የካዛኪስታን የታችኛው ምክር ቤት እና የገዢው አማናት ፓርቲ አባል ሳማት ኑርታዛ ምን አሉ

 

👉 ኢትዮጵያ ለካዛኪስታን ታማኝ እና እውነተኛ አጋር ናት። ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ፣ የባለብዝሃ ወገን እና ሁሉን አቀፍ ትብብሯን ለማጠናከር ትሻለች።

👉ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ለቀጣናው እና ዓለም አቀፍ ደህንነት ቁልፍ አበርክቶ አድርጋለች።

👉የብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል። ብልጽግና ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር ረገድ ስኬታማ ተግባር አከናውኗል።

👉 አማናት ፓርቲ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ያለውን ግንኙነት እና ካዛኪስታን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጎልበት ይሰራል።

👉 አማናት ለዓለም ሰላም እና ብልጽግና ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በትብብር መስራት ይሻል።

👉 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ሰጪነት ብልጽግና ፓርቲ የለውጥ እና የሽግግር ተምሳሌት መሆን ችሏል።

👉 የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ባለ ራዕይ መሪነት፤ ውጤታማ አስተዳደር ሀገርን ከቀውስ በማውጣት ለዘላቂ ልማት መሰረት መጣል እንደሚቻል በግልጽ ያመላከተ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም