የፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ እና የጅቡቲ ፋይናንስ ሚኒስትር ኢልያስ ሙሳ ዳዋሌህ ምን አሉ - ኢዜአ አማርኛ
የፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ እና የጅቡቲ ፋይናንስ ሚኒስትር ኢልያስ ሙሳ ዳዋሌህ ምን አሉ
ኢትዮጵያ ሁሌም የቀጣናው ምሰሶ፤ የሰላም ዘብ እና የቀጣናዊ ትስስር ትዕምርት ናት። በቀጣናው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ወሳኝ ሚና ያላት ሀገር ናት።
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ መዲናም ናት። አዲስ አበባ እንደ ስሟ ዛሬ አዲስ ሆናለች።
ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠንካራ አመራር ሰጪነት በፈጣን ለውጥ ላይ ናት። በአስገራሚ ሁኔታ ወደ ዘመናዊ ከተማነት እየተቀየረች ነው።
ጅቡቲ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ ናት።
ጅቡቲ ጠንካራ፣ ሰላማዊ እና በኢኮኖሚ የተሳሰረ ቀጣና ለመፍጠር በትብብር ከኢትዮጵያ ጋር ትሰራለች። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በቀጣይ ዕጣ ፈንታ እና የጋራ ህልሞች ለማሳካት መስራት ይገባቸዋል።
በአድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘቴ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል። አድዋ የአይበገሬነት፣ አንድነት እና የአሸናፊነት መንፈስ ተምሳሌት የሆነ ቦታ ነው።