የተፋሰስ ልማት የግብርና ልማት ስራቸውን ያቃናላቸው የሁለቱ ዞኖች አርሶ አደሮች - ኢዜአ አማርኛ
የተፋሰስ ልማት የግብርና ልማት ስራቸውን ያቃናላቸው የሁለቱ ዞኖች አርሶ አደሮች
አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች የልማት አማራጮችን በማስፋት ተጠቃሚነትን እንዳሳደገላቸው ኢዜአ ያነጋገራቸው የካፋ እና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች አርዞ አደሮች ገለጹ።
በካፋ ዞን ሺሾ-እንዴ ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ወልደየስ ወልደማሪያምና በቀለ ወልደገብርኤል የእርሻ መሬት ለማስፋፋትና በተለያዩ ምክንያቶች የአካባቢ መራቆት በመከሰቱ የግብርና ምርታማነታቸው ቀንሶ እንደነበር አስታውሰዋል።
የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራዎች ግን የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙና የአፈር ለምነት እንዲመለስ በማስቻላቸው በአትክልፍትፋ ፍራፍሬ ልማት እንዲሁም በእንስሳት መኖ በማልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ፈጥሮላቸዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የርዕሰ መስተዳድር የኢኮኖሚና መሰረተ ልማት ዘርፍ አማካሪ (ዶ/ር) ኢንጂነር ምትኩ በድሩ ባለፉት ሦስት ዓመታት በስነ ህይወታዊና አካላዊ ስራዎች የተገኙ አበረታች ውጤቶችን ማስቀጠል ዘንድሮም የተፋሰስ ልማት ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።
በዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በ1 ሺህ 100 ንዑስ ተፋሰሶች ከ225 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንደሚለማ ተገልጿል።
በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ወረዳ አርሶ አደሮች በማህበር ተደራጅተው በአካባቢያቸው የሚገኝ ደን በመንከባከብና በመጠበቅ ከእንሰሳት መኖና በንብ ማነብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አርሶ አደር አቡሌ መሀመድ አሊና ርሶ አደር አደም መሀመድ በማህበር ተደራጅተው በደን ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች በንብ ማነብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን ገልጸው፤ በደን ውስጥ መኖ በማልማት ለእንስሳቶቻቸው በቂ መኖ ማግኘት መቻላቸውን አአረጋገጠዋል።
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የሐረርጌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፋኪያ ጀማል እንዳሉት በምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች በአሳታፊ የደን ጥበቃና እንክብካቤ ከ2 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በ25 ማህበራት ታቅፈው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡ በባለቤትነት ስሜት ለደን ጥበቃ ማድረግ ከጀመረ ወዲህ በደን ላይ የሚደርስ ጉዳት ቀመቀነሱን ገልጸው ህብረተሰቡ ደኑን በመጠበቅ በውስጡ የእንስሳት መኖ እና ንብ በማነብ እንዲሁም ከደን ውጤቶች ሽያጭ ተጠቃሚ በመሆን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የምዕራብ ሐረርጌ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት የሰብል ልማት ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መገርሳ ዴሬሳ በዞኑ የግብርና እንሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ እና ያልታረሱ መሬቶችን በማልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተከናወኑት ተግባራት ውጤታማ ሆነዋል
በዞኑ 15 ወረዳዎች ለልማቱ ሲውሉ ያልነበሩና በበጋው የተፋሰስ ልማት የአፈር መሸርሸር የሚከላከሉ እርከኖች የተሰሩባቸው መሬቶች ለምነታቸው እየጨመረ በመምጣቱ አርሶ አደሩ ለልማቱ እንዲያውል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በመኸር ወቅቱ ከ559 ሺህ 343 ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የአገዳ፣ ብርዕ እና ቅባት ሰብሎች መልማቱን ገልጸው ይህም ከቀዳሚው አመት ከ159 ሺህ ሄክታር በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል፡፡