አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በጊዜያዊነት ሲያለጥኑ የነበሩት መሳይ ተፈሪ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ለአንድ ዓመት እንዲቆዩ መወሰኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
አሰልጣኙ የቀደሙት አሰልጣኝ ሲል ገብረመድህ ኃይሌ ከዋልያዎቹ ጋር ከተለያዩ በኋላ ብሄራዊ ቡድኑን በጊዜያዊነት ሲመሩ ቆይተዋል።
ቡድኑ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች የሚያስመዘገበው ውጤት መሰረት ተደርጎ ሊታደስ በሚችል የአንድ ዓመት ውል ብሔራዊ ቡድኑን እየመሩ እንደሚቀጥሉም የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
አሰልጣኙ አብረዋቸው የሚሰሩ የአሰልጣኝ ቡድን አባላትን የማዋቀር ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።