌ ብርሃኑ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ሕገ- ወጥ ተግባራትን ለማስቀረት ከህብረተሰቡና ከተቋማት ጋር በጋራ እየተሰራ ነው።
በሕገ-ወጥ መንገድ የነዳጅ ንግድ እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
ነዳጅና የሸቀጥ ምርቶች ለሸማቹ ህብረተሰብ በትክክል እንዲደርስ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።