ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ስድስተኛ ተከታታይ ድሉን በማስመዘገብ መሪነቱን አጠናክሯል 

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፏል። 

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አማካዩ ዳዊት ተፈራ በ56ኛው ደቂቃ የማሸነፊያዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን በ32 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል። በውድድር ዓመቱን ዘጠነኛ ድሉን አስመዝግቧል።

ቡድኑ በሊጉ ስድስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል። 

በአንጻሩ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀዲያ ሆሳዕና በ26 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በ17ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም