የሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ኤስፒኤልኤም) ዋና ፀሐፊ ፒተር ላም ቦዝ ምን አሉ

 

👉 የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን የሁለትዮሽ ትብብር እና የግንኙነት አድማስ እያደገ መጥቷል። የናይል ትብብር ማዕቀፍ የሁለቱ ሀገራት ትስስር ዋንኛ ማሳያ ነው።

👉 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ የኢትዮጵያ መሪዎች ለደቡብ ሱዳን ላደረጉት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ። እ.አ.አ በ2025 ብቻ 632 ደቡብ ሱዳናውያን በኢትዮጵያ ነጻ የትምህርት እድል አግኝተዋል።

👉 ብልጽግና ፓርቲ ቃል የገባቸውን ተግባራት የፈጸመበት መንገድ እጅግ የሚደነቅ እና ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው።

👉 አዲስ አበባ በመሰረተ ልማት ግንባታ ከፍተኛ ለውጥ እያሳየች ነው። በከፍተኛ ሁኔታ ተቀይራለች። ፒያሳ ደማቅ ውበትን ተጎናጽፋለች።

👉 ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ በመሰረተ ልማት፣ በወደብ አገልግሎት፣ ትራንስፖርት፣ ኢነርጂ እና በኃይል ማመነጫ ግድብ ግንባታ ያላትን ትብብር ማጠናከር ትሻለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም