የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2017(ኢዜአ)፦የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ይገኛል።
በትናንትናው እለት በደማቅ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የተጀመረው የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜው በጉባኤው አዘጋጅ አብይ ኮሚቴ ሪፖርት እና በሁለተኛው ጉባኤ የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።
ጉባኤው በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ኮሚቴው በቀረበ ሪፖርት ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሪፖርቱን በውይይት አዳብሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በቀጣይ መርሀ ግብሩም በቀሪ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎች ያሳልፋል፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።